በማጀቴና አጣዬ በኦነግ ታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ማጀቴና አጣዬ በኦነግ ታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች የቀብር ስነስርዓት በዛሬው ዕለት ተፈጸመ።

የአካባቢው ነዋሪዎች  ከኦነግ ታጣቂዎች ጥቃት ሊሰነዘርብን ይችላል በሚል ስጋት ከስፍራው እየለቀቁ መሆናቸውን ኢሳት ያነጋገራቸው  ገልጸዋል።

በአጣየ ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ከባድ መሳሪዎች በያዙ የኦነግ ታጣቂዎች በተከፈተው ጥቃት 15 ነዋሪዎች መገደላቸው ተገልጿል።

በአጣዬ በነበረው ጥቃት ምክንያት መንገዶች ተዘግተዋል።

በጥቃቱ የቆሰሉ ሰዎችን ወደ ህክምና ማዕከላት ለመውሰድ እንዳልተቻለም ነዋሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል።

ኢሳት ዲሲ

2 COMMENTS

 1. ኦነግ በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያን ክፉነት ልክ እንደ ወያኔ ሃርነት ትግራይና እንደ ሻቢያ እየሰበከ ሲሻው የእስልምና ተከታይ ያለዚያም ክርስቲያን ነኝ በማለት በአረብ ሃገሮችና በጀርመንና በሳክንድኔቪያ ሃገሮች ድጋፍ በማሰባሰብ በአስመራ መሽጎ የኖረ አጥፊ ሃይል ነው። ለኦሮሞ ህዝብ እንደ ቆመ ተደርጎ የሚነዛው የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳም ከሚያልፍ ውሃ የተቀዳ ውሸት ነው። በመደመር ሂሳብ አሁን ሃገር ውስጥ በመግባት የፓለቲካ ሴሎቹን በይፋና በስወር እያስማማ የሚገኘው ይህ አጥፊ ድርጅቶ ከግብጽና ከወያኔ ሃርነት ትግራይ አይዞአቹሁ እንደሚባሉ ጥብቅ መረጃ አለ። አላማቸው ለሰላም ሳይሆን ሃገር ለመበጥበጥ በኦሮሞ ህዝብ ሲነግዱ የኖሩና ያሉ ለመሆናቸው ከሃገር ከገቡ በህዋላ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ያመላክታሉ። ሰው ይገላሉ፤ ባንክ ይዘርፋሉ፤ ሴቶችን ይደፍራሉ፤ ሃገራችሁ አይደለም በማለት ለይተው አናሳ ብሄሮችን ያዋክባሉ፤ ሃብታቸውን ይሰርቃሉ። ከዚህ በተሻገረ አማራ ጠላትህ ነው ብሎ ወያኔ ባቆመው የአኖሌ ሃውልት ተደግፈው የሰውን አንገት የሚቀሉት የኦነግ ወንበዴዎች ለኦሮሞ ህዝብና ለሃገር አንድነት ደንታ አይሰጣቸውም።
  የሚያሳዝነው በጊዜው መንግሥት ነኝ የሚለው ይህን ያህል ኦነግን መታገሱ ከሴራው ተካፋይ ሆኖ ነው ወይስ ፍራቻ? እንደ እነ በቀለ ገርባ ያለ አምታችን የኦሮሞ አቀንቃኞች ቋንቋን መግባቢያ መሆኑ ቀርቶ የፓለቲካ መሳሪያ ለማድረግ ቋንቋህን ከማይናገር አትግዛ፤ ኦሮሞ ካልሆነ አትጋባ እያለ ሚዲባል በሆነ እይታ በህዝባችን ላይ የጥላቻ ፓለቲካ ሲዘራ መንግስት ዝም ብሎ ይመለከተዋል። እንደ እነ እስክንድር ያሉት ደግሞ ሃገር የጋራ ነው በማለታቸው ዛቻና ማስፈራሪያ ከበላይ አካል ሳይቀር እየደረሰባቸው ይገኛል። ድመትን ዋና ማስተማር አይቻልም። ትንኝንም ከቆሻሻ ማጽዳት አይሞከረም። ለምን ቢባል ለሞት ይዳርጋልና። ኦነግን ሁለገብ እይታ እንዲኖረው ማድረግ አይቻልም። ጠ/ሚሩ በሚኒሶታ በመጡበት ወቅት ኢትዮጵያ ሳይሆን ያየነው የኦሮሞን አክራሪና ጠባብነት ነበር። የሚድኑ ሰዎች አይደሉም። ታመዋል። ታዲያ ምን ይደረግ? እኔ ተግባራቸውን አይዞአቹሁ ለሚሏቸው ስዎች በቪዲዮና በድምጽ በተደገፈ መረጃ (የፈጠራ ሳይሆን እውነት ላይ በተመረኮዘ) ለአለም ህዝብ ማሳወቅ፡ ጉርሻ የሚሰጧቸውንም የአረብ፤ የሰሜን አሜሪካ፤ የአውሮጳ ወዘተ… በማስረዳት የእርዳታ ምንጫቸውንና ተሰሚነታቸውን ማዳከም። ሁለተኛ – መስሎአቸውና አምነው ለዘመናት በፍዳ ከሚያመጡት ክፍያ መዋጮ ለሚሰጡ የኦሮሞ ተወላጆችና ድጋፊዎች መረጃን ተደግፎ የሚሰሩትን ማሳየት፤ ሰዎች ሁኔታዎን ወደ ሃገር ብቅ በማለት እንዲያዪ በማድረግ የኦነግን የገቢ ምንጭና የተንሻፈፈ የፓለቲካ ስልት ማድረቅ ይቻላል። ሶስተኛ – የኢትዮጵያ መንግስትና በአቶ ለማ የሚመራው የኦሮሞ ህዝብ የፓለቲካ ቢሮ በተቀናጀ መልኩ የኦነግ ጠበንጃ አንጋቾችን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት አለበት። በልመና የሚቆም ቢሆን ኑሮ አባገዳዎች ከወራት በፊት ባደረጉት ስምምነት ይመክን ነበር። እንደዚያ ዓትነት የስምምነት ጉዳይ ጊዜ ለመግዛትና ከደጋፊዎቻቸው ጋር የጥምረት እቅድ ለማውጣት ኦነግን ይጠቅማል እንጂ ለሰላም ልብ የላቸውም። አሁን በሃገራችን በዶ/ር አብይና ለማ የመደመር ፓለቲካ የምናየው ትንሽ እፎይ የሚያሰኝ የፓለቲካ አየር በኦነግና በሌሎች ዘርና ጎሳ ተከል ፓለቲካ ተከታዮች ክፋት የተነሳ ወደ እማያቋርጥ መከራ እንደሚከተን ከአሁን መገመት ይቻላል። በመሰረቱ የሃገሪቱ ችግር ህገ መንግሥቱ ነው። የክልል ፓለቲካ መላ ሃገርንና አንድነትን አያይም። ኦነግ አይቀጡ ቅጣት ከተቀጣ ሌሎቹም ኑና ግጠሙን የሚሉ ሁሉ ሰከን ይላሉ። ይህ እስካልሆነ ድረስ ሰካራሙና ጫት ያመረቀነው ሁሉ አለቃ እንሁን ማለቱ አይቀርም።

 2. * የሚያሳዝነው በጊዜው መንግሥት ነኝ የሚለው ይህን ያህል ኦነግን መታገሱ ከሴራው ተካፋይ ሆኖ ነው ወይስ ፍራቻ?

  Abiy = OLF

  ODP = OLF

  What more evidence do you need to realize that ?

  You said it yourself: እንደ እነ እስክንድር ያሉት ደግሞ ሃገር የጋራ ነው በማለታቸው ዛቻና ማስፈራሪያ ከበላይ አካል ሳይቀር እየደረሰባቸው ይገኛል።

  * ሶስተኛ – የኢትዮጵያ መንግስትና በአቶ ለማ የሚመራው የኦሮሞ ህዝብ የፓለቲካ ቢሮ በተቀናጀ መልኩ የኦነግ ጠበንጃ አንጋቾችን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት አለበት።

  What … , are you kidding ?

  ODP = OLF !

  Abiy’s (=OLF) mission is “to liberate oromia”. Wake up !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.