31.01 F
Washington DC
March 2, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የገንዘብ እጥረት የባሕር ዳርን ስታዲዬም ጣሪያ እንዳይለብስ አድርጎታል፡፡

የገንዘብ እጥረት የባሕር ዳርን ስታዲዬም ጣሪያ እንዳይለብስ አድርጎታል፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) ከተጀመረ ዓመታት ያለፉት የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ሁለገብ ስታዲዬም በተባለለት ጊዜ መጠናቀቅ አልቻለም፡፡ ከሃምሳ አምስት ሺህ በላይ ሰዎችን በወንበር መያዝ እንደሚችል የሚገርለት ስታዲዬሙ መጠናቀቅ ሳይችል ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ለስታዲዬሙ በተባለለት ጊዜ አለመጠናቀቅ ደግሞ የተለያዩ ምክንያቶች ይነሳሉ፡፡

የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክተር ባንተአምላክ ሙላት ከአብመድ ባደረጉት ቆይታ የስታዲዬሙ አብዛኛው ሥራ ተጠናቋል ብለዋል፡፡ ስታዲዬሙ የቀረው ጣሪያ ማልበስና የወንበር መግጠም ብቻ ነው፡፡

ስፖርት ኮሚሽኑም ስታዲዬሙ ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ብቁ እንዲሆን መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮችን የማሟላት ሥራ እያከወነ ነው ብለዋል፡፡ ዓለምአቀፍ የሆኑ ውድደሮችን ማስተናገድ እንዲችል ለማድረግ ከክልሉ መንግሥት ጋር በመሆን ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

ኢትዮጵያ በሜዳዋ የምታደርጋቸውን ጨዋታዎች በሜዳ ችግር ምክንያት ወደ ጎረቤት ሀገራት ሄዳ እንዳታደርግ የሚያስችል ጥረት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡ በዚህም ስኬታማ በመሆን ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ሁለገብ ስታዲዬም መመረጡን ነው የተናገሩት፡፡

ዓለም አቀፍ ውድደሮች በባሕር ዳር እንዲካሄዱ በአፍሪካ እግር ኳስ የበላይ ጠባቂ ካፍ ማረጋገጫ መሰጡንም ተናግረዋል፡፡

ለስታዲዬም ግንባታ የበጀት ችግር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ጣሪያውን ለመሥራት ስታዲዬሙ እስካሁን የተሠራበትን ያክል ዋጋ እንደጠየቀ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ከአንድ ዓመት በፊት በተደረገ ጥናት 600 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው መገለጹን ጠቅሰዋል፡፡

ለስታዲዬሙ ጣሪያ ሥራ የተተመነው ገንዘብ አሁን ላይ ባለው ዋጋ ሊጨምር እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡ ብሩን አንድ ጊዜ ማግኜት እንደሚከብድም አስታውቀዋል፡፡ ንብረት እንዳይጎዳ ጣሪያው ከተገጠመ በኋላ ወንበር የመግጠም ሥራው መቀጠል እንዳበትም ተናግረዋል፡፡ ቅድሚያ ጣሪያው ይሠራ የሚል ለክልል ምክር ቤት አቅርበው መልካም ምላሽ ማግኜታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ጣሪያው ሳይሠራ ወንበር መግጠም ለንብረት ብክነትና ውድመት ስለሚዳርግ እንጂ ወንበር መግጠም የሚያስችል ገንዘብ መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡

ስታዲዬሙ ዓለማቀፋዊ ደረጃውን ጠብቆ እንዲሠራ ባለው የሥራ መርኃ ግብር ቅደም ተከተል መሰረት እንደሚከናወን ነው የተናገሩት፡፡ ክልሉ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ፈታኝ ነገሮች ቢገጥሙትም የስታዲዬሙን ቀሪ ሥራዎች ለመሥራት ለሚጠየቀው ጥያቄ መልካም ምላሽ አለውም ብለዋል፡፡

የገንዘብ ችግር ጣሪያውን እንዳይለብስ አድርጎታልም ነው የተባለው፡፡ የሥራ ኃላፊዎች መቀያዬርም ሥራውን አጓቶታል ተብሏል፡፡ በጀቱ የሚለቀቅ ከሆነ ሥራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚቻልም ተናግረዋል፡፡ ሕዝቡና ባለሀብቶች የግንባታው ተሳታፊ እንዲሆኑ ይሠራልም ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ስታዲዬሙ ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን እንዲያደርግ ቢፈቀድለትም የምሽት ጨዋታዎችን ማድረግ አይችልም፡፡ መብራት ወይም ፓውዛ የመትከል ሥራም ከጣሪያው ጋር እንደሚያያዝም ተነስቷል፡፡

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ሁለገብ ስታዲዬም 4 ዘመናዊ የመልበሻ ክፍሎች አሉት፡፡ ሁሉም ክፍሎች ደረጃዎችን የጠበቁና ለጨዋታ ዝግጁ ናቸው፡፡ የአሰልጣኞች፣ የዳኞችና የሚዲያ አካላት ዘመናዊ ክፍሎችም አሉት፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ምክር ቤቱ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት የ160 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረገ

admin

ጠቅላላ ጉባኤ ያላደረጉ ፓርቲዎች 6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በተጠናቀቀ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲያካሂዱ ተፈቀደ

admin

ሱዳን በሶስተኛ ወገን የተደገሰላትን የጦርነት ወጥመድ  በመተው ችግሩን በድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆን አለባት-ጀነራል ብርሃኑ ጁላ

admin