የአማራ ሕዝብ አሁን እየደረሰበት ላለው መከራ የበቃነው ጠላታችንን እጅግ በመናቃችን፣ በዋህነታችንና በደግነታችን ምክንያት ነው!

(ቬሮኒካ መላኩ)

አንዳንድዬ በአእምሮዬ እየመጣ እረፍት የሚነሳኝ ጥያቄ አለ። እኛ የሁሉም ነገር የፊት ተሰላፊ ሆነን እያለ ፣ የጄግንነትን ሀ ሁ ሂ አስተማሪዎችና ፊታውራሪዎች መሆናችን የተረጋገጠ ሆኖ እያለ አሁን ለደረስንበት ” ዝቅታ ” ያበቃን ምን ይሆን ብዬ ራሴን እጠይቃለሁኝ።

ይሄን ጥያቄ አውጥቼ አውርጄ የማገኘው መልስ “ለዚህ የበቃነው ጠላታችንን እጅግ መናቃችን ፣ የዋህነታችንና ደግነታችን ነው” የሚል መልስ ይሆናል።

እርግጥ ነው እኔ ራሴ በፊትም እንቃቸው ነበር አሁንም እነሱን የማስቀምጠው በሰው ዘር ግርጌና በእንስሳ ራስጌ መካከል ነው። መናቅ ብቻ ሳይሆን እጠየፋቸዋለሁኝ።

እነዚህ ሰዎች የተሟላ ሰብዕናና ግብረገብነት የሌላቸው ፍጡር ስለሆኑ ናቅናቸው።ቢያንስ እንደ አማኝነታችን ” እንደ እርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልህ ሁን።” የሚለውን ቅዱስ ቃሉን ብንሰማ ጥሩ ነበር። እኛ ግን እርግብን ስንመርጥ እነሱ እባብን መረጡ።

እርግጥ ነው ዛሬ መሬታችን መወሰዱ ለጊዜያዊነት ሊያስቆጣኝ ፣ስሜቴን ሊነካው ይችላል ነገር ግን ብዙ አያወራጨኝም። አማራ አንድት ስንዝር መሬትና አንድ እፍኝ አፈር ሳትቀር እንደሚያስመለስ ስለማውቅና እርግጠኛ ስለሆንኩኝ ብዙም አያስጨንቀኝም። መሬት ተቆርሶ ኪስ አይገባ ወይም ወደ አሜሪካና እንግሊዝ ባንክ አያሸሹት። የጊዜ ጉዳይ ነው።

ይሄን የምለው ወለምታ ቢጤ ነካ ያደረገውን ልባችንን በስነ-ልቦና ወጌሻ ለማፅናናት አይደለም። እንደ ፀሀይ ፍንትው ያለ ሀቅ ስለሆነ ነው።

የእነዚህ ሰዎች ስግብግብነት አቻ አይገኝለትም። የማይጠረቃ ስግብግብነታቸውን ለማርካት ሲሉ እንኳን መሬት መውሰድ ይቅርና አዲስ ከተወለደ ህጻን ጉሮሮ ፈልቅቀው፣ ከወላድ እናት የጡት ወተት የሚዘርፉ ዓይነት ናቸው። ዛሬ እነሱ ያላጋበሱት መሬት የለም። ጋምቤላ ኗሪውን አፈናቅለው መሬታቸውን ወርረዋል። ቤኒሻንጉልም “ብዛት ስላለን ልዩ ወረዳ ይሰጠን ” እያሉ ነው። የአፋሮችን የጨው መሬት ቀምተዋል። እነዚህ በደማቸው ሳይቀር አነሱንና የነሱ የሆኑትን ብቻ የሚመግቡ፣ ውስጣቸው በድንጋጤ ድባብ የተሞላና ከፍርሃታቸው የተነሳ በጨለማ የሚተኩሱ፣ የህዝብ ፍቅር፣ የሀገር አንድነትና ሰላም እንደ ቀትር የአቀበት ጉዞ የሚተናነቃቸው፣ ለመገንባት ሳይሆን ለጥፋት የተሳሉ፣ በአይምሮ ዋሻ ውስጥ የጥፋት ባህር ሠርተው የሚዋኙ እፉኝቶች ናቸው።

መፍትሄው ምንድነው?

ራስን ለማበልፀግም ሆነ ራስን ከጥቃት ለመከላከል ራስን ማወቅና ማንነትን ፈልጎ ማግኘት አይነተኛ ቁልፍ ነው። እኛ ዘግይቶም ቢሆን ራሳችንን ፈልገን አግኝተናል። ማንነታችን አማራ ነው ብለናል። ከዚህ ቅርቃር መውጫ መፍትሄው አማራዊነት አደረጃጀት ፣ አማራዊነት መንፈስ ነው ብለን ጉዞ ከጀመርን ቅርብ ጊዜ ቢሆነንም ጥሩ እየተጓዝን ነው።

የአብሮነት ገመዳችን ለመቁረጥ እለት ተእለት ለሚሳለው የጎጠኝነት ጎራዴ ሳንበገር አማራነታችንን ማጥበቅ አለብን።

ዛሬ ችግሩን ተንትነን የአማራዊነት መንፈስ የተቃኜ አንድ ወጥ አደረጃጀት ካልፈጠርን እንደ ግሪካዊው የአፈ-ታሪክ ሰው ሲሲፐስ ቋጥኝ ድንጋይ ቀጥ ባለ ተራራ ወደ ላይ ለዘላለም መግፋት ነው የሚሆነው።

አማራዊነት ስለ አማራ ነፃነት የሚዋትተው አማራን ከዘረኛ የወያኔ ወጀብ ለመከላከል እንጂ አንዳንዶች እንደሚፈሩት፣ የአማራን ማንነት በዘረኛ እርሾ አቡክቶ ለመጋገር አይደለም።

የአማራዊነት ጥረትና ግብ ወያኔ የሰረቀውን የአማራ አካላዊና መንፈሳዊ ርስት አስመልሶ ለአማራ ሌላ ህዝቦች ቁመቱና ወርድ የሚመጥን ደሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት ነው። አማራዊነት ለሌሎች ሌላ ሊሆን ይችላል። ለእኛና አኛን መሰሎች ግን፣ የደም ዋጋ፣ የህይወት ምንዳ፣ የማንነት ስንክሳር፣ የአባቶች አደራ፣ የፈጣሪ ትሩፋት፣ የመኖርና ያለመኖር ማተብ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.