61.99 F
Washington DC
May 11, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የ‹‹ዓለም ባንክ ግሩፕ›› ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ በክልሉ በሚገኙ 32 ከተሞች የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አስታወቀ።የ‹‹ዓለም ባንክ ግሩፕ›› ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ በክልሉ በሚገኙ 32 ከተሞች የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የከተሞች ተቋማዊ እና የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ መርሃ ግብር (ዩ.አይ.አይ.ዲ.ፒ) ሥራ ሀገሪቱ በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ከያዘችው ዕቅድ እንደ አንድ መነሻ ተደርጎ ተቀምጧል። ከዚህ ግብ ለመድረስ የከተሞች የካፒታል ኢንቨስትመንትን ከነበረበት በሦስት እጥፍ ማሳደግ ግድ ይላል። ይህንን ለማሳካት የሀገሪቱ የውስጥ አቅም የማይችል በመሆኑ ከተለያዩ አጋር አካላት የብድርና የእርዳታ ገንዘብ በማፈላለግ የተለያዩ የልማት ሥራዎች በከተሞች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከእዚህ ውስጥ ደግሞ የከተሞች ተቋማዊ እና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ መርሃ ግብር (ዩ.አይ.አይ.ዲ.ፒ) አንዱ ነው።
በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የከተሞች ተቋማዊ እና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ መርሃ ግብር ከፍተኛ ሂሳብ አዋቂ አቤል ጥላሁን እንደነገሩን የከተሞች ተቋማዊ እና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ መርሃ ግብር (ዩ.አይ.አይ.ዲ.ፒ) ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በከተሞች ማኀበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማቶችን ማጎልበት እና ማስቀጠል ላይ ትኩረት ተድርጎ እየተሠራ ይገኛል።
አረንጓዴ ልማት፣ የደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ፣ የመንገድና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል በትኩረት ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ተጠቃሾች ናቸው። ባለሙያው እንዳሉት ከ20 ሺህ በላይ የሕዝብ ብዛት ያላቸው፣ በከንቲባ የሚመሩ እና የከተማ ምክር ቤት ያላቸው 32 የከተማ አስተዳደሮች ናቸው በ‹‹ዓለም ባንክ ግሩፕ›› ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገኙት።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ከሆኑት 117 ከተሞች ውስጥ የአማራ ክልል ከተሞች የተሻሉ ሆነው በመገኘታቸው በዚህ ዓመት ከ2 ቢሊዮን 298 ሚሊዮን 800 ሺህ ብር በላይ መመደቡን ከፍተኛ ሂሳብ አዋቂው አቤል ጥላሁን ገልጸዋል። ይህም በ2011 ዓ.ም መርሃ ግብሩ ሲጀምር ከነበረው በጀት ከ1 ቢሊዮን 618 ሚሊዮን 426 ሺህ ብር በላይ ብልጫ አለው ነው ያሉት።
መርሃ ግብሩ የከተማ ልማት ፖሊሲዎችን፣ ግቦችን እና ስትራቴጅዎችን መሠረት ተደርጎ ተዘጋጅቷል፤ በአንደኛው እና በሁለተኛው መርሃ ግብር ላይ ያልተፈጸሙ ተግባራትንም ለማከናወን ታስቢ ተደርጓል፤ መርሃ ግብሩ እንደጀመረ ከተማ አስተዳደሮች የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ባለማቅረባቸው በጀቱን በወቅቱ ያለመልቀቅ ችግር ቢኖርም በዚህ ዓመት ችግሮች ተፈተዋል፤ ከተሞችም ቀድመው ወደ ልማት መግባታቸውን አቶ አቤል ነግረውናል፡፡
ይሁን እንጅ አሁንም ከጨረታ እስከ ውል አሰጣጥ፣ የተቋራጮች አዲስ መሆን እና ልምድ አለመኖር፣ ግዥ ቀድሞ አለማከናወን ችግሮች እንዳሉ ባለሙያው ገልጸዋል። የሲሚንቶና ብረት ግብዓቶች ዋጋ በየጊዜው መናርም በልማቱ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል ብለዋል።
ከመርሃ ግብሩ የሚጠበቁ ውጤቶች ምንድን ናቸው? በሚል አሚኮ ላቀረበው ጥያቄም
-የዓለም ባንክ ግሩፕ ድጋፍ ቢቆም ራሱን ችሎ የሚቆም ስርዓት መፍጠር ተቀዳሚ ተግባር ነው።
-የሚገነቡት መሰረተ ልማቶች ዜጎችን ያሳተፉ መሆናቸው፡፡
-የከተሞችን የውስጥ ገቢ በማሳደግ ካቀዱት ከ95 እስከ 105 በመቶ ገቢ እንዲሰበስቡ ይጠበቃል።
-የተሻሻለ እና ጥራቱን የጠበቀ መሠረተ ልማት ግንባታ እንዲኖር ማድረግ፡፡
-የተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥ፣የአሰራር እና አስተዳደር ሥርዓት እንዲኖር ይፈለጋል።
-የሚሠሩ ፕሮጀክቶች ማሕበራዊ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖ ችግር የማይፈጥሩ እንዲሆኑ ይጠበቃል፡፡
-ልማቶች ከመሰራታቸው በፊት የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ማካሄድ፣ ከተሠራ በኋላ ደግሞ በዕቅዱ መሠረት መሠራቱን የአካባቢ ኦዲት ሥራ መሥራት ነው ተብሏል።
የ‹‹ዓለም ባንክ ግሩፕ›› መርሃ ግብር እስከ 2015 ዓ.ም የሚቀጥል እንደሆነም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleበኢትዮጵያ አይሲቲ ተሰጥኦ ሥነ ምሕዳርን ለማልማት የሚረዳ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈረመ፡፡

Source link

Related posts

ቦርዱ ሕጋዊ ሃላፊነቱን እና ግዴታውን እንደሚወጣ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ አስታወቁ

admin

መሬት አስረክቦ ትዕግስት – እግር እያስበሉ ዝምታ …!!! (አባይነህ ካሴ)

admin

በአስመጪ ዳዊት የማነ ሀሰተኛ ሰነድ ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረ ገጀራ ተያዘ

admin