73.2 F
Washington DC
June 14, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ፋሲል ከነማን መደገፍ የጋራ ጀግናን የማሳደግ፣ የማሻገር ተግባራዊ ምላሽ መሆኑን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
ፋሲል ከነማን መደገፍ የጋራ ጀግናን የማሳደግ፣ የማሻገር ተግባራዊ ምላሽ መሆኑን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር: ግንቦት 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) “ስፖርት ለኢትዮጵያ ሕብረት” የፋሲል ከነማ ገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ክለቡን በመደገፍ ሁሉም አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ቀኑ ፋሲል ከነማ ድሉን የሚያከብርበት እና የአፍሪካ ቀን መሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው ነው አቶ ደመቀ የጠቀሱት፡፡
ከየማዕዘኑ እና ከየዘርፉ የሚወጡትን ጀግኖች በታሪክ ማጣቀስ እንደነሱ መሥራት እንደሚጎድል አንስተዋል፡፡ በተለያየ ዘርፍ በርካታ የጋራ ጀግኖች አሉ ፤ ታሪክ በተዛባ
መልኩ ለትውልዱ መተላለፉ ኢትዮጵያ በሁሉም ማዕዘናት ያሏትን በርካታ ጀግኖች በመቀበል ረገድ ችግር መፍጠሩን ጠቅሰዋል፡፡ “ጀግኖቻችንን ማወቅ፣ የጋራ ሃብት አድርጎ
በእነርሱ መኩራት፣ ማጣቀስ እነሱን መከተል፣ የተሻለ ሆኖ መገኘት ነው ይኼ ትውልድ የሚገባው” ብለዋል አቶ ደመቀ፡፡
በስፖርቱ ዘርፍ በድል አድራጊነት አጼዎቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ጀግኖች መሆናቸውን ነው አቶ ደመቀ የገለጹት፡፡ “ኮርተንባችኋል፤ እንኳን ደስ አላችሁ” ነው ያሉት፡፡
በተለያየ ዘርፍ እንደ አርዓያነት የሚነሱ ሀገራዊ ጀግኖች እንዳሉ እና በስፖርቱ ዘርፍ አብነቶችን የጠቀሱት አቶ ደመቀ የጋራ ጀግኖችን በማክበር፣ በማወቅ እና በመኩራት
ሀገርን ወደፊት ማራመድ እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በዛሬው ቴሌቶን ፋሲል ከነማን ወደ ተሻለ አቅም እንዲመጣ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የጋራ ጀግናን የመደገፍ እና የማሳደግ፣ የማሻገር ተግባራዊ ምላሽ ነው ብለዋል፡፡
“ፋሲል ከክለብም በላይ ነው” ያሉት አቶ ደመቀ ክለቡ ስኬታማ ጉዞውን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበት ተናግረዋል፡፡ በዚህ ዘመን ይህ ትውልድ መሙላት፣ መሻገር
ካለበት የሚያጋምዱ የጋራ ሀብቶችን ይዞ መጠበቅና ለጠንካራ ሀገር መሥራት፣ መተባበር እና መጎልበት አለበት ብለዋል፡፡ “ከምንም በላይ የሚያምርብን ስናብር ነው” ነው
ያሉት አቶ ደመቀ፡፡
ፋሲል በዚህ መልኩ ተምሳሌትነት እንዳለውም አንስተዋል፡፡ የክለቡ ተጫዋቾች ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች ተሰባስበው ለድል መብቃታቸውን በመጥቀስ፡፡
በስፖርት ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘርፍ ማበር እና በጋራ መቆም የሚያመጣውን አዎንታዊ ውጤት ገልጸዋል፡፡
በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫና ያነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በፋይናንስ፣ በጉዞ፣ እና መሰል
ቁሳዊ ክልከላዎች ቢኖሩም የኢትዮጵያን ክብር ግን ማንም ሊነካው እንደማይችል አስገንዝበዋል፡፡
ከመቼውም ጊዜ በላይ መከባበር፣ መነጋገር፣ መደማመጥ፣ በሁሉም ማዕዘን ለዜጋ ክብር መስጠት እና ዜጎች የማይገደሉበት፣ የማይፈናቀሉበትን እና አንገት መድፋት
የማይደመጥበት ሀገር መፍጠር እንደሚገባ በአፅንኦት አንስተዋል፡፡ ይህ ከሆነ ሁሉንም እንቅፋቶች መሻገር እንደሚቻል እና መበልጸግ እንደሚቻል አስታውቀዋል፡፡
ዘጋቢ:- የማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m


Previous article“ለስፖርቱ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ለሰላም፣ ለአብሮነትና ለወንድማማችነት ማጠናከሪያ ገመድ ሆኖ እንዲያገለግል መሥራት ይገባል” የጎንደር ከተማ ከንቲባ


Source link

Related posts

ሕጋዊ እውቅና ተሰጥቷቸው የመኖሪያ ቤት ቦታ ሲጠባበቁ ለቆዩ ማኅበራት የቤት መሥሪያ ቦታ ለመስጠት ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

admin

የአዉሮፖ ህብረት  ምርጫዉን  የሚታዘቡ ኤክስፐርቶችን  የመላክ ፍላጎት እንዳለዉ አሳውቋል- አምባሳደር ዲና

admin

የጎሳን እድል በጎሳ መወሰን – ሰመረ አለሙ

admin