55.85 F
Washington DC
March 3, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ጊዜ ቆጣቢ እና ምርትን ከብክነት ሊታደጉ የሚችሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን እያስተዋወቀ መሆኑን “ሳሳካዋ አፍሪካ አሶሴሽን” የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት አስታወቀ፡፡ጊዜ ቆጣቢ እና ምርትን ከብክነት ሊታደጉ የሚችሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን እያስተዋወቀ መሆኑን “ሳሳካዋ አፍሪካ አሶሴሽን” የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) እንደ ድርጅቱ መረጃ በኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነት በዓለም ላይ ዝቅተኛ ከሆኑት ሀገራት መካከል ሲሆን የግብርና ቴክኖሎጂ አለመስፋፋት መሠረታዊ ምክንያቱ ነው፡፡ አብዛኛው አርሶ አደር ዘርፉን ለማዘመን የቴክኖሎጂ እውቀት የሌለው መሆኑ፣ በገንዘብ እጥረት እና የገበያ ተደራሽነት አለመኖር ምርታማነታቸውን እና ገቢያቸው እንዳያድግ ማነቆ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ግብርናውን በማዘመን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ምርትና ምርታማነቱን ማሳደግ የችግሩ ሁነኛ መፍትሄ ነውም ተብሏል፡፡

ሳሳካዋ አፍሪካ አሶሴሽን የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጊዜ ቆጣቢ እና ምርትን ከብክነት ሊታደግ የሚችል ዘመናዊ የእህል መውቂያ መሣሪያ እና የእህል ማከማቻ ጎተራ ለአርሶ አደሩ እያስተዋወቀ ነው፡፡ ደርጅቱ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ከግብርና ሚኒስቴር እና አጋር አካላት ጋር ሲሠራ እንደቆየ ተጠቅሷል፡፡

ድርጅቱ በቡሬ ዙሪያ ወረዳ አለፋ ቀበሌ ጊዜ ቆጣቢ፣ ምርትን ከብክነት ሊታደግ የሚችል ዘመናዊ የእህል መውቂያ መሣሪያ እና የእህል ማከማቻ ጎተራ ተጠቃሚ አርሶ አደሮችን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በተመለከተ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል፡፡

በጉብኝቱ አስተያየታቸውን የሰጡ አርሶ አደሮች መካከል ወይዘሮ እድሜዓለም ዋነኛው እና አቶ አልማው ደሥታ ቀደም ሲል እህሉ የሚወቃው በባሕላዊ መንገድ ስለሆነ ከድካም ባለፈ የሚወቃው አፈር ላይ በመሆኑ የምርት ብክነት እና ጥራት መጓደል ይከሰት ነበር፡፡ በተጨማሪም ሥራው ጊዜ ቆጣቢ ባለመሆኑ እህሉን ሳይወቃ ወቅቱን ላልጠበቀ ዝናብ እና በክምችት ወቅትም ለብክነት ይጋለጥ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና ዳይሬክተር ፈንታሁን መንግሥቴ (ዶክተር) እንደተናገሩት ይህንን ችግር ለመፍታትና አርሶአደሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ ምርት እና ምርታማነትን እንዲያሳድግ ሳሳካዋ አፍሪካ አሶሴሽን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ በአማራ ክልል ውስጥ ባሉ 96 ቀበሌዎች ከ43 ሽህ በላይ አርሶ አደሮችን የድኅረ ምርት ስብሰባ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል ተብሏል፡፡

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ- ከቡሬ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Previous article‹‹እነሆ ቤተመቅደሱን ይጠብቁ ዘንድ ነብሮች ታዘዙ››
Next article“የክትባት አቅርቦት እና የተጎጅዎች ቁጥር አለመመጣጠን ውሻን የሚያሳብድ በሽታ ለመከላከል ፈታኝ አድርጎታል” የአማራ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

Source link

Related posts

“ኢትዮጵያ እና ሱዳን ብሔራዊ ጥቅሞቻቸውን አስከብረው በትብብር ከመሄድ የተሻለ አማራጭ የላቸውም” ሱዳናዊ ፕሮፌሰር ሙሃመድ ሳላህ

admin

የአማርኛ ቋንቋ እና አክራሪ ብሄርተኞች

admin

የተፈራው አልቀረም ሙሉ ነጋ(ዶ/ር)  ዳግማዊ ስብሃት ነጋን ሆነው መጥተዋል!?! (ታምሩ ገዳ)

admin