79.57 F
Washington DC
June 14, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ዩኒቨርሲቲው በዋሸራ አውራ በጎች ዝርያ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዋሸራ አውራ በጎች ዝርያ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 08/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት በዋናነት ሦስት ማኅበራዊ ኃላፊነቶችን፣ መማር
ማስተማር፣ ምርምር እና የማኅበረሰብ አግልግሎቶችን ያከናውናሉ፡፡ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲም እንደ ሌሎች ነባር ዩኒቨርሰቲዎች
ሦስቱንም ተግባራት በተሳካ መልኩ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው በማኅበረሰብ አግልግሎት ዘርፍ የዋሸራ በግ ዝርያን ለአርሶ አደሮች ለማስተዋወቅ ምርምሮችን እያደረገ ይገኛል፡፡
ዝርያው በመቀነስ ላይ የሚገኘውን የዋሸራ (ዳንግሌ) በግ ዝርያን ጠብቆ ለማቆየት በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በፋግታ ለኮማ
ወረዳ በብዛት እናት በግ በሚገኝባቸው እና የተሻለ ግጦሽ ባለባቸው ሦስት ቀበሌዎች 41 አውራ በጎችን ገዝቶ አሰራጭቷል።
አሚኮ ያነጋገራቸው የፋግታ ለኮማ ወረዳ ነዋሪዎችም ዩኒቨርሲቲው ያቀረበላቸው የዋሸራ አውራ በጎች ዝርያ ኢኮኖሚያዊ
ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድግ ተናግረዋል፡፡
አርሶ አደር ትዛዙ የኔው እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው በመልክ፣ በቁመትና በውፍረት የተሻለ ዝርያ ያላቸውን አውራ በጎች በመግዛት
ለአርሶ አደሮች ማስረከቡን ተናግረዋል። ይህም አንድ አውራ የዋሸራ በግ 30 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል። አርሶ አደሮቹ
በተለምዶ የተሻለ የሚሉትን የበግ ዝርያ ለማዳቀል አውራ በግ ለማገኘት ጥረት ያደርጉ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በምርምር የታገዘውን የዋሸራ በግ ዝርያ ማቅረቡ በግ አረባባቸውን ዘመናዊ ከማድረጉም ባሻገር ለገበያ በማቅረብ
ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚያግዛቸው አስረድተዋል። የሥራው ውጤትም ከስድስት ወራት በኋላ እንደሚታወቅ ገልጸዋል፡፡
ሌላው አርሶ አደር ዓለምአገኝ መላኩ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከአርሶ አደሮች ጎን በመኾን የበጎችን ዝርያ ለማሻሻል
የሚያደርገው ጥረት የሚመሰገን ነው ብለዋል፡፡ በተለምዶ የሚያረቡአቸው የበግ ዝርያዎች ትናንሽ እና የሥጋ ምርታቸው አነስተኛ
በመሆናቸው ጥሩ የሚባል የገበያ ዋጋ እንደሌላቸውም ገልጸዋል፡፡
የቀረቡላቸውን የዋሸራ አውራ በጎች በመንከባከብ ለጥሩ ውጤት ለመድረስ እየሠሩ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ዋሸራ ማኅበረሰብ አቀፍ የበጎች ዝርያ ማሻሻል የፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ መልካም ፀጋ እንደነገሩን
በአካባቢው የዋሸራ በግ ዝርያ መመናመን መኖሩን በማጥናት ችግሩን ለመቅረፍ እየተሠራ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ከፋግታ ለኮማ ወረዳ አራት ቀበሌዎች በመለየት በሦስቱ ቀበሌዎች እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
በእነዚህ ቀበሌዎች በዋሸራ አውራ በግ የሚዳቀሉ 1 ሺህ 978 እናት በጎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም
አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡
የዋሸራ በግ በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን የተሻለ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በጥናት ተረጋግጧል ብለዋል አቶ
መልካም፡፡ እነዚህ የበግ ዝርያዎች መንታ፣ ጥሩ መልክና ቁመና ያሏቸውን በጎች በመውለድ የሚታወቁ መሆናቸዉን ነው የነገሩን።
የሚወለዱ በጎችም በሦስት ወራት ለሥጋ የሚደርሱና ለጥቅም መዋል የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በፋግታ ለኮማ ወረዳ የዋሸራ በጎችን በብዛት ለማዳረስ እቅድ ይዞ በመሥራት ላይ የሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክት አምስት
ዓመታት የሚቆይና በ44 ማኅበራት የተደራጀ መሆኑን አስተባባሪው አስታውቀዋል።
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን (ዶክተር) አካባቢው
በግብርናው ዘርፍ ጎልቶ የሚታወቅ በመሆኑ ዘርፉን ለማዘመንና ለመደገፍ የአርሶ አደሮችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የምርምር
ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በቀጣይ የአርሶ አደሮችን የወተት ሀብት ለማሳደግ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በጥንቃቄ ይዘው ወደ ፋብሪካ ማድረስ የሚያስችሉ
የምርምር ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አስታውቀዋል።
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m


Previous articleየተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም ከ945 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የአጣዬና አካባቢው መልሶ ማቋቋም ግብረ ኀይል ገለጸ።


Source link

Related posts

“ሰው ምን ያህል መሬት ይፈልጋል?”በላይነህ አባተ

admin

21 ሺህ 695 የጋራ መኖርያ ቤቶችና ከ13 ሚሊየን በላይ ካሬ መሬት በህገወጥ መንገድ መያዛቸው መረጋገጡን ወ/ሮ አዳነች ገለፁ

admin

የእንባ ጠብታ – እኔንያየህተቀጣ

admin