68.38 F
Washington DC
June 22, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች ኢትዮጵያን የሚመስሉ፣ የምንኮራባቸውና የድል ተምሳሌት ናቸው” የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቀሰሙ ማሞ

“የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች ኢትዮጵያን የሚመስሉ፣ የምንኮራባቸውና የድል ተምሳሌት ናቸው” የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቀሰሙ ማሞ

ባሕር ዳር: ግንቦት 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ የገቢ ማሰባሰቢያ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

በገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቀሰሙ ማሞ ስፖርት በባሕሪው ብዙዎችን የሚያገናኝ ድልድይ በራስ መተማመን፣ ሰላምና ፍቅር፣ መቻቻል፣ ትዕግስት፣ በጎነት የሚታይበት መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ስፖርትም ይህንኑ ባሕሪ የተላበሰ ስለሆነ በማሸነፍና በመሸነፍ ውስጥ ሆነው ሲያሸነፉ ደስ ሲላቸው፤ ሲሸነፉ ቢከፋቸውም ተቃቅፈው ፍቅራቸውንና ወንድምነታቸውን የሚያሳዩበት “የፍቅር ቤት ነው” ብለዋል።

የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች ኢትዮጵያን የሚመስሉ፣ የምንኮራባቸውና የድል ተምሳሌት ናቸው ብለዋቸዋል።
የኢትዮጵያን ሰንደቅ ከፍ የሚያደርጉ ስሟንና ክብሯን የሚያስጠሩ በመሆናቸውም ክብር ይገባቸዋል ነው ያሉት።

ፋሲል ከነማ ስሙና ትውልዱ አማራ ክልል ጎንደር ቢሆንም ፋሲለደስ ኢትዮጵያዊ ነው፣ የኢትዮጵያ ምንጭ ነው፣ ፋሲል ከነማም የኢትዮጵያ ነው፣ ሁለቱም ኢትዮጵያዊ ናቸው ብለዋል።

ስፖርት በተግባር ኢትዮጵያን የሰላም፣ የአንድነትና የመቻቻል ተምሳሌት እንድትሆን የሚሠራበት ሜዳ ነው፤ ስፖርት ዘርን፣ ጎጠኝነት፣ ምቀኝነትን፣ ተንኮልና ፅንፈኝነትን አምርሮ ይጠላል ምክንያቱም አንዱ ያለአንዱ መኖር አይችልምና ነው ያሉት።
ልክ እንደ ስፖርት ሁሉ በአንድነትና በትብብር ከተሠራ ኢትዮጵያ ውጤታማ ትሆናለችም ብለዋል። የክለቡ ተጨዋቾች በእግር ኳስ ብቻ ማሸነፍ ሳይሆን ተፅዕኖ በመፍጠር ኢትዮጵያ የአንድነት፣ የትብብርና የመቻቻል ሀገር እንድትሆን እንዲሠሩም ጥሪ አቅርበዋል። “ስፖርቱም እኛም የምንኖረው ኢትዮጵያ ስትኖር ብቻ ነው” ብለዋል።

ፋሲል እንዲጠናከር ሁለንተናዊ ድጋፍ ያስፈልገዋል፤ ድጋፍ ያደረጋችሁም ምስጋና ይገባችኋል ነው ያሉት።

የፋሲል ከነማ ክለብ አባላት አምራችሁና ደምቃችሁ እንደትቀጥሉና የኢትዮጵያን ሕዝብ የበለጠ ለማስደሰት እንድትሠሩም ብለዋል። የአማራ ክልል ሕዝብ ከጎናቸው መሆኑንም ወይዘሮ ወርቀሰሙ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Source link

Related posts

ምዕመኑ የጥምቀት በዓልን ሲያከብር ለኮቪድ-19 ተጋላጭ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለበት – የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

admin

የኢትዮ-ኮሪያ የቱሪዝም ፎረም በበይነ መረብ ተካሄደ

admin

አቶ ደመቀ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና ተያያዝ ጉዳዮች ላይ በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛን ጋር ተወያዩ

admin