51.91 F
Washington DC
May 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የአፍራሽ ኀይሎችን ተልዕኮ በመመከት ሁሉም አካል ለሕዝብ ደኅንነት፣ ለሀገራዊ አንድነትን እና ብልጽግና የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ቀረበ፡፡

የአፍራሽ ኀይሎችን ተልዕኮ በመመከት ሁሉም አካል ለሕዝብ ደኅንነት፣ ለሀገራዊ አንድነትን እና ብልጽግና የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ቀረበ፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 15/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

አቶ ደመቀ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአጭር እድሜው አንጋፋ ተግባራትን በማከናወን የበኩር ልጆቹን ለማስመረቅ በመብቃቱና ተማሪዎች ለምረቃ በዓላቸው በመድረሳቸው እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው እንጅባራ ላይ እንዲመሰረት እና ለዚህ እንዲበቃ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትንም አመስግነዋል አቶ ደመቀ፡፡

በሀገራችን የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የግርግር ማዕከል በማድረግ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ አካላት ዩኒቨርሲቲዎች እጅግ አሳዛኝ ድርጊቶች ይፈጸሙባቸው እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ በነዚህ ጊዜያት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል ላስቻሉት የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው ትኩረቱን ሀገርን በሚያሻግር ምርመር ላይ እንዲያደርግ አስገንዝበዋል፡፡

እንደ ሀገር ትምህርትና ሥልጠናን ተደራሽ በማድረግ የተማረ የሰው ኀይል ለማፍራት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አቶ ደመቀ አብራርተዋል፡፡ በዚህ ረገድ ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተመዘገበ ቢሆንም ቀላል በማይባል ደረጃ ሀገር የማትጠብቀው ጥፋትና ጉድለት ሲስተዋል መቆየቱንም ገልፀዋል፡፡

የኅብረተሰቡን የመማር ፍላጎት ለማርካት እና ማኀበረሰባዊ ንቃትን ለማጎልበት ነገሮችን በምክንያታዊነት መመዘን የሚያስችል አቅም መገንባት ሲገባ ፈር የለቀቁ አካሄዶች በተማረው ማኅበረሰብ ሲጠነሰሱ እና አሳዛኝ ጥፋቶች እየተስተዋሉ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ በተለያየ አካባቢ እየተፈጸሙ ያሉ አረመኔአዊ ድርጊቶች በአብዛኛው በተማሩ እና የተሻሉ ግንዛቤ ባላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ፊት አውራሪነት እየተቀነባበሩ እና እየተፈጸሙ መሆናቸውን ነው አቶ ደመቀ የተናገሩት፡፡ በአንጻሩ ሕዝቡ ቱባውን የአብሮነት እና የአጋርነት ባህሉን ጠብቆ ችግሩን ለመሻገር ጥረት ሲያደርግ ይስተዋላል ብለዋል፡፡

እንደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጥቂቶች ከሀገር እና ከሕዝብ በላይ ሆነው በሀገር ላይ የከፋ ክህደት እና ጭካኔ አሳይተዋል፤ ሌሎች ዜጋን በማንነቱ እየለዩ ጭካኔና ጭፍጨፋን የእርካታ ምንጫቸው ሲያደርጉት ይስተዋላል፤ በቅርቡ መተከል አካባቢ የተፈጸመውን የዜጎች ጭፍጨፋ እና መፈናቀል ለአብነት አንስተዋል፡፡

አቶ ደመቀ እንዳሉት መተከል የሀገሪቱ ልዩ ልዩ ጸጋዎች አምባ፣ የአብሮነት ማሳያ እና የኢትዮጵያ ተስፋ የነበረ አካባቢ ነው፡፡ አሁን ግን በከፋ ጫፍ በምድራችን የጭካኔዎች ጥግ ማሳያ ሆኗል፤ የዚህ ሀሳብ አቀንቃኞች፣ ተላላኪዎች፣ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ፈጻሚዎች በደሃ ደም ላይ ተረማምደዋል ነገር ግን ከቶውን ከተጠያቂነት ማምለጥ አይችሉም፤ እነዚህ የሀገር እና የሕዝብ ጠላቶች በአሁኑ ወቅት በተባበረ ክንድ እየተወገዱ ቢሆንም ለዘመናት ሲያራምዱት የነበረው የተሳሳተ ትርክት ፈጽሞ ከስሩ እስኪነቀል ድረስ በአብሮነት ልንታገለው፣ ልናርመው እና ልናስተካክለው ይገባል ነው ያሉት፡፡

ሁሉም አካል የአፍራሽ ኀይሎችን ተልእኮ በመመከት ለሕዝብ ደኅነት ለሀገራዊ አንድነትን እና ብልጽግና የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አስተላፈዋል፡፡

“የኢትዮጵያዊነት ከፍታ ማሳያ አንድነታችሁ እና አብሮነታችሁ በመሆኑ ይህን ትርጉም አዘል ኀላፊነት እንድታስፋፉት የመሪነት ሚናችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ” ብለዋል አቶ ደመቀ መኮንን፡፡

ዘጋቢ፡- የማነብርሃን ጌታቸው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ይህቺን ውብ ሃገር! – በይመር ሙሄ

admin

የፓለቲካ ፓርቲዎች የኘሮግራም ማስተዋወቅና የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ ግብር በጎንደር ተካሄደ

admin

የምርት ብክነትንና የጥራት መጓደልን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡

admin