48.63 F
Washington DC
February 27, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የግብርና ምርቶችን ለሚያቀነባብሩ ፋብሪካዎች ሀገር በቀል ግብዓት እንዲያገኙ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የግብርና ምርቶችን ለሚያቀነባብሩ ፋብሪካዎች ሀገር በቀል ግብዓት እንዲያገኙ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2013 ዓ.ም (አብመድ) በአማራ ክልል የሚገኙ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ከውጪ የሚገቡትን ግብዓቶች በመተካት ሀገሪቱ የምታወጣውን የውጪ ምንዛሬ በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው። ፋብሪካዎቹ ከውጪ ሊገቡ የሚችሉትን ግብዓቶች ማስቀረት ብቻ ሳይሆን የአርሶ አደሮችን ገቢ በማሻሻልና የሀገር ምጣኔ ሀብትን በማሳደግ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ለሚደረገው የኢኮኖሚ ሽግግርም ቁልፍ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ።

ይሁን እንጂ ፋብሪካዎቹ ሀገራዊ ራዕይ አንግበው ሥራቸዉን ቢጀምሩም ከግብርናዉ የሚገኘው ምርት አጥጋቢ ባለመሆኑ ትልቅ ማነቆ እንደሆነባቸው በተደጋጋሚ አሳውቀዋል።

ሆኖም የግብርና ሚኒስቴር ጉዳዩን በችልተኝነት እንዳላለፈው በግብርና ሚኒስቴር የግብዓትና ምርት ግብይት ዘርፍ ሚንስትር ድኤታ ወይዘሮ ዓይናለም ንጉሤ በተለይ ለአብመድ አስረድተዋል። ከባለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ ከውጪ የሚገቡትን የግብርና ምርቶች በሀገር ውስጥ ለመተካት ሚኒስቴሩ አቅዶ እየሠራ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ከውጪ የሚገባን ስንዴ በማስቀረት በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የሚኒስቴሩ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትር ድኤታዋ ከዚህ ፕሮጀክት ጎን ለጎን ለዘይት ምርት ግብዓት የሚሆኑ ሰብሎችን በሁለተኛ ዙር መስኖ ለማልማት መታሰቡን ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል የምግብ ዘይት ለማምረት ወደ ሥራ ለገቡ ፋብሪካዎች ግብዓት እንዲያገኙ ለማስቻል በሀገሪቱ ቆላማ አካባቢዎችና በመስኖ በማልማት ከውጪ የሚገቡ የዘይት ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ቀነ ገደብ መያዙን ነው ወይዘሮ ዓይናለም ያብራሩት፡፡ ይህንን ከግብ ለማድረስም በዓመት በመስኖ ሦስት ጊዜ በማልማት መታቀዱንም ገልጸዋል፡፡ ግብርናዉን ለማዘመን ለሰብል፣ ለእንስሳት መኖና ለሌሎችም ልማቶች የሚውሉ ከ524 በላይ የግብርና ቁሳቁስ ከቀረጥ ነፃ በማስገባት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች እንቅስቃሴዎች መጀመራቸዉን ወይዘሮ ዓይናለም ጠቅሰዋል፡፡ ሌሎች ክልሎችም ይህን ተሞክሮ ሊወስዱ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

“ከውጪ የሚገቡትን የግብርና ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት እንተካለን በማለት ወደ ሥራዉ የገባነው በተለምዶዉ አሠራር ለመሥራት ሳይሆን ግብርናዉን ሜካናይዝድ ለማድረግ በማሰብ ነው፤ ይህንንም በተግባር መፈጸም ጀምረናል” ብለዋል ሚኒስትር ድኤታዋ፡፡ በኢንዱስትሪዉ ኢኮኖሚ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች አርሶ አደሮች የሚያመርቱት ምርት ለእነሱ እንደሆነ ተገንዝበው ከአርሶ አደሮች ጋር የጠበቀ ትስስር እንዲፈጥሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ብሩክ ተሾመ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ ተገብቷል- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

admin

ሲዋጉና ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ዋሉ

admin

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዳሳሰባቸው የከተማዋ የምክር ቤት አባላት ተናገሩ።

admin