46.09 F
Washington DC
February 25, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የመፀዳጃ መገልገያ ገንዳዎችን ድጋፍ አደረገ።

የጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የመፀዳጃ መገልገያ ገንዳዎችን ድጋፍ አደረገ።

ባሕር ዳር ፡ የካቲት 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጃፓን መንግሥት የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 1 ሚሊዮን ዶላር ወጭ የተደረገባቸው የመፀዳጃ መገልገያ ገንዳዎችን በዩኒሴፍ በኩል ለኢትዮጵያ አስረክቧል፡፡

በጃፓን መንግስት በኩል የተበረከቱት 165 ሺህ የመጸዳጃ ገንዳዎች (ሶቶ ፓን) ናቸው፡፡ ገንዳዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ ተወካይ በሆኑት ወይዘሮ ኢየሩሳሌም ታየ በኩል ከከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በመሆን ለተጠቃሚዎች ይደርሳሉ ተብሏል።

በርክክቡ ወቅት በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ እና የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ አዴል ኮድር ተገኝተዋል፡፡

በርክክቡ ላይ የተገኙት የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጌታቸው በዳኔ ግብዓቶቹ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የከተማ ነዋሪዎች ይሰራጫሉ ብለዋል፡፡ ድጋፉ በመንግሥት በኩል የተጀመረውን የንፅህና አጠባበቅ እና የጽዱ አካባቢ ሥራ ዘመቻን ለማገዝ ጠቀሜታ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡

በተለይ በኮሮናወረርሽኝ ወቅት በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን እና ገንዳዎቹ በአንድ አካባቢ ለተጨናነቁ የማህበረሰብ ክፍሎች የንፅህና አገልግሎትን በማሳደግ እና የዜጎችን ለበሽታ ወረርሽኝ ተጋላጭነት በመቀነስ በኩል ፋይዳቸው ትልቅ ነው ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ናቸው፡፡

የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ አዴል ኮድር

የመፀዳጃ ገንዳዎቹ ከቆሻሻ ጋር ንክኪ ከሚፈጥሩ ነፍሳት የሚመጡ በሽታዎችን እና የበሽታ ስርጭትን ለመቀነስ እንዲሁም ደኅንነቱ የተጠበቀ የመፀዳጃ ቤት እንዲኖር ድርሻቸው የጎላ ነው ብለዋል።

ከጃፓን መንግሥት የተበረከቱት 165 ሽህ የሚሆኑት የመጸዳጃ ገንዳዎች በዩኒሴፍ በኩል ለተጠቃሚዎች የደርሰ ሲሆን ይህም በጃፓን መንግሥት በኩል ለኢትዮጵያ ከተሰጠው 4 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ የተወሰደ ነው፡፡ ገንዳዎቹ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሰራጫሉ ተብሏል፡፡ የኮሮናቫይረስን ተጽዕኖ በማቃለል በኩልም ግብዓቶቹ ጠቀሜታቸው ከፍ ያለ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና አጠባበቅን ለማሻሻል ጥረት እያደረገች ቢሆንም በቤተሰብ ደረጃ መሰረታዊ መፀዳጃ ቤቶች በመገንባት ዘላቂ የልማት ግቦችን ከግብ ለማድረስ ብዙ ሥራዎች እንደሚጠበቅባትም ተነስታል፡፡

ድጋፉ በ 10 የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ የሚሰራጭ ሲሆን 750 ሽህ የሚደርሱ ዜጎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብላል።

ዘጋቢ:– ጋሻው ፈንታሁን– ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ሁሉም በሀገር ነው. ..!!! (ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን)

admin

‹‹የእምዬን መሪነት የእቴጌን ብልሃት የኢትዮጵያን ክብር ፣ ሰው ዝም ይበልና ተራራው ይመስክር››

admin

300 በላይ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በቅጣት ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ መደረጉን የፌደራል የሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።

admin