82.62 F
Washington DC
June 21, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የኮሮናቫይረስ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።የኮሮናቫይረስ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ ስርጭት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የአማራ ክልል
የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ የኮሮና ቫይረስ መከሠትን ተከትሎ
ስርጭቱን ለመግታት አበረታች የሚባል ቅድመ ጥንቃቄ ይደረግ እንደነበር አንስተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ የቫይረሱን
ስርጭት ለመግታት ሲደረግ የነበረው ጥረት በመቀዛቀዙ ስርጭቱ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡ በተያዘው
ሚያዝያ ወርም የመከላከል ሥራውን አጠናክሮ መቀጠል በማስፈለጉ መመሪያ ወጥቶለት መተግበር መጀመሩን ኃላፊው
አንስተዋል።
በኢንስቲትዩቱ የኅብረተሰብ ጤና ቅኝት ባለሙያ አቶ ተስፋሁን ታደገ አሁናዊ የስርጭቱን ሁኔታ በተመለከተ እንደገለጹት በአማራ
ክልል
• ከ990 በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል
• 218 ያህል ሰዎች ሞተዋል
• በኮሮናቫይረስ የሞት ምጣኔ ደረጃ (2 ነጥብ 18 በመቶ) ከዓለምአቀፉ የሞት ምጣኔ (2 ነጥብ 12 በመቶ) ጋር ሲነጻጸር
የበለጠ ነው፡፡
አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ናሙና የመውሰድ መጠን ቀንሶ የሞት መጠን ግን መጨመሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትና ገዳይነት
እየጨመረ መሆኑን እንደሚያመላክትም አብራርተዋል። እስካሁን ድረስ ለጤና ባለሙያዎችና ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ
የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሰጠት የተጀመረው የኮሮና መከላከያ ክትባት መከተብ ከነበረባቸው ሽፋኑ 5 በመቶ ብቻ መሆኑ
የስጋቱ ማሳያ ሆኖ ተመላክቷል ብለዋል።
በአማራ ክልል ውስጥ በርካታ ተፈናቃዮች በመጠለያ ቦታዎች ለቫይረሱ ስርጭት ተጋላጭ በሆነ አሰፋፈር እንዲኖሩ መገደዳቸው
ሌላኛው ስጋት መሆኑን አቶ ተስፋሁን ጠቅሰዋል።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዋለ በላይነህ እንዳሉት በዚህ ወር መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ
ሀገራት በቫይረሱ በሚያዙ ሰዎች አራተኛ ደረጃ ላይ ነች፤ ከተያዙት ውስጥ በአስጊ ሁኔታ ላይ በሚገኙ 1 ሺህ 59 ታማሚዎች
የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛለች፡፡ ይህም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት አሁንም ትኩረት ሰጥቶ መሠራት እና መጠንቀቅ
እንደሚገባ አሳስበዋል።
በአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ጤና ቢሮ ትብብር የምክክር መድረክ ተዘጋጅቶ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትና በሽታ
ያለበት ደረጃ ተገምግሟል፡፡ በቀጣይ ሦስት ወራት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያላሠለሰ ጥረት
እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡
ዘጋቢ፡- ዋሴ ባየ – ከደብረታቦር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleʺዓባይ የዘጋውን ዓባይ ይከፍተዋል “

Source link

Related posts

የሱማሌ ክልል ዳያስፖራ አባላት የመጀመሪያ ክልላዊ ውይይት በጅግጅጋ እየተካሄደ ነው።

admin

ሐረር ለዘመናት የምትታወቅባቸው መቻቻልና የመተባበርን የመሰሉ እሴቶች ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል- አቶ ኦርዲን

admin

በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በኢትዮጵያ የ12 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል – የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

admin