ግንቦት 7 ራሱን ከፎቅ ከስክሷል – የኢሳት ባልደረባ ካሳሁን ይልማ የግል ምልከታ

አርበኞች ግንቦት 7 ራሱን ከፎቅ ከስክሷል –
ዘረኞችም ገበያ ይደራላቸዋል
===============================
ከፕሮፍ ብርሀኑ የኦቢኤን ቃለምልልስ ቅንጫቢ ንግግር የተረዳሁት ሁለት ነጥቦችን ነው።

1.የፓርቲው ሁለት ዋና አመራሮች ወቅታዊ የፖለቲካ አረዳድ ለየቅል ሆኗል:: አቶ አንዳርጋቸው ከሰሞኑ በሰጧቸው ሁለት ቃለምልልሶች ያደመጥነው የእነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ሀዲድ እየሳተና ሀገሪቷ ወደለየለየት እርስበርስ ግጭት እያመራች መሆኗን ነው።ፕሮፍ ብርሀኑ ደግሞ የሚያሻግረን የእነ ዐቢይ መንገድ ነው ይላሉ:- “ዶክተር ዐቢይ፣ አቶ ታከለ ሆነ አቶ ለማ አሻጋሪዎቻችን ናቸው::”
ሁለቱ አንጋፋ ፖለቲከኞች የዛሬ ዓመት የነበራቸው አመለካከት አንድ እንደነበር ያስታውሷል። አሁን አንዳርጋቸው ይሰጋሉ፣ ብርሀኑ ተሰፋ ያደርጋሉ።

2.ፕሮፌሰሩ የእነ እስክንድር ባልደራስ ምክርቤትን “ባለአደራ የሚባለው ነገር ትክክል አይመስለኝም” ሲሉ በቀጥታ የዐቢይን ተቃውሞ ይደግማሉ።

ይህ ምን ማለት ነው? አርበኞች ግንቦት 7 ላይስ ምን ያስከተላል?
=================
ፕሮፍ ብርሀኑ በእነ ዐቢይ ላይ የፀና እምነት የጣሉበት የራሳቸው አሳማኝ ምክንያት ሊኖራቸው ቢችልም የድርጅታቸውየደጋፍ መሠረትን ያላገናዘበ ነው። በእነ ዐቢይ የአንድ ዓመት ሥልጣን ዘመን በርካታ ለውጦች ቢታዩም በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ሕዝብ ላይ የተቃጣው ጥቃትና ስጋትን የቡራዩ ተፈነቃዮችን ከመጎብኘት በስተቀር ማውገዙ ቀርቶ በአደባባይ ሕመሙን አለመጋራታቸው እምነት የጣለባቸውን ደጋፊ መሠረት እየናደ ነው።
የእነ ዐቢይ መንግሥት በአክራሪ ኦሮሞ ፖለቲከኞች ሴራ በየቦታው መሠንጠቅ እንዲገጥመውና ለውጡ እንዲደናቀፍ ማፈናቀልና የኬኛ ስግብግብ ፖለቲካን ሆን ብለው እያራመዱ እንደሆነ ቢገለጽም ያንን የማክሸፍና ሕዝብን አንድ አደርጎ ሀገርን የመምራት ኃላፊነት በዋነኛነት የሥርዓቱ ፈንታ እንጂ የአርበኞች ግንቦት 7 አይደለም። የተቃዋሚ ድርጅቱ ኃላፊነት ለውጥ እንዲደናቀፍ መንስዔ ባለመሆን የራሱን ፖለቲካ በማራመድ የደጋፊዎቹንና የሕዝብን ጥያቄ አጀንዳው እያደረገ በአጭርና ረጅም ጊዜ እቅድ ምላሽ መፈለግ ነው። ይሁን እንጂ አርበኞች ግንቦት 7 ከተቃዋሚ ድርጅትነት ይልቅ ወደ እነ ዐቢይ መንግሥት ፍጹም ደጋፊነት ተቀይሯል። ሀገር እንድትረጋጋ ከገዢ ሥርዓት ጋር መተባበርና የራስን ሕዝባዊ መሠረት መጣል ለየቅል ነው። ለራስ ፓርቲ አደጋው ከፍተኛ ነው። ከዚያ ይልቅ አንድ ፊቱን ከኢህአዴግ ጋር መዋሃድ ይሻላል።

በተለይ የእነ እስክንድር እንቅስቃሴ ላይ የተያዘው አቋም ራስን ከፎቅ ከፍታ እንደመከስከስ ነው። ስሌቱ ተወራርዶ የማያልቅ ዋጋ የሚያስከፍል ነው።በመከራ ዘመን የታነፀ ሕዝባዊ ድጋፍን አሁን በተገኘው የመንቀሳቀስ ዕድል ይበለጥ አደራጅቶ ለምርጫ የመዘጋጀት አጋጣሚ አምልጧል። እውነቱን ለመናገር ድርጅቱ በዚህ ከቀጠለ ድጋፍ ሊያገኝ የሚችለው ምናልባት በኃዘኔታ ጀረባውን መታ-መታ ሊያደርጉት ከሚችሉ የዐቢይ ደጋፊዎች ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ አልማዝን ባህር ውስጥ ወርውሮ እንደመፈለግ ይሆናል። ፖለቲካ ውለታ አያውቅም።

ይህ ምን ይፈጥራል?
==================
በተለይ የአንድነት ፖለቲካ የሚያራምዱ ድርጅቶች የሌሉት ደጋፊ ሌላ ምንም አማራጭ መግቢያ ያጣል። ይህ ደግሞ ለዘረኞቹ የብሔር ድርጅቶች ትኩስ ገቢያ ይፈጥራል። ዘረኞች እንደሚያደርጉት ቅድመ አያት ፣ እናት፣ አጎት … ወዘተ የዘር ሐረግ ቆፍረው እየፈለጉ ወደ አብን፣ ኦነግ፣ ህወሓት፣ … እና ሌሎች የብሔርተኛ ድርጅቶች ይሰገሰጋሉ። የፀና ብቻ ሀገሩን አስቀድሞ ኢትዪጵያዊነቱን ይዞ የራሱን ትክክለኛ መርከብ ይፈልጋል። የሚያሻግረው የራስ አቋም ነው።

ማሳሳቢያ 🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመለስ በታች መቃብር ውስጥ ያለውን ሙት ልደቱ አያሌውን ይቺን አጋጣሚ ተጠቅሞ ያለኃፍረት ወደ መድረክ ለመጎተት የምትደረገው ጉተታን እዚያው መቃብር ውስጥ ተውት። አማራ ቅብርጥስዮ የዘር ጭምብል አይሰራም።
ሌላው ትምህርት መጨረስ አቅቶት በብርሀኑ እያሳበበ ውድቀቱን ለመሸፋፈን የሚጥረው እብድ መዳኛ የለውም።

(ለበለጠ ግንዛቤ የፕሮፍ ብርሀኑን ሙሉ ቃለምልልስ መስማት ያስፍለጋል)

6 COMMENTS

 1. Who knew Berhanu was a sell out. He has actually supported the current race based system on one of his interviews before but that was never given any focus. There was also his alignment with the father of race based politics, Lencho Leta himself that sent a clear message for most of us but not picked up by many. And when he instructed ESAT to apologize to the OLF and its cohorts on someone’s honest opinion. Well the cat is out of the hat, better to know sooner than later. Kudos to Neamen Zeleke for disassociating himself from the G7 and telling us in no uncertain terms when he said some leaders in the G7 were supporters of race based politics under the clock of Ethiopianism. Thank you Neamen for being honest, forthright and fighting for Ethiopians from your heart. My emotional self hoped Berhanu will come out swinging as the champion of total emancipation of Ethiopians from the clutches of race, even if my logical self disagreed with the thought, obviously logic won in the end. Talk about hunger for power another one bites the dust. How sad.
  Enqoqo

 2. ” አቶ አንዳርጋቸው ከሰሞኑ በሰጧቸው ሁለት ቃለምልልሶች ያደመጥነው የእነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ሀዲድ እየሳተና ሀገሪቷ ወደለየለየት እርስበርስ ግጭት እያመራች መሆኗን ነው። ”

  The above is absolutely correct !

  Even a blind can see in Ethiopia that the country is on the wrong track and close to civil war. The people had so much patience with Abiy and after 12 months he hasn’t changed anything fundamental yet !

  Why wait any longer ?

  Abiy had enough time to practice what he preached. But he didn’t do that. So, we must demand his immediate resignation.

  .

  ፕሮፍ ብርሀኑ ደግሞ የሚያሻግረን የእነ ዐቢይ መንገድ ነው ይላሉ:- “ዶክተር ዐቢይ፣ አቶ ታከለ ሆነ አቶ ለማ አሻጋሪዎቻችን ናቸው::”
  ሁለቱ አንጋፋ ፖለቲከኞች የዛሬ ዓመት የነበራቸው አመለካከት አንድ እንደነበር ያስታውሷል። አሁን አንዳርጋቸው ይሰጋሉ፣ ብርሀኑ ተሰፋ ያደርጋሉ።

  2.ፕሮፌሰሩ የእነ እስክንድር ባልደራስ ምክርቤትን “ባለአደራ የሚባለው ነገር ትክክል አይመስለኝም” ሲሉ በቀጥታ የዐቢይን ተቃውሞ ይደግማሉ።

  ይህ ምን ማለት ነው? አርበኞች ግንቦት 7 ላይስ ምን ያስከተላል?
  =================
  ፕሮፍ ብርሀኑ በእነ ዐቢይ ላይ የፀና እምነት የጣሉበት የራሳቸው አሳማኝ ምክንያት ሊኖራቸው ቢችልም የድርጅታቸውየደጋፍ መሠረትን ያላገናዘበ ነው። በእነ ዐቢይ የአንድ ዓመት ሥልጣን ዘመን በርካታ ለውጦች ቢታዩም በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ሕዝብ ላይ የተቃጣው ጥቃትና ስጋትን የቡራዩ ተፈነቃዮችን ከመጎብኘት በስተቀር ማውገዙ ቀርቶ በአደባባይ ሕመሙን አለመጋራታቸው እምነት የጣለባቸውን ደጋፊ መሠረት እየናደ ነው።

  WARNING !

  Berhanu Nega is not credible.

  There is no basis for his trust in the Abiy government.

  The Ethiopian people very well know Abiy and his government, and they have concluded that Abiy didn’t practice what he preached to them.

  Why can’t Berhanu Nega see that ?

  Well Berhanu Nega is a dubious person, we know his destructive role within Qinijit in 1997/2005.

  And Eritrea and the West pay and control him.

  So, he supports Abiy because Eritrea and the West ordered him to support Abiy.

  Berhanu Nega is not an independent individual.

  Also, Eritrea, the West and Berhanu want to prevent Ethiopian nationalist forces from taking power.

  That explains Berhanu Nega’s position.

 3. የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲህ የዘቀጠዉ እንደ ካሳሁን ይልማ አይነት የተጻፈ ዜና አንባቢዎች የኛን አይነት ዉጥንቅጡ የወጣ ፖለቲካ ዉስጥ እየገቡ ሲፈተፍቱ ነዉ- ካሳሁን እንኳን ብርሃኑ ለምን ያለዉን እንዳለ ቀርቶ ከዚያም ያነሰ ተራ ነገር ላይ መተቸት የማትችል ኢሳት ባይኖር ኖሮ መኪናቸዉን ከሚያሳጥቡ ኢትዮጵያዊያን ዉጭ ማንም የማያዉቅህ ከተራም ተራ ሰዉ ነህኮ! አስኪ አንተ ስታስበዉ ማነዉ ለእስክንድር ነጋ የአደራ የአዲስ አበባ አስተዳደር እንዲያቋቁም የፈቀደለት? አንተ ደደብ ከደደብም ደደብ! በቃ ዳያስፖራ መኖር የእዉቀት ምልክት መስሎህ ከሆነ እኔ በሚገባ ስለማዉቅህ እሱን ልተወዉ- አባክህ አንተም ስለፖለቲካዉ ለሚያዉቁ ተዉላቸዉ- ቴሌቪዥን መስኮት ላይ መቅረብ የማወቅ ምልክት አይደለም! እስክንድር ነጋ አዲስ አበባዎችን ለመብታቸዉ እንዲታገሉ ማደራጀት መብቱ ነዉ፥ የታከለ ኡማ አስተዳደር ህጋዊነት የለዉም ብሎ በጎን ሌላ ባለ አደራ አስተዳደር አዘጋጅተናል ማለት ግን በህግ የሚያስጠይቅ ጥፋት ነዉ። ይህ መታወቅ አለበት!! ባንተና በመሰሎችህ እይታ እስክንድርን የማያስጠይቀዉ አማራ መሆኑ ብቻ ነዉ። እስክንድር ኦሮሞ ቢሆን ኖሮ የመጀመሪዉ ዱላ የሚወረወርበት ካንተዉ ይሆን ነበር- እባክህ ካሳሁን እራሳህን እወቅ!

 4. ጉራ ፈርዳ
  በዬትም ሀገር እስክንድር ነጋ የሰራው ህገወጥ ነው:: በዚህ እንስማማለን:: ዶክተር ብርሀኑም የሰጠው አስተያየት ከአንድ አዋቂ የፖለቲካ መሪ የሚጠበቅ ነው::የእስክንድርን አማራነት መግለፅህ ያንተን የወረደ ዘረኝነት ያሳያል::ቴዎድሮስ ፀጋዬ ( ርእዮት) አቋሙ የተለየ አይደለም እሱም አማራ ስለሆነ ነው?

 5. ” And that blind man is you! ”

  I see, you are an Abiy supporter.

  Instead of throwing insults you could have use arguments.

  Why on the wrong track ?

  1. There is still tribalism in the country, leading to tensions ( ውጡልንና ዛቻ በአሰላ ከተማ እየተሰማ እንደሆነ ተዘገበ ), conflicts, violence, evictions, humanitarian crises like the one against the Gedeo ( ለጌዴኦ ተፈናቃዮች ዕርዳታ እንዳይደርስ ያደረጉ በሕግ ይጠየቁ! )

  2. Tribalism and the Killil system are now leading to civil war

  That is the reality mr. Dreamer.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.