መስከረም 27 ቀን 2011 ዓም የዐኅኢአድ በጎንደር ከተማ ሲኒማ አዳራሽ በርካታ ሕዝብ በተገኘበት የድርጅቱን ዓላማና የወደፊት የጉዞ አቅጣጫውን ያመላከተ ውይይት ከሕዝቡ ጋር አድርጏል::
በዚህ ስብሰባ የድርጅቱ አመራር አባል የሆኑትብ አቶ ተስፋዬ መኮንን ስለድርጅት ምንነትና ዐማራው የተጋረጠበትን የኅልውና አደጋ ተቋቁሞ የኢትዮጵያን አንድነት የማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከመደራጀት ሌላ የተሻለ አማራጭ እንደሌለ በስፋት አብራርተዋል::
አቶ ተክሌ የሻው በበኩላቸው የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አመሠራረት: ዓላማ : ተልዕኮ እና ግቦች ምን እንደሆኑ በማስረዳት ዐማራ የሆነ ሁሉ ኅልውናውን ታድጎ የኢትዮጵያን አንድነት ለማረጋገጥ ባመነበት የዐማራ ድርጅቶች ዙሪያ መሰባሰብ እንዳለበት አሳስበዋል::