የግብጾች ያደረጉትን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አያውቅም ነበር -ነቢዩ ሲራክ

“ሰበር ሰናይ ዜና ከወደ ካይሮ … “ ሲል የዘገበው ጋዜጠኛ ነቡዩ ሲራክ በግብጻዉያን እጅ ስለተረፉት ኢትዮጵያዉይን ጉዳይ ለማጣራት በካይሮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስልክ ደዉሎ “መረጃው ትክክል አይደለም” የሚል ምላሽ እንደተሰጠዉና ጉዳዩን ኤምባሲው እንደማያውቀው ዘግቧል። ሆኖም ከርሱ ዜናውን ከሰሙ በኋላ አረጋግጠው፣ ለጋዜጠኛ ነብዩ መረጃዉን ትክክል እንደነሆነ ከይቅርታ ጋር መግለጻቸውን ጋዜጣኛው አሳዉቋል።

ጋዜጣኛ ነብንዩ የሚከተለውን ነበር ብሎግ ያደረገው ፡

ሰበር ሰናይ ዜና ከወደ ካይሮ …
* ሊቢያ ላይ በጭንቅ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ግብጽ ገቡ !
* የግብጹ ፕቴዚደንት ካይሮ አየር ማረፊያ ሄደው በክብር ተቀበሏቸው
* ግብጾች ታሪክ ሰሩ !
* ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ግብጽ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ስልክ ደውየ አንድ ኃላፊ ” መረጃው የለንም ፣ የተሳሳተ መረጃ ይሆናል ” ያሉኝ ቢሆንም ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ስልክ ደውለው መረጃው ትክክል መሆኑን ማረጋገጣቸውን ከይቅርታ ጋር ገልጸውልኛል
* የተመላሾች ቁጥር ሰላሳ እንደሚደርስና በቢንጋዜ ፖሊስ ተይዘው የነበሩ እንደነበር እኒሁ በግብጽ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የገለጹልኝ ሲሆን ተመላሾቹ በነገው እለት ወደ ሀገር ቤት እንደሚላኩ አክለው ጠቁመዋል!
ዝርዝሩን እመለስበታለሁ !
ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 29 ቀን 2007 ዓም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.