41.83 F
Washington DC
May 8, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በባሕር ዳር እና ደሴ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በባሕር ዳር እና ደሴ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 14/2013 ዓ.ም (አብመድ) በባህር ዳር ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች እየተንቀሳቀሰ የምርጫ ቅስቀሳውን የጀመረው አብን ኢትዮጵያዊነት ቅድመ ሁኔታ የሚቀመጥለት ማንነት አይደለም፣ ሰብዓዊነት የአብን የትግል አስኳል ነው፣ ጊዜው አሁን ነው እና ሌሎች መልዕክቶች መተላለፋቸውን ታዘብ አራጋው ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርኃ ግብሩን በደሴ ከተማ አካሄዷል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ኢትዮጵያዊያኖች በአንድነት ተከባብረው የሚኖሩባትን ሀገር ለመፍጠር እንደሚሠራ ገልጿል፡፡

ምርጫው ፍትኃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ሁሉም ፓርቲዎች የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርቧል፡፡

የአማራ ሕዝብ ጥያቄ እንዲመለስ ችግሮቹ በዘላቂነት እንዲፈቱ ዴሞክራሲን ማስፈኛ ጊዜው አሁን ነው፣ የአማራ ሕዝብ የህልውና ደኅንነት ተረጋግጦ ፍትህ የሰፈነባት ሀገርን ለመገንባት ጊዜው አሁን ነው የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች እንደተላለፉ ዘጋቢያችን ቤተልሄም ሰለሞን ከደሴ ዘግባለች፡፡

በሌላ በኩል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሰሜን ሸዋ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የምርጫ ቅስቀሳ ሥራዉን በይፋ መጀመሩን አስታወቋል፡፡ የምርጫ ቅስቀሳ ሥራዉን መጀመር ምክንያት በማድረግ መግለጫ የሰጠዉ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ ለአባላቱና ደጋፊዎቹ የምርጫ ምልክቱንና የምርጫ መቀስቀሻ መሪ ቃሉን አስተዋዉቋል፡፡

መግለጫዉን የሰጡት የዞኑ አብን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ጌታሁን ሳህሌ የአብን የምርጫ ምልክት ሰዓት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የምርጫ መቀስቀሻ መሪ ቃሉም ጊዜዉ አሁን ነዉ የሚል መሆኑም ተገልጿል፡፡

የዞኑ አብን ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አመራር አቶ ሃሳቡ ተስፋ በበኩላቸዉ የ2013 ጠቅላላ ሀገር አቀፍ ምርጫ ሲካሄድ አብን የዴሞክራሲ ግንባታዉ ላይ የበኩሉን ለመወጣት ወደ ዉድድር ሜዳ ይገባል ብለዋል፡፡

በምርጫዉ ሂደት ላይ ሰላማዊ ትግል እንዲደረግ አብን ለደጋፊዎቹና አባላቱ ጥሪዉን ማቅረቡን ኤልያስ ፈጠነ ከደብረብርሃን ዘግቧል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመቀነስ የሚሰራው ስራ ትኩረት እንዲሰጠው ተጠየቀ

admin

ከተለያዩ ክልሎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በአማራ ክልል ለሚገኙ ዜጎች የዕለት ምግብ እርዳታ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸ

admin

ትግራይ እንዴት ሰነበተች? (ክፍል 3)

admin