ሁሉም ሊነቃበት የሚያስፈልገው አደገኛው የሰሞኑ የወያኔ ደጋፊዎች አካሄድ – ሰርፀ ደስታ

እባብ ሞኝን ሁለት ጊዜ ነደፈው ይባላል፡፡ አንዴ ሳያየው በሌላ ጊዜ ደግሞ ሞነገድ ላይ ከጓደኛው ጋር ሲሄድ የተጠቀለለ እባብ ያይና ባለፈው የነደፈኝ ነገር ይሄ ነው ብሎ በጣቱ እባቡን ነክቶ ለጓደኛው ሲያሳይ ነው፡፡የእኛን ነገር ሳስበው ግን ከሞኙም ባስን፡፡ ስንቴ በመርዘኞች እንደምንነደፍ አላውቅም፡፡ ሰሞኑ በሆኑ በሆኑ አጋጣሚዎች በየኢነተርኔቱ ያሉ ነገሮችን ሳይ አሁንም እየተሸወደ ያለው ሕዝብ ቀላል አይመስልም፡፡ የወያኔ ደጋፊ የነበሩ ሚዲያዎች ጸጉራቸውን ቀይረው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳቢና ኢትዮጵያዊ መሆናቸው በራሱ አስቂኝ ሆኖ ብዙ የሚባለው ሰው እነሱ የሚሉትን እያነሳ አብሮ ሲያጫፍር ሳይ ዛሬም አይገባንም እንዴ ብዬ አዝኛለሁ፡፡ ይህ ደግሞ መሸወድ እየሆነ ያለው ትልቅ አገራዊ ፍቅር ያላቸውና ስለኢትዮጵያ ብዙ ማስተዋል አላቸው የምላቸውን ግለሰቦች ጨምሮ ነው፡፡ አንዳነዶቹ በዚህ ጉዳይ ብተቻቸው ይቀየማሉ ብዬ ስለማላስብ በቀጥታ ስማቸውን እጠቅሳሉ፡፡ በዛው ልክ የኢትዮጵያ ጠላቶች ያለ የሌለ ኃይላቸውን እየተጠቀሙ ነው፡፡ ደስ የሚለው ግን ለብዙዎቻችን ደግሞ ልዩ ሚስጢር እንድናውቅ ተደርገናል፡፡ ጠላቶቻችን ጠቃሚ መረጃዎች እየሰጡን ነው፡፡ እስኪ የተወሰኑትን ላንሳ

የሪፖረትር ጋዜጣ ርዕሰ ዐንቀጽ፡

ብዙዎቻችን እንደምናውቅው የኢትዮጵያው ሪፖረተር ጋዘጣ ከወያኔ እድሜ ጋር እኩል ያለመቸገር የቀጠለ ብቸኛው የግል ጋዜጣ ነው፡፡ ይህ ጋዜጣ አሁን አድጎ የምስል ዜና አቅራቢም ሆኗል፡፡ በድጋሜ ብቸኛው የግል ጋዜጣ ወያኔ ከገባ ጀምሮ ያለማቋረጥ ሲሰራ የነበረ፡፡ የግል የሚለውን በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ይደረግልኝ፡፡ የዚህ ጋዜጣ በብቸኝነት ለዚህ ሁሉ ዘመን መዝለቅ ከሌሎቹ በተለየ የጋዜጠኝነት አገልግሎት በመስጠት አልነበረም፡፡ ይልቁንም በብቸኝነት አንጋፋ እንዲሆን ከወያኔ በቂ ድጋፍ ስለሚደረግለት ጭምር እንጂ፡፡ ብዙ የሕዝብ ልሳን የነበሩ ጋዜጦችማ ዕድሚያቸው ከ6 ወር አንኳን በላይ የዘለሉ ስንት እንደሆኑ አላውቅም፡፡ አዘጋጆቻቸውም ዛሬ ወይ እስር ቤት ናቸው ወይም ደግሞ አገር ጥለው ተሰደዋል፡፡ ታዲያ ሰሞኑን ወያኔን በመተቸት ርዕሰ አንቀጽ ያወጣው አንጋፋው ጋዜጣ ሪፖርተር በምን ምትሀታዊ ችሎታው ነው እዚህ የደረሰው የሚያስብል ምንም ሞጋች ሚስጢር የለውም ለወያኔ በወሳኝ ጊዜ ወሳኝ ልሳን ሆኖ ማገልገሉ ነበር እንጂ፡፡ ጋዜጣው በጣም ገበያ አለው ዜናዎችንና ዘገባዎችን የሚያቀርበው ሁሉም በተጠናና ሕዝባዊ በመምሰል ነው፡፡ ለወያኔዎች ርፖርተር የቱንም ያህል ቃላት ቢጠቀም ትርጉም ይገባቸዋል፡፡ ለእነሱ ሕልውና ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን መጠቆም እንጂ መንቀፍ እንዳልሆነ አሳምራው ያውቁታል፡፡ ይልቁንም ሕዝብ ምን እያለ ነው ብለው ሕዝብን የሚሰልሉበት አንዱመ መንገዳቸው በመሆኑ ርፖርተርን በጣም ይደግፉታል፡፡ አዘጋጁ በሆነ ወቅት ታስሮ እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ እንደነ እስክንድር ነጋ ግን አልነበረም፡፡ ይልቁን የዚህ ጋዜጣ አዘጋጅ መታሰር ቁማጁር ነበር፡፡ አዘጋጁ ትክክለኛ የግል ጋዜጣ አዘጋጅ እንሆነ ለማሳየትና በስለላው ተግባር እንዲያገለግል ልዩ ስልት ነበር፡፡ ወያኔዎች አነድን ሰው ለረጅም ጊዜ ሲፈልጉት የሚያደርጉት ይሄንኑ ነው፡፡ ያስሩትና አንደ 3 ወር የሆነ ቦታ አቆይተው ዋና ተቃዋሚ አስመስለው ለሕዝብ ማደናገር የሚጠቀሙባቸው በዙ አባሎች አሏቸው፡፡ የሪፖርተር አዘጋጅ ደግሞ የተሰጠው ሚና ለራሱ ጥሩ ቢዝነስ እየሰራ ለወያኔ ጆሮ መሆን ነው፡፡ ዛሬ ጋዜጣውን ብታዩት መጻፍ እንጂ ጋዜጣም አይመስልም፡፡ በጣም አብዛኛው የጋዜጣ ክፍል የሚሸፈነው በማስታወቂ ነው፡፡ የንግድ፣ የሥራ ምኑ ቅጡ ምን አለፋችሁ ሁሉም ሪፖርትር ላይ ካላወጣህ ማስታወቂያህ ፍጹም አይታይልህም የተባለ ነው የሚመስለው፡፡ ለነገሩ እውነት ነው ሌላ ምን አማራጭ አለ; ሌሎች እንደዚህ ጋዜጣ እድል ቢያገኙ ሪፖርተር በውድድር ላይዘልቅ ሁሉ ይችል ነበር፡፡ ወያኔ ሌሎችን ጋዜቶች እያፈነችለት በብቸኝነት ሁሉንም ለመቆጣጠር ስችላዋለች፡፡ እሱም ቢሆን ይህን ውለታ ያውቀዋል፡፡ ዛሬ ሕዝብ ጋዜጣውን የሚገዛው ዜና ሊያነብ ሳይሆን ማስታወቂያ ሊያነብ ነው፡፡ ሌላ ምንም አማራጭ የለውምና፡፡ በገዛ ገንዘቡ የጠላቱን ኪስ ለማደለብ የተገደደ ሕዝብ ይልሀል ይሄ ነው፡፡

ሰሞኑን ታዲያ ከብዙ ጉዳዮች ጋር እያያዘ ወያኔን የሚተች የሚመስል ርዕሰ አንቀጽ አስነበቦ ልክ ነው ያለው ብሚል ለራሱ ብዙዎችን አስጨብጭቧል፡፡ አንሸዋወድ፡፡ እባብ ሞኝን የነደፈው ሁለቴ ነው እኛ ግን ዘላለም እየተነደፍን እንኖራለን፡፡ ሪፖርተር ያደረገው ግን ለወያኔ የተሰለፈበትን የሥለላ ተግባር ለራሱ ገበያን ነው፡፡ ወያኔም በዚህ ሥራው በጣም ታመሰግነዋለች እንጂ እንዴት አንተ ትተቸኛለህ አትልም፡፡ እንዲህ ያሉ ርዕሰ አንቀጾችን ሲያወጣ ደግሞ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ሁሌም ወያኔ ውጥረት ውስጥ ስትሆን የሚያደርገው ማደናገሪያ እግረመንገድም ለወያኔ ባለስልጣናት ጥቆማ የሚሰጥበት ሥራው ነው፡፡ ብዙ ሰው በዚህ ጉዳይ እየሸወደ ነው፡፡ እንደነ አለምነህ ዋሴ የመሳሰሉት ጋዜጠኞች ሳይቀሩ ሲያስተጋቡት ሰምተናል፡፡ አለምነህ እጅግ ተሸውደሀል፡፡ ይህን ርዕሰ አንቀጽ እኮ ያወጣው ሪፖርተር ነው፡፡ ሌላ አሁን አንኳን የሉም ግን ከድሮ ጋዜጠኞች አንዱ ቢሆን ያወጣው እንኳን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዛሬ እንደልባቸው ሁሉንም መግደልና ማስር እንዲችሉ ሕግ አውጥተው በየትኛውም ዘመን አሸባሪ በሚል ቃሊት ከመወርወር ሌላ እድል አይኖረውም፡፡ ስንቱ ጋዜጠኛ ምን ክፉ ነገር ጽፎ  ነው ዛሬ በየእስር ቤቱ እየማቀቀ የሚገኘው፡፡ ሪፖርተርና ወያኔ የሚግባቡበት ርዕሰ አንቀጽ ነበር፡፡ በዛውም የፕሬስ ነጻነት አለ የሚል ፕሮፓጋንዳ ለማስነዛት፡፡ ምን አልባት ዛሬም አያፍሩምነና፡፡ ከዚህ የዘለለ ግን ለሕዝብ ከማዘን እንዳልሆነ እርግጠኞች ነን፡፡ ቆሻሻ ቢናድበት በጥይት ቢያልቅ ሌላም ሌላም ለዜናቸው ጥሩ ግብዓት ከመሆን የዘለለ ሪፖርተርንና እንደነዛሚ 97ን የመሳሰሉ ሚዲያዎችን አይመለከታቸውም፡፡ ለዜና ግን ጥሩ እድል ይሰጣቸዋል፡፡ ሪፖርተር ማለት ይሄ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ፊርስትና ቤን

ይሄ የወያኔ ቀንደኘ ካድሬ ሲሆን ሰሞኑን ሕዝባዊ ለመምሰል የተለያዩ የወያኔን ጥፋቶች በመዘርዘር አልበዛም እንዴ አይነት ንግግር ይናገራል፡፡ እውነታው ከላይ ከጠቀስኩት ከሪፖርተር የተለየ አደለም፡፡ የሚገርመው ይሄው ቤን እያለ ራሱን የሚጠራው ግለሰብ ያንን የፈረደበት ምን ብዬ እንደምጠራው ራሱ ቃል ስለጠፋብኝ አሻንጉሊት ሲተች አፉን ሞልቶ ነው፡፡ ከራሱ ወገኖች ግን አንድም ሰው አያነሳም፡፡ ለጋመቤላ ተደጋጋሚ እልቂት ተጠያቂ የሚሆነው በመጀመሪያ የወያኔ ጦር አዛዦች ናቸው፡፡ የቆሼ አደጋንም ከአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በማያያዝ ሊተች ይፈልጋል፡፡ ልብ በሉ የአዲስ አበባው ከንቲባ ሌላ አሻንጉሊት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ አደጋውን ከወያኔ እያራቀ ለሌሎች ሲሰጥ ታዩታላችሁ፡፡ እግረ መንገዱን የወያኔ ትግሬዎን ብቃት ከእነዚህ አሻንጉሊቶች ጋር በማነጻጸር እንድናደንቅለት እየሞከረም ነበር፡፡ እሱም እንደ ሪፖርተሩ አዘጋጅ ሁሉ ለወያኔ እንዲህ ያሉ ዘገባዎችን በማቅረብ ለሕዝብ አሳቢ በመምሰል እግረ መንገዱንም ገበያ ለማተረፍ ነው፡፡ እነሱ በብቸኝነት እድሉ ተሰጥቷቸው ሌላ የሚሰማም ባለመኖሩ ሕዝብ የግድ እነሱኑ ይሰማል፡፡ ሌሎች እድሉን ቢያገኙት እኮ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለውን ጉድ የሚያቀርቡት እንዲህ ባልነበረ፡፡ ወያኔ ተፎካካሪዎቻቸውን ሁሉ እያጸዳች ለእነሱ ገበያ እድል ፈጠረችላቸው አሁንም ገበያቸውን ሌላ ተፎካካሪ እንዳይገጥመው ትንፋሹን ያሰማ ጋዜጠኛ ሁሉ ወደ እስር ቤት ታጉራለች፡፡ ሌላው የሚገርመው የነዚህ ጋዜጠኞች ድፍረት ንግግራቸው ሁሉ መንግስትን በሚወክል እስኪመስል ነው፡፡ ለነገሩ በእርግጥም የወያኔ ወኪል ናቸው፡፡ እንደነ ሚሚ ስበሐቱ ያለ ወሮ በላ ጋዜጠኛ ነኝ ማለቱ ሳያንሰው በሕዝብ ላይ መወሰድ ያለበትን እምጃ ሳይቀር ውሳኔ ሲያስተላልፉ ሰምተናል፡፡ ለመሆኑ ሌላው እንደነዚህ እድል ተሰጥቶት ቢሆን ማን ናቸው ነበሩ በሚዲያ ባለቤትነት አይደለም በተራ ሪፖርተርነት ተቀጥረው ለማገልገል ብቃቱ የሚኖራቸው; እውነታው አንድና አንድ ነው ትግሬና ወያኔ በመሆናቸው ነው፡፡ ትግሬና ወያኔ ሳይሆኑ አይታሰብም፡፡ ልብ በሉ ትግሬ መሆን ብቻውን በቂ አደለም፣ ወያኔም መሆን ብቻውን በቂ አደለም፡፡ ብዙ ትግሬ ወያኔ ያልሆነ አለ፡፡ ብዙ ትግሬ ያልሆነመ ወያኔ አለ፡፡ ዛሬ የአገሪቱ ሐብትም በሉት ወሳኝ ቦታዎች የተያዙት ትግሬና ወያኔ በሆኑት ነው፡፡ ሌላው እስር ቤት ነው፡፡

የኦሮሞ ሕዝብ ጠላቶቹና የወያኔ ትብብር

ሰሞኑን ከምናያቸው አስቂኝ ድራማዎች መካከል ራሱን የኦሮሞ ሕዝብ ትግል አክቲቪስት ነኝ እያለ የሚጠራው የኦሮሞን ሕዝብ እያስጨረሰ ያለው በጀዋር ሙሐመድ የሚመራው የወሮበሎች ቡድን እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይህ ቡድን አሁን ሕዝብ እየነቃበት እንደሆነ ተረድቶታል፡፡ ከወያኔም ጋር ያለው ግንኙነቱ የአደባባይ ሚስጢር እየሆነ መጥቷል፡፡ በዛው ልክ የማይወጣቸውን ርቀቶች እየሄደ ጭራሽ ሲፍጨረጨር መቀመቅ ራሱን እየከተተ ነው፡፡ ምስጋና ምርጥ ኦሮሞ የኢትዮጵያ ልጆች፡፡ ስም አልጠቅስም ግን ይህን ቡድን በብቸኝነት ተጋፍጠውት አዘቅት እያወረዱት የኦሮሞንም ሕዝብ ከብዙ ዘመን በኋላ አይኑን እንዲገልጥና ከእነማን ጋር እየታገለ እንደሆነ እያሳዩት ነው፡፡ ሰሞኑን የዚሁ ቡድን ሕዋስ የሆነ ከአንድ ለወያኔ ከሚያገለግል ኤርትራዊ ጋር ቃለ ምልልስ በሚል ለሕዝብ እያሰራጨው ያለውን ሒደት ለተመለከተ ብዙ ከዚህ በፊት ግራ የተጋባባቸውን ነገሮች ሁሉ ያውቃል፡፡ አቅራቢው ራሱን አምቦ ብሎ የሚጠራ የጀዋር ቡድን አባል ነው፡፡ ጠያቂው አመቦ ታዲያ እንደጠያቂ ብቻ ሳይሆን ተጠያቂው እንዲመልስለት በሚፈልገው መልኩ ግማሽ ያህል እራሱ ለሚያቀርበው ጥያቄ መልሱን  እየሰጠ ነበር ተጠያቂው እንዲያሟላበት የሚጋብዘው፡፡ ተጠያቂው ኤርትራዊ ደግሞ በቀጥታ ከወያኔ ተጸፎ የተሰጠውን ነገር የሚያነብ ነበር የሚመስለው፡፡  ስለዚህ ሌሎች ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆች አሳምረው ተንትነውታል፡፡ እኔ ይብቃኝ፡፡ የሚገርመው ግን እስከዛሬ ለእኔም ያለገባኝን የእነ ግንቦት7 እንቅስቃሴ ለወያኔ ስጋት እንደሆነባት እንዳስብ አደረጉኝ፡፡ ሌላው ቀርቶ እኛ እንድናውቀው የተደረገው ኦነግ ፍጹም ትክክለኛው ለኦሮሞ ሕዝብ የሚታገለው እንዳልሆነ እንድረዳ ሆኛለሁ፡፡ አተርፍ ባይ አጉዳይ ይሉታል፡፡ ኢሳትንም ያጥላላ መስሎት ትልቅ ፕሮፓጋንዳ ሰራለት፡፡  እውነት ነው ብዙዎቻችን በብዙ ውዥንብር እየተሸወድን እንደሆነ ገባኝ፡፡ ግንቦት 7፣ ኦነግ(ትክክለኞቹ)፣ ሌሎችም ሥራ እየሰሩ መሆኑን በጠላቶቻቸው ነው የተነገረን፡፡ ግን ምን እየሰሩ ይሆን፡፡ ይሄን ያህል ለወያኔ ራስ ምታት እንደሆኑበት አልገባኝም፡፡ ከአሁን በኋላ ብዙ ደጋፊ የምታገኙ መሰለኝ ግን ውጤታችሁ ቶሎ ካልሆነ በሌላ በተሰላ ፕሮፓጋንዳ ደጋፊዎቻችሁን መልሳችሁ እንደምታጡት አመኑ፡፡ ሕዝብ ዛሬን ነው እየጠበቀ ያለው፡፡ እጅች የከፋ ችግር ውስጥ ነው ያለው፡፡ እግረ መንገድ ኢሳትም ደጋፊ ያተረፈ መሰለኝ፡፡ ቢያንስ እኔ ኢሳት ከማይጥሙት አንዱ ነበርኩ፡፡ አሁንም ግን ችግር የለበትም ማለቴ አደለም፡፡ የሕዝብንና የአገርን ጉዳይ ያለምንም መሸማቀቅ ሊያስተጋባ ይጠበቅበታል፡፡ እስካሁነ በተለይ የኦሮሞን ሕዝብ ጉዳይ ኢሳት ብዙም አያወራም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ጉዳይ የእስላማዊ አክራሪነትን በሚያራምዱ የወያኔ ሚስጢራዊ ካድሬዎች የኦሮሞን ሕዝብ በሚያፈጁና በሥሙ በሚነግዱ ጀዋራዊያን ሥር ወድቆ ነበር፡፡ ከአሁን በኋላ ኢሳት ወሳኝ ኦሮምኛ ተናጋሪ ለኦሮሞ ሕዝብ ከልብ በሚቆረቆሩ ጋዜጠኞች ለኦሮሞ ሕዝብም ወሳኝ አንደበት ሊሆን ይገባል፡፡ በቅንነትና ፍጹም የእኔነትን በተላበሰ፡፡ ለሌላውም እንደዛው፡፡ ያኔ የሕዝብ ድምጽነቱን ያረጋግጣል፡፡ እስከዛሬ እኔን ራሱ ቅር ያሰኙ ብዙ ስንፍናዎችን ሰርቷል፡፡ አንዳርጋቸው ሲታሰር ብዙ ያሉት ኢሳትና ደጋፊዎቹ ለሕዝብ ሲል እድሜ ልኩን ብዙ መከራን የተቀበለውን መረራ በወሮበሎቹ ሊያውም ከሠላማዊ ከሆነ ውጭ አንዴም የኃይል ትግልን ያለደገፈ ሲታሰር ከዜና ማሟሻነት ያለፈ ጉዳያችሁ አልነበረም፡፡ የመረራ ጉዳይ ግን ከየትኛውም ግለሰብ መታሰር በላይ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ አለምን የሚያንቀሳቅስ ክስተት በተፈጠረበት ነበር፡፡ ለሕዝብ ሲል በመታሰሩም የእሱ መታሰር ለሕዝብዊ ትግሉ ትልቅ ጉልበት የሚሆንበትን ዲያስፖራውን በማስተባበር ትልቅ ክስተት መፍጠር በተቻለ ነበር፡፡ ዓለም አቀፋዊውም ማሕበረሰብ ልዩ ትኩረት የሚሰጥበትን እድል ማስገኘት በተቻልም፡፡ ይህ እናንትን አልታያችሁም

መረራና ቡድኑ፡

እኔ የኦሮሞ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ነጻነት ወሳኝ ነው ብዬ ስለማምን ሆሌም ዋና አጀንዳዬ ነው፡፡ የኦሮሞ አዲሱ ትውልድ ግን ፍጹም የታወረበትን ሥነ ልቦና በ25 ዓመት ስለወረሰ ዛሬ ላይ ጥቂቶች ቢነቁም ብዙዎች አሁንም እዛው ናቸው፡፡ ይህ ትውልድ የተደረገበት መሠረታዊ አዚም ኩራቱና ወኔው የነበረውን የአባቶቹን ታሪክ ከሕሊናው አምክኖ ጭራሽ የጠላት ታሪክ አድርጎ እንዲያየው ነው፡፡ ለኦሮሞ የዛሬው ትውልድ እየተዋጋ ያለው በማንም ኃይል የማይሸነፈውን ከ100 ዓመት በፊት ጠላትን ሁሉ በፊታቸው የሚጥሉትን ጀግኖች አያቶቹን ነው፡፡ ይህን ወደልቦናው ተመልሶ ማሰብ እስካልቻለ ድረስ ነጻነት የለውም ለሌሎችም ነጻነት ማግኘት እንቅፋት ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ዛሬ የኦሮሞ ትልቁ ሕዝብ አንድ ወረዳ የሆነችው የኮንሶን ያሕል ወያኔን የሚያሰጋ ወኔና አቅም አጥቶ ባዝኗል፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ትክክለኛ የሆኑትን መሪዎቹን ትቶ ዛሬ ለባርነት የዳረጉትን የጠላቶችን ድምጽ እየሰማ ስነልቦናው ፍጹም ስለተሰለበ ነው፡፡ ፕ/ሮ መረራ ጉዲና በትምህረት ደረጃም ሆነ የሕዝብን ትክክለኛ የነጻነት መንገድ ለመንደፍ ዛሬ እንደ አሸን የሆኑትን የኦሮሞ ነጻነት ትግል ባለቤቶች ነን ከሚሉ መሪዎች ሁሉ የተሻለ ብቃት ነበረው፡፡ በትዕግስትም አስከዛሬ ትክክለኛውን መንገድ ከማሳየት አልቦዘነም፡፡ ለዚህ የኦሮሞ ልጅ ግን ከኦሮሞ ሕዝብ ነኝ ከሚለው አዲሱ ትውልድ የተሰጠው ምላሽ ወያኔና አጋሮቿ የሚያወሩለትን የነፍጠና አቀንቃኝ የሚል ነበር፡፡ ከመረራ ይልቅ የኦሮሞ ሕዝብ ነቀርሳ የሆኑት እነ ተስፋዬ ገብረአብ ለብዙ የዛሬው ትውልያ ኦሮሞዎች ክብራቸው ናቸው፡፡ ሌሎች እጅግ ወራዳና ጸያፍ የሆኑ ተራ ምናምነቴዎች ኦሮሞ ነን ስላሉት ብቻ በጸያፍ ስድብ ሕዝብን የሚሳደቡትን ሁሉ የእኔ ብሎ እየሰደቡት ዘመረላቸው፡፡ አሁን ያለውን የኦሮሞ ትውልድ ስነ ልቦናውን ወያኔና አጋሮቹ ራሳቸው የሰሩት እንደሆነ ስለሚያውቁት እንደፈለጋቸው ያሾሩታል፡፡ ዛሬም ብዙው የእውነተኛ ታጋዮቹን ለማየት አይኑ አልተገለጠለትም፡፡ መረራን በኦሮሞ የዛሬው ትውልድ ዘንድ ከወያኔዎቹ ተስፋዬና ሌሎች ብዙ ምናምንቴዎች  ሳይቀር  ያሳነሰው ከአማራ ሕዝብ ነፍጠኛ እንዳለ ከኦሮሞም ሕዝብ ነበር፡፡ ሥርዓት እንጂ ማንም ሕዝብ ሌላውን ሕዝብ አልበደለም የሚለው ፍልስፍና ነበር፡፡ በእርግጥም ፍልስፍናም ብቻ ሳይሆን መረራ ጥርት ያለውን የሕዝቦችን የቆየ ታሪክ ስለሚያውቅ ነበር፡፡ መረራን በመቀላቀል የኦሮሞን ሕዝብ ከልብ ሊታገሉለት አብረውት የቆሙት እነ በቀለ ገርባም ይሄንኑ ስለሚያምኑና ትግላችን የሕዝብ ጠላት ከሆነው ከወያኔ እንጂ ከሌላ አደለም፡፡ በታሪክ እንደሕዝብ የትኛውም ሕዝብ ሌላውን አልበደለም፡፡ ይልቁንም የኦሮሞ ሕዝብ ልጆች በተለይ ዛሬ በብዙ የኦሮሞ ዘንድ እንደ ጠላት ታሪክ በሚታየው በሚኒሊክ ሥርዓት በመሪነት ሥልጣኑን የተቆናጠጡትና ሥርዓቱን በዋናነት የመሩት የአሮሞ ሕዝብ ልጆች ናቸው ብለው ከሚያምኑት ናቸው፡፡  ይህን የመሠለ የእውነት መሠረት ላይ ስለቆሙም ነበር በኦሮሞ ሕዝብ ያላገኙትን ድምጽ ጎንደሬዎቹ የበቀለን ምስል ከፍ አድርገው በመዲናቸው ሰማይ ላይ አርማቸው አድርገው የወጡት፡፡ ብዙው የኦሮሞው የዛሬው ትውልድ ግን እነ በቀለ ትዝም አይሉትም፡፡ ዛሬም በእነ ጀዋር አዚማዊ ስብከት ውስጥ ሆነው የጀዋር ዜና መሥሪያ ሆነው ይኖራሉ፡፡ ወያኔም ትልቁ ጥንቃቄዋ ሕዝብ እነ መረራንና በቀለን እንዳይከተል ነው፡፡ እነ መረራን የኦሮሞ ሕዝብ ተከተለ ማለት ወያኔ እንደሚያበቃላት አሳምራ ታውቀዋለች፡፡ እነ መረራ በኦሮሞ ሕዝብ ብቻም እንደማይገደቡ ታውቀዋለች፡፡ የእነመረራ ስኬታማነት ለ26ዓመት እንዳይገናኙና እርስ በእርስ እንደጠላት እንዲተያዩ ያደረገቻቸው ሕዝቦች በተለይ የአማራውና የአሮሞው ሕዝብ አንድ እንደሚሆን አሳምራ ታውቀዋለች፡፡ ወያኔን እጅግ የሚያስፈራት የሚኒሊክ ታሪክ በኦሮሞ ሕዝብ ሕሊና ተመልሶ እንደሚገባ ታውቃለች፡፡ ብቸኛ አማራጭ አድርጋ የነበራት እነዚህን መሪዎች ማሰር ነበር፡፡ እነዚህ መሪዎች እንደሌላው በሆድ ጉዳይ አይታለሉም፡፡ እንደ ሚከተለው እንደሙዚቀ ሰምተዋቸው የማይጠገብ ፍልስፍና ያላቸው ናቸውና ለወያኔ እጅሄ  ያስፈሯታል፡፡ ስሙት በቀለ ገርባ ማለት ይሄ ነው፡፡

አመሰግናለሁ!

ሰርፀ ደስታ

እግዚአብሔር ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጠን! አገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቅ! አሜን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.