27.09 F
Washington DC
March 8, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ በቅርቡ ግንባታው የጀመረው የአጅማ ጫጫ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን ለማገዝ መዘጋጀቱን አስታወቀ።

የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ በቅርቡ ግንባታው የጀመረው የአጅማ ጫጫ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን ለማገዝ መዘጋጀቱን አስታወቀ።

ባሕር ዳር፡ ጥር 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) በደብረብርሃንና አካባቢው ላለው ከፍተኛ የኢንዱስትሪ ፍሰት በቂ ግብዓት እንዲኖር የተለያዩ የግብርና ምርምር ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ገልጻል። ዩኒቨርሲቲው አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ ነው።

በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢም የተለያዩ የምርምር ሥራዎች የሚከናወኑባቸው፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ የተለያዩ ሰብሎችና የዛፍ ችግኝ፣ የዶሮ ርባታና ተማሪዎች በተግባር የታገዘ ስልጠና የሚሰጡበት ቦታ መኖሩን ተመልክተናል።

ከዩኒቨርሲቲው ውጪ በጫጫ፣ በአንኮበር፣ በሸዋሮቢትና በደብረ መዓዛ የግብርና ምርምርና ሠርቶ ማሳያ ቦታ መኖሩንም ከዩኒቨርሲቲው የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አዳዲስ የግብርና የምርምር ውጤቶች በነዚህ አካባቢዎችና በቤተ ሙከራ ተሠርተው በዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ አገልግሎት በኩል ለሕዝቡ እንደሚደርሱም የኮሌጁ የእንስሳት ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰርና የጥናትና ምርምር ተባባሪ ዲን ሁሉንም ጋተው አስረድተዋል።

የኮሌጁ ዲን ዮሐንስ ሙሉነህ (ዶክተር) በእጽዋት፣ በእንስሳት፣ በተፈጥሮ ሀብት፣ በአበባ እርሻና በግብርና ምጣኔ ሀብት ላይ ያተኮረ የምርምር ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አመላክተዋል። ለአብነትም ወደ 78 ኩንታል ምርጥ የቢራ ገብስ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢና በጫጫ በማልማት በግብርና ዘርፍ በተሠማሩ ባለሀብቶች በኩል ለአርሶ አደሮች ማሠራጨቱን አስታውሰዋል።

ይህም በአካባቢው ላሉ ሁለት የቢራ ፋብሪካዎችና በቅርቡ ተመርቆ ሥራ ለጀመረው የብቅል ፋብሪካ በቂ ግብዓት እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።

በአካባቢው ከፍተኛ የወተት ሀብት መኖሩን ተከትሎም የወተት ፋብሪካዎች ተተክለዋል። የእንስሳት ጤናን በመጠበቅ ጥራት ያለው ወተት በብዛት በማምረት ሀብቱ ሳይባክን ለገበያ ለማቅረብም ለአርሶ አደሮች ሥልጠና ተሰጥቷል ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው የተሻለ የእንስሳት መኖ ዝርያ በማልማትም አከፋፍሏል። በጓሮ አትክልት፣ በንብ ማነብ፣ በዶሮ እርባታ፣ በዓሳ ልማት፣ በተፈጥሮ ሀብትና ሌሎችም የግብርና ዘርፎች ምርትን በማሳደግ ገቢን መጨመር የሚያስችሉ ዘመናዊ አሠራር እንዲለመድ እየሠራባቸው ያሉ ዘርፎች ናቸው።

ዶክተር ዮሐንስ እንዳሉት የሰሜን ሸዋ ዞን አብዛኛው አካባቢዎች ቀዝቃዛ የአየር ጸባይ ያላቸው በመሆኑ የዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስክ የደጋ ግብርና ነው። በዋናነት ደግሞ በቢራ ገብስ፣ በወተት ሀብቱና በደጋ ፍራፍሬ ላይ ትኩረት ይደረጋል።

በቅርቡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የተካሄደለት የአጅማ ጫጫ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የዩኒቨርሲቲውን ሥራ እንደሚጠብቅም ዶክተር ዮሐንስ ተናግረዋል።

ከመስኖ ልማትና ከዓሳ ርባታ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመሥራት ቁርጠኝነት መኖሩንም አመላክተዋል። ለዚህም በነበረው የሥራ እንቅስቃሴ ከማኅበረሰቡ፣ ከሌሎች የግብርና ምርምር ተቋማትና ከመንግሥት እንዲሁም ከልዩ ልዩ ማኅበራት ጋር የነበረውን መልካም ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም የኮሌጁ ዲን ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ኢዜማን ጨምሮ 5 ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን ቀይረው እንዲያቀርቡ ቦርዱ አሳሰበ

admin

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ ጀምረዋል።

admin

በአምባሰል ወረዳ በ64 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባ የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ

admin
free web page hit counter