የርዳታ ድርጅቶች የ90 ቀን ንቅናቄ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አስታወቁ

0,,18892932_303,00

(ሳተናው) የሰብአዊነት ድጋፍ የእርዳታ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የድርቅ ሁኔታ የአለም ማህበረሰብ ተገንዝቦ የተጠየቀውን የእርዳታ ድጋፍ እንዲያደርግ ግንዛቤ የማስጨበጫ ንቅናቄ ለ90 ቀናት ለማድረግ መወናቸውን ዛሬ አስታወቁ፡፡

‹‹ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛው በመሆን በተመዘገበው የአየር ጸባይ ለውጥ በመመታቷ 10 ሚልዩን የሚጠጉ ዜጎቿ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ሆነዋል፣ሰብሎች ደርቀው ሲወድቁ እንስሳት በመሞት ላይ ይገኛሉ በአገሪቱ የንጹህ የመጠጥ ውሃ እጥረት በመፈጠሩ በከፍተኛ ደረጃ የተላላፊ በሽታዎች ስጋት አንዣብቧል፡፡ይህንን ችግር ለመጋፈጥ ተጨማሪ እርዳታ አገሪቱ ማግኘት የምትችልበትን መንገድ ለማመቻቸት ግንዛቤ የማስጨበጫ ንቅናቄ ለመፍጠር ተዘጋጅተናል››በማለት በኢትዮጵያ  የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊነት ድጋፍ አሰባሳቢ  የሆኑት አሁና ኢዚኮንዋ ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊነት ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ በመግለጫው ለኢትዮጵያ በያዝነው ዓመት ከቀረበ 1.4 ቢልዩን ዶላር የእርዳታ ጥያቄ ውስጥ 758 ሚልዮን ዶላሩ ከአገሪቱ መንግስት መገኘቱን በማውሳት ቀሪውን ክፍተት ለመሙላት ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይጠበቃል ብሏል፡፡በመጪዎቹ አራት ወራት ውስጥ የእርዳታ ገንዘቡን ለማግኘትም ንቅናቄው መጀመሩ ወሳኝ መሆኑን አስምሮበታል፡፡

የብሄራዊ የአደጋና መከላከል ቢሮ ኮሚሽነር የሆኑት ምትኩ ካሳ በበኩላቸው ‹‹አገሪቱ ባጋጠማት የድርቅ ቀውስ ኢትዮጵያን ለመርዳት የውጪ መንግስታትና የእርዳታ ድርጅቶች ባደረዱት ሁሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡ ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮም የተወሰኑ መንግስታት የቀውሱን አንድ ወገን ለመደገፍ አስተዋእጾ በማድረጋቸው በአልሚ ምግብ እጦት የተጎዱ ህጻናትን ማገዝ የተቻለ ቢሆንም ችግሩ ቀድሞ ከታሰበው በሶስት እጥፍ በመጨመሩ የተረጂዎቹ ቁጥር ንሯል››ብለዋል፡፡

ምንጭ አዲስ ስታንዳርድ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.