የአግአዚ ወታደሮችባሕር ዳር ዩንቨርስቲ የተማሪዎችን ዶርም ሰብሮ በመግባት በአሰቃቂ ሁኔታ እየደበደባቸው ይገኛል


ተማሪዎቹም የወያኔ አብሪ ጥይት በሆነው ብአዴን ወያኔ ልዩ ሃይል እየተደበደቡ ነው ።
ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ውጭ በየትኛውም ዩንቨርስቲ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የለውጥ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ይገኛሉ !!







#አዲግራት_ዩኒቨርስቲ ((( ከቀኑ 9:00)))
<< 15 ተማሪዎች በመጥፋታቸው እጅጉን ተጨንቀናል፡፡>>
.
….ዛሬ በአዲግራት ዩኒቨርስቲ መጠነኛ መረጋጋት እንዳለ ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል፡፡ የጊቢው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሠራዊት እጅ ወድቋል፡፡ የተማሪዎች እንቅስቃሴም በጊቢ ውስጥ ተወስኗል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሠሞንኛው ሁኔታ አስፈርቷቸው ወደገዳማት ለመጠጋት በሚል ፤ ከጊቢ አምልጠው የወጡ 15 ወጣቶች እስካሁን የት እንዳሉ አለመታወቁ እጅግ እንዳሳሰባቸው የዩኒቨርስቲ ጓደኞቻቸው ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹ ከትናንት ወዲያ ጀምሮ የእጅ ስልካቸው አለመስራቱና አንድም አየናቸው የሚል ሰው መጥፋቱ ፤ << ክፉ ነገር ገጥሟቸዋል፡፡ >> የሚል ጥርጣሬ እንደፈጠረባቸው ጓደኞቻቸው ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል << የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቤተሠቦቻችንና ወዳጆቻችን የተቆረጠልንን የበረራ ትኬት እንዲሰረዝ ማድረጉ እጅግ አሳዝኖናል ፡፡ >> ሲሉ ፤ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
(ማሳሰቢያ ፦ ለቤተሠብና ለልጆቹ ደህንነት ሲባል ፤ የልጆቹን ማንነት ለመግለፅ አልተፈለገም፡፡ )
((( ዘሪሁን ገሠሠ )))