51.91 F
Washington DC
May 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የእንስሳት ሃብትን ለማዘመን መንግሥት የመሬት፣ የብድር አቅርቦት እና የግል ባለሃብቱን ማሳተፍ እንደሚገባው የአማራ ምሁራን መማክርት ገለጸ፡፡የእንስሳት ሃብትን ለማዘመን መንግሥት የመሬት፣ የብድር አቅርቦት እና የግል ባለሃብቱን ማሳተፍ እንደሚገባው የአማራ ምሁራን
መማክርት ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የእንስሳት ሃብትን በቀጣይ አስር ዓመታት ለማሳደግ የምሁራን መማክርት እየሠራ
መሆኑን ገልጿል፡፡ በክልሉ የእንስሳት ሃብት የቀጣይ አስር ዓመት መሪ እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና ትምሕርት ክፍል መምሕር እና በአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ የእንስሳት ሃብት
ልማት ዘርፍ አስተባባሪ የሽዋስ ፈረደ (ዶክተር) እንዳሉት በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ካለው የእንስሳት ቁጥር አኳያ በዘርፉ
በሚፈለገው መጠን ጥቅም እየተገኘ አይደለም፡፡
የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤም ከተመሰረተ ጀምሮ የእንስሳት ሃብቱን ለማዘመን እየሠራ ይገኛል፡፡ በተለይም የእንስሳት
ሃብቱን ለማዘመን መንግሥት የግል ባለሃብቱ እንዲሳተፍ፣ የመሬት፣ የብድር አቅርቦት ማሳደግ እና መኖ ከታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገባ
ለማስቻል ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይገባል ነው ያሉት፡፡
መማክርቱ በዘርፉ ያሉ የውጭ ሀገር ተሞክሮዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ለመንግሥት የማቅረብ ሥራ እንደሚሠራ አንስተዋል፡፡
በዚህም በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ከ10 ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከግብርና ምርምርና ከእንስሳት ሃብት ልማት ኤጀንሲ ጋር በጋራ እየተሠራ
ይገኛል ብለዋል፡፡
መንግሥት የሰለጠነ ባለሙያ በመመደብ፣ የተቋማት የአሠራር ለውጥ ማድረግ እንዳለበት መክረዋል፡፡
የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ኤጀንሲ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፈንቴ የሻው እንዳሉት ባለፉት ዓመታት የወተት አቅርቦት፣
የእንቁላል እና የስጋ ምርት ማሻሻል ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሲከናወን መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ የወተት ምርትን ለማሳደግ የአካባቢ
ላሞችን ምርታማነት ማሳደግ የሚያስችል አሠራር ተዘጋጅቶ ሲሠራ መቆየቱን ገልጸውልናል፡፡
የገበያ ሁኔታው አመች በሆነባቸው አካባቢዎች የዝርያ ማሻሻያ ሥራ እየተሠራ ይገኛል፡፡ ባለሃብቶችም በወተት ማቀነባበር ሥራ
መሰማራታቸውን አንስተዋል፡፡
ሕብረት ሥራ ማሕበራትም የአርሶ አደሩን የወተት ምርት በማሰባሰብ ወደ አዲስ አበባ መላክ ጀምረዋል፡፡ በዚህም 66 ሺህ ሊትር
ወተት በየቀኑ ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ እንደሚላክ ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡
ባለፉት አምስት ዓመታት የእንቁላል ምርት ከእጥፍ በላይ ቢጨምርም ከሕዝብ ቁጥር መጨመርና ከማኀበረሰቡ የመግዛት አቅም
ጋር ተያይዞ ፍላጎትን ማሟላት አለመቻሉን አንስተዋል፡፡
የስጋ ምርትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢገኝም ከስጋ ጥራቱ ጋር በተገናኘ ለውጭ ገበያ ማቅረብ አለመቻሉን አንስተዋል፡፡
መተማ፣ ቋራና ጃዊ አካባቢ የሳር አቅርቦት ያለበትና ለሱዳን ቅርብ በመሆናቸው ባለሃብቶች በዘርፉ መሰማራት ቢችሉ ውጤታማ
እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል በእንስሳት ሃብት ከሀገሪቱ 29 በመቶ ይሸፍናል፤ የክልሉ ጥቅል ምርት 24 በመቶ እንደሚሸፍንም አንስተዋል፡፡
በየዓመቱም ከ6 በመቶ በላይ እድገት እያሳየ ያለ ዘርፍ መሆኑንም ሥራ አስኪያጁ ነግረውናል፡፡
የቴክኖሎጅ ሽግግርን ማሳደግ፣ የመኖ አማራጮችን መፍጠር፣ የሀገር ውስጥ እንስሳት ዝርያዎችን በመረጣ ማሻሻልና ከታወቁ
የውጭ ዝርያዎች ጋር ማዳቀል፣ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ በልማቱ የግል ባለሃብቶችን ተሳትፎ ማሳደግና
ምርታማነትን የሚያሳድጉ ግብዓቶችና የቴክኖሎጅ አቅርቦትን ማሳደግ በአስር ዓመቱ ዕቅድ ትኩረት የተሰጣቸው ናቸው፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተመለከተ የሚመጡ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን መቋቋም የሚያስችል የተደራጀ ሥልት መቀየስ እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ።

Source link

Related posts

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ በደቡብ ሱዳን ከተሰማሩ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሻለቆች ጋር ተወያዩ

admin

የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ለሽሬ እና አካባቢው ነዋሪዎች አልሚ ምግብና መድሃኒት ላከ

admin

በዓለም ላይ በህገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ በማስመሰል ከ800 ቢሊየን እስከ 2 ትሪሊየን ይመዘበራል ተባለ

admin