82.62 F
Washington DC
June 22, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ፋሲል በአሸናፊነቱ እንዲቀጥል የአማራ ክልል ሰፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዘዘው ጫኔ አሳሰቡ።

ፋሲል በአሸናፊነቱ እንዲቀጥል የአማራ ክልል ሰፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዘዘው ጫኔ አሳሰቡ።

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፋሲል ከነማ እግርኳስ ቡድን የገቢ ማስገኛ ዝግጂት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

በዝግጂቱ ላይ የተገኙት የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ስፖርት፣ ሰላምና አንድነትን በማምጣት ትልቅ ሚና አለው፣ ዛሬም ያዬነው እርሱን ነው ብለዋል። በስፖርቱ ዘርፍ ብዙ የተሳካልን አልነበርንም አሁን ፋሲል ከነማ ፈር ቀዳጅ ሆኗል ነው ያሉት። አረያነቱ ሌሎችም ፋሲል ከነማን እንዲከተሉ እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል።

እግር ኳስ ክለቦች እንዲጠናከሩ ሁለንተናዊ ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ብለዋል።

የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዘዘው ጫኔ ታሪካዊቷ ጎንደር የገነባቸው ቡድን የአሸናፊነት ድል እንድንጎናጸፍ ስላደረግን እንኳ ደስ አለን ብለዋል። ፋሲል በታሪካዊቷ ከተማ የተመሠረተ ታሪካዊ ቡድን ነው፤ ታላቋን ሀገር ወክሎ በአፍሪካ የሚሳተፍ ነውም ብለዋል።

ቡድኑ ከአንድ መንደር የተሰባሰበ ሳይሆን ከመላው ኢትዮጵያ የተሰባሰበ ነው፣ ተጫዎቾችን ዓላማ እንጂ ብሔርና መንደር አላገናኛቸውም፤ ቡድኑ ሕዝብን አንድ ያደረገ ነውም ብለዋል።

ፋሲል ከነማ የአንድነት፣ የፍቅርና የሰላም አምባሳደር እንደሆነም ተናግረዋል። ፋሲል የጎንደርን ብቻ ሳይሆን አማራንና ኢትዮጵያን አሸናፊ አድርጓልም ብለዋል። ሁሉም ውጤታማ ለመሆን የአንድነትንና የአሸናፊነትን ትምህርት ከፋሲል መውሰድ አለበትም ነው ያሉት።

“የጎንደር ወጣቶች ለከፈላችሁት ዋጋ አግኝታችኋልና እንኳን ደስ ያላችሁ፤ ፋሲልን ከጎኑ ያልተለያችሁ ሁሉ እጅግ ኮርተንባችኋልም” ነው ያሉት።

ዓመቱ አማራ ክልል በስፖርቱ ውጤታማ የነበረበት እንደሆነም ተናግረዋል። ፋሲል አስፈሪውን ስም ይዞ እንደ ንጉሡ በአስፈሪነቱና በአሸናፊነቱ መቀጠል አለበትም ብለዋል። ባለሀብቶችም የሚቻላቸውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Source link

Related posts

“ኦነግ ሼኔ ካቅማችን በላይ ነው እና አካባቢውን ለቅቃችሁ ውጡ ተብለናል” ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርቴ ጃርደጋ ወረዳ ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ወሎ ዞን የመጡ አማራዎች

admin

“ልጄ መቼ ይሆን ወደ ነበርንበት ወግ ማዕረግ የምንመለሰው?” ከመተከል ዞን የተፈናቀሉ አዛውንት

admin

“ከፍያለው የኢትዮጵያውያኑ የዐዕምሮ ልዕልና ኢ-ሰባዊ ድርጊት ለመፈጸም እንዴት ቻለ”

admin