82.62 F
Washington DC
June 22, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የኢትዮ-አውሮፓ ሕብርት የጋራ ምክክር ተካሄደ።
የኢትዮ-አውሮፓ ሕብርት የጋራ ምክክር ተካሄደ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 03/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮ-አውሮፓ ህብረት የጋራ ምክክር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ
ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ጆሃን ቦርግስታም በጋራ መሪነት ተካሂዷል።
ምክክሩ በኢትዮ-አውሮፓ ህብረት የትብብር ጉዳዮች፣ የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ፣ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ እንዲሁም በቀጣይ
በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ላይ በማተኮር የተካሄደ ነበር።
በወቅቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት መካከል
የሚደረገው ቋሚ ምክክር በኮቶኖ ስምምነት እንዲሁም በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት መካልል እ.ኤአ በ2016 የተፈረመውን
የስትራቴጂያዊ የትብብር ሰነድ መሰረት ያደረገ ሰለመሆኑ ገልጸዋል።
በወቅቱም ተሳታፊ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት አምባሳደሮች በሰጡት አስተያየት የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ የኮቪድ-19
ወረርሽኝን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት በተያዩ መልኩ ድጋፍ ማደረጉን አስታውሰው፣ ወረርሽኙ በኢኮኖሚው ላይ
የሚደርስባትን ተጽዕኖ ለመከላከል የተከተለችውን መንገድ እንደሚያደንቁ ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵ ኢኮኖሚውን ለመክፈት በያዘቸው አቋም በተሌኮም ሴክተር የታየው ተግባራዊ እርምጃ የሚበረታታ መሆኑንም
አንስተዋል።
በሌላ በኩል አውሮፓ ኩባንያዎች ከረጅም ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ በወጪ ንግድ እንዲሁም በስራ እድል
ፈጠራ አስተዋጸኦ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በአገሪቱ በሚወጡ ህጎች በአፈጻጸም ወቅት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ አስቀድሞ ምክክር እንዲደረግ
ያላቸውን አስተያየት ገልጸዋል።
የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተም የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ቅንጅታዊ አሰራሮች የበለጠ ለማሻሻል የሚቻልባቸው
መንገዶች እንዲታዩ፣ በክልሉ የግብርና ተግባራት ትኩረት እንደሚሹም ተወያይተዋል ።
መንግስት በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተሳታፊ የሆኑ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ የሚያደርገው ጥረትን የሚደግፉ መሆኑንና
በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሰብዓዊ መብት ተቋም መካከል ገለልተኛ
የጋራ ምርምራ ለማድረግ የተጀመረው ሂደት አንደሚያደንቁ ገልጸዋል።
በስደተኞች ዙሪያ የሚከናወኑ ተግባራትን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እንዲሁም መንግስት ለፕሬስ ነጻነት ተገቢው
ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ቀጣዩን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ከሎጀስቲክ ስርጭት አንጻር የሚያጋጥሙ ችግሮች ትኩረት መሰጠት ያለበት መሆኑን
አንስተዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ምንም አንኳ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ግጭቶች የተከሰቱ ቢሆንም
እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የደቀነው አሉታዊ ተጽእኖ ቢኖርም ኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችን በመፍጠሯ
የውጭ ቀጥታ አንቨስትመንት ፍሰት ከመሳብ አንጻር አበረታች ውጤቶች መመዝገቡን አንስተዋል።
ኢንቨስተሮች የሚያጋጥማቸውን ማነቆዎች ለመፍትታ አገራዊ የቅንጅት መድረክ መቋቋሙን አንስተው፣ የአውሮፓ ህብረት አገራት
ኩባንያዎችም የሚጋጥማቸውን ተግዳሮቶች በዚሁ ማዕቀፍ የሚታይ ስለመሆኑ አስረድተዋል።
በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የተሟላ መሰረት ልማት ያለው የቅሊንጦ የኢንዱስትሪ ፓርክ በመዘጋጅቱንም
በዘርፉ በመሰራት ተሳትፎ አንዲደርጉ ጠይቀዋል።
በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተም በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ ለሚሰማሩ አካላት ያልተገደበ ምቹ ሁኔታ
መመቻቸቱን አስታውሰዋል።
ለእርዳታ አቅራቢ ሰራተኞች ደህንነት ሲባል በተወሰኑ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል።
ነግር ግን በአጠቃላይ በክልሉ የተደራሽነት ችግር መኖሩን አመላካች አለመሆኑን አስረድተዋል።
በክልሉ በሁለተኛውና በሶስተኛው ዙር 5.2 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ መቻሉንም ጠቅሰዋል።
የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊዎችን በተመለከተ የሚቀርበው አሀዝ ቀደም ሲል በክልሉ ያሉና የተለየ ሀብት የተመደበላቸውን
ተፈናቃዮች፣ የምግብ ዋስትና ተረጂዎች እንዲሁም ስደተኞችን ቁጥርን ከግምት ያላስገባና የተጋነነ መሆኑን አንስተዋል።
በሲቪል እና ወታደራዊ አካላት መካከል ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የሰብዓዊ አቅርቦት ተደራሽ ለማሳደግ የተጠናከረ ስራ
እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
በክልሉ የግብርና ስራዎች የቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶ የግብርና ግብዓቶች የማቅረብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እየወጡ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሂደቱን ለማፋጠን የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ
ስለመሆኑም ገልጸዋል።
በትግራይም የተፈናቀሉ ዜጎች ከዝናብ ወቅት በፊት ለመመለስ እንዲቻል በክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ
አህመድ በተቋቋመው ኮሚቴ አማካይነት ስራዎች እየተከናወኑ ስለሆኑም ገልጸዋል።
የሕወሓት ቅሪቶች በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር አባላት እና ሌሎች ንጹሃን ዜጎችን ዒላማ ማድረግ መቀጠላቸውን ጠቅሰው፣ ዓለም
አቀፉ ማህበረሰብ ሁኔታውን በሚዛን በማየት መሰል ተግባራትን በይፋ መኮንን እንደሚገባው ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል የሚገኙ ሁለት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎችን ወደ ሌላ በማዛወር አስፈላጊው ግብዓት በሟሟላት ወደ ስራ
ማስገባት መቻሉን እንዲሁም ተጨማሪ መጠለያዎችን የማቋቋም ስራዎች ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሸን ጋር
በመተባበር እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም የጠቅላይ አቃቢ ህግ፣ የፌደራል ፖሊስ ከሚሽን ከትግራይ ክልል ጊዚዊ አስተዳደር ጋር
በመተባበር አስፈላጊው ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።
በተያያዘም የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛው የሰብዓዊ መብት ተቋም ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር የጋራ ምርመራ
ለማካሄድ ባለሙያዎች በክልሉ ማሰማራታቸውን ጠቅሰው፣ የአፍሪካ ህብረትም በተመሳሳይ ስራውን እንዲጀመር መንግስት
እየጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ግጭት በነበራቸው በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የጸጥታ ሁኔታዎች በመሻሻላቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀድሞ
ቀያቸው ለመመለስ የሚያስችል ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የፕሬስ ነጻነትን በተመለከተም መንግስት ከመቸውም ጊዜ በላይ የፕሬስ ነጻነት እንዲከበር ማድረጉን ጠቅሰዋል።
ነገር ግን ከጋዜጠኝነት ስነ ምግባርን ባፈነገጠ መልኩ የተለየ ተልዕኮ በመያዝ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ጋዜጠኞች ስለመኖራቸው
አንስተዋል።
ቀጣዩ ምርጫ ነጻ፣ ገለልተኛ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከናወን መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸው፣ ለዚህም የኢትዮጵያ ምርጫ
ቦርድ ገለልተኛ ሆኖ አንዲደራጅ መደጉን ገልጸዋል።
የሎጀስቲክ ስርጭት ችግሮችን ለመቅረፍም ቦርዱ የጊዜ ሰሌዳውም በመከለስ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት
ማድረጉን አንስተዋል።
በመጨረሻም ተሳታፊዎች በመድረኩ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የተደረገው ጥልቅ ውይይት በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት
መካከል ያለውን የስራቴጂያዊ ግንኙነት አመላካች መሆኑን ጠቅሰዋል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት
ቤት ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m


Previous articleየኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ፡፡
Next article“በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት ታሪካዊ፣ ጠንካራና በማናቸውም የውጭ ተፅዕኖ የማይናወጥ ነው” የጅቡቲ ፕሬዝዳንት እስማዔል ኡመር ጉሌህ


Source link

Related posts

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ከሀገር ውስጥ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከ134 ሽህ በላይ ታዛቢዎች እንደቀረቡ ገለጸ፡፡

admin

በገጠር የበይነ-መረብ ግንኙነትንለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

admin

ሱዳን ኢትዮጵያን የወረረችባቸው 10 ምክንያቶች (መስፍን ሙሉጌታ)

admin