64.54 F
Washington DC
June 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“የአዊ ሕዝብ በፍቅር፣ በልማት፣ በአብሮነት እና በገናና የኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ቦታ ያለው ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

“የአዊ ሕዝብ በፍቅር፣ በልማት፣ በአብሮነት እና በገናና የኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ቦታ ያለው ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 01/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የምርጫ 2013 የማኒፌስቶ የትውውቅ መድረክ በእንጅባራ ከተማ አካሄዷል። የፓርቲው ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ከነዋሪዎች ጋር ውይይትም አድርገዋል፡፡ ከብሔረሰብ አስተዳደሩ ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የፓርቲው ደጋፊዎች እና አባላት ተገኝተዋል።

ተሳታፊዎቹ ከሳ – አዘና -ግምጃ ቤት መንገድ ግንባታ እና የዳንግላ-ጃዊ የአስፋልት መንገድ ግባታዎች እንዲጀመሩ ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የእንጅባራ ሆስፒታል ያለበት የመድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት እንዲቀረፍ አንስተዋል፡፡ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና የኑሮ ውድነት በመቆጣጠር በኩል መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራም ነዋሪዎቹ በውይይቱ ወቅት ለፓርቲው ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ ጠይቀዋል፡፡ የአማራ መፈናቀል ሊቆም እንደሚገባ ሌላው ነዋሪዎቹ ያነሱት ሐሳብ ነው፡፡

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ኅብረተሰቡ በስፋት የሚሳተፍበትን እና ያለምንም ተጽዕኖ እንዲመርጥ እየተሠራ መሆኑን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናግረዋል፡፡

ብልጽግና በዚህ ወቅት እንደ መንግሥትና እንደ ተወዳዳሪ ፓርቲም ብዙ ኀላፊነት እየተወጣ መሆኑን አስታውቀዋል። “የአዊ ሕዝብ በፍቅር፣ በልማት፣ በአብሮነት እና በገናና የኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ቦታ ያለው ነው” ያሉት አቶ ደመቀ በሐሳብ ልዕልና የሚያምን የተሰጠውን ኀላፊነት በአግባቡ እየተወጣ የሚገኝ እንደሆነም ገልጸዋል። “ብልጽግና ኢትዮጵያን ከሞት አፋፍ ያዳነ ፓርቲ ነው” ነው ያሉት አቶ ደመቀ ፓርቲው አሁንም መሪ እቅዶችን በማቀድ በልዩ ትኩረት እየሠራ እንደሆነ አስታውቀዋል። የሕዝብን ይሁንታ በካርድ ሲያገኝም የተያዙትን ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ለማሳካትና የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሠራ ተናግረዋል።

በምርጫው የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደርን ወክለው የቀረቡ የብልጽግና ተወካዮች ሀገርን ሊያሻግሩ የሚችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ “ሁልጊዜም የምንጥረው ነገን የተሻለ ለማድረግ ነው” ብለዋል አቶ ደመቀ፡፡

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በልማት፣ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተጠቃሚ እንዲሆን ብልጽግና ፓርቲ እየሠራ እንደሆነ አቶ ደመቀ ገልጸዋል። በቀጣይ ይሠራሉ ተብለው በእቅድ የተያዙ የአስፋልት መንገድ ሥራዎችና ሌሎች ፕሮጀክቶች የሚሠሩበትን ሂደት መመቻቹቱን አብራርተዋል።

በመተከል እና በሌሎች አካባቢዎች ማንነትን መሰረት አደርጎ እየደረሰ ያለውን ሞትና መፈናቀል ለማስቆምም ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ዘንድሮ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና በሕዝቡ ዘንድ ተዓማኒ እንዲሆን ብልጽግና ፓርቲ አበክሮ እየሠራ መሆኑን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባይነሳኝ ዘሪሁን ተናግረዋል። “የኢትዮጵያን ሰላም እና ብልጽግና የማይሹ ኃይሎች ከሩቅም ከቅርብም ውስጣዊ ባንዳዎችን በመጠቀም ሀገራችንን ለማፈራረስ እየሠሩ ቢሆኑም የአያቶቻችንን ደም፣ አንድነት እና ወኔ አሁንም በእኛ ውስጥ ስላለ አይሳካላቸውም” ብለዋል አቶ ባይነሳኝ።

ዋና አስተዳዳሪው ብልጽግና ድል አድራጊነትን አልሞ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል። አቶ ባይነሳኝ ሕዝቡን ከመንግሥት ለመነጠል አበክረው የሚሠሩ አካላት ቢኖሩም የአዊ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰና ሰላም ወዳድ መሆኑን ገልጸው ብልጽግና ቢመረጥ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል። ብሔረሰብ አስተዳደሩ የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ አቅም በሚፈቅደው ልክ እየሠራ መሆኑን እና ከአቅም በላይ የሆኑትን ጉዳዮች ደግሞ ከክልልና ከፌዴራል መንግሥት ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ አመላክተዋል።

በመድረኩ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ብናልፍ አንዱዓለም ብልጽግና በተግባር የተፈተነ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል። ፓርቲው በቀጣይም የኢትዮጵያን ሕዝቦች ተጠቃሚነት በተግባር ያረጋግጣል ብለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ የሚባል ለውጥ መጥቷል፤ብልጽግና ይህ ለውጥ እንዲመጣ መራራ ትግል አድርጓል ነው ያሉት፡፡

ፓርቲው በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ምረጡኝ ብሎ ሲቀርብም ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና በብቃት የማሻገር ቁመና ስለአለው ነው ብለዋል።

ዘጋቢ:- አዳሙ ሽባባው – ከእንጅባራ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የበይነመረብ ስነምግባር – ፀጋዬ ደግነህ ጉግሳ (ዶ/ር) | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

admin

በምን እንግባባ .??? – መሰረት ተስፉ | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

admin

ፖሊስ ለህዳሴ ግድብ ጠንካራ የደጀን ኃይል መሆኑን በድጋሜ አረጋግጧል- ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል

admin