68.25 F
Washington DC
May 13, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“የአማራ ሕዝብ ጠላቶች የቱንም ያህል ቢበረቱ አሸናፊ መሆን ግን አይችሉም።” አቶ አብርሃም አለኸኝ“የአማራ ሕዝብ ጠላቶች የቱንም ያህል ቢበረቱ አሸናፊ መሆን ግን አይችሉም።” አቶ አብርሃም አለኸኝ
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ ለትንሣኤ በዓል
የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንኳን ለበዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ ያሉት አቶ አብርሃም ያሸነፈው የተሰቀለው ክርስቶስ እንጂ የሰቀሉት
አይሁዳውያን አይደሉም፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በተከታዮቹ ዘንድ እልህ ፣ ቁጭትና ብስጭት ፈጥሯል፤ የኢየሱስ ክርስቶስ
ሞት የቀዳሚ ሰማዕት ዲያቆን እስጢፋኖስን በድንጋይ ተወግሮ በጭካኔ መገደል ተከትሎ በሰማእታት መንደር ከለቅሶና ከዋይታ
ይልቅ ሰማዕትነትን ለመቀበል እሽቅድድም የፈጠረ ነው ብለዋል ።
ነፍሰ ገዳዮቹ
“ከገደላችሁንስ እምነታችንን አውልቀን እንጥላለን፤ እናንተን ገዳዮቻችንንም እንቀበላለን፤ ለትዕዛዛችሁም እንገዛለን፤
ሕግጋታችሁንም እናከብራለን” የሚል ተስፋ የቆረጠ የፈሪ ድምጽ ሲፈልጉ የሆነው በተቃራኒው መሆኑን አስገንዝበዋል።
“ሰማዕትነትን በጽናትና በድፍረት መጋፈጥ የደቀመዛሙርቱን እምነት አፀናው። አላውያን ነገሥታት የክርስቶስን ተከታዮች
ማሳደድና መግደል ቋሚ ሥራቸዉ ቢያደርጉትም ህልማቸውን ማሳካት ግን አልቻሉም። በመጀመርያው፣ በሁለተኛውና በሦስተኛው
መቶ ክፍለዘመን ሰማዕታት እንደአሸን ተፈለፈሉ። እናጠፋቸዋለን በሚል ዕቅድ ሰይፍ የመዘዙባቸው ደቀመዛሙርት ቁጥር በየእለቱ
እየጨመረ ሄደ። የሰማዕታት የዓላማ ቁርጠኝነትና ሞትን አቅሎ መመልከት የገዳዮችን መንደር በድንጋጤ እንዲናጥ አደረገ። ያን
ዘመን ላስተዋለ ዛሬን መቀበል ከቶ አይቻልም” ነው ያሉት አቶ አብርሃም።
ያሁሉ መከራ ታልፎ እዚህ መድረስ እንዴት ተቻለ ? እንኳን አደረሳችሁ የተባባልነው የክርስቲያኑ ዓለም ያንን ሁሉ የመከራ ዘመን
ተሻግሮ ሃያ አንደኛው ክፍለዘመን ላይ በአሸናፊነት በመገኘቱ ነው። ይኸ ሁሉ የሆነው ግን የፅናትና የብርታት የአሸናፊነት ስነልቦና
የበላይነት የያዘበት የነፃነት ዓለም መፍጠር በመቻሉ እንደሆነም በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት አብራርተዋል።
የአማራ ሕዝብ ጠላቶች የቱንም ያህል ቢበረቱ አሸናፊ መሆን ግን አይችሉም ያሉት አቶ አብርሃም ገዳዮች ዕለታዊ የክፋት
ፍጆታቸውን ማሟላት ከመቻል ያለፈ ዘላቂ ድል መቀዳጀት አይችሉም፤ የግድያ ዜናቸውን እየከተቡ ዘገባ በመሥራት ገዳዮቻችንን
አናሸንፋቸውም፤ የገዳዮችን የጭካኔ ጥግ በዜና አውታሮቻችን እየተቀባበልን የሕዝባችንን ሥነልቦና በመሰባበር አሸናፊ መሆን
አንችልም፤ እንደሰማዕታቱ ሁሉ በአመንበት፣ ለአመንበት ስንቆም፣ ስንታገልና ጸንተን ስንፋለማቸው ብቻ ገዳዮቻችንን
እናሸንፋቸዋለን ነው ያሉት።
ወትሮም ቢሆን አሸናፊ የሚሆነው ለማሸነፍ ቆርጦ የተነሳው ነው። በፌስቡክ ጫጫታ የሚቀየርና ሊያጥር የሚችል የመከራ ጊዜ
የለም። የተሳሳተ የትግል አማራጭ በመከተልም አሸናፊ መሆን አይቻልም። የምናሸንፈው በአንድነት ስንቆም ብቻ ነው። ጎንደር
ጎጃምን ፣ ጎጃም ሽዋን ፣ ሽዋ ወሎን ሲያቅፍ እናሸንፋለን። አሸናፊነታችን ከአንድነታችን ነው። የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ያሸነፉት
ይዘውት በተነሱት ቅዱስ ዓላማ ላይ ልዩነት ስላልነበራቸው መሆኑን አንስተዋል።
ኅብረታችን የይሁዳ ባህርይ ቢፈታተነውም እንደምናሸንፍ መጠራጠር የለብንም፤ ሀናና ቀያፋን የመሳሰሉ አጓጉል ሽማግሌዎች
ቢገዳደሩንም ከፍታችንን አያስቀሩትም፤ እንደመጻጉዕ አይነት ከሀዲዎች ህልውናችንን ቢፈታተኑትም ከማሸነፍ አያስቆሙንም፤
ስቅላታችንን ማስቀረት የማይችሉ እንደፒላጦስ ያሉ ምንደኞች ከደሙ ንፁህ ነን እያሉ የሚላገዱብን አስመሳዮች ከመንገዳችን
ላይ ቢቆሙም እኛ አንድ ከሆንን ማሸነፋችን ሳይታለም የተፈታ መሆኑን ነው የተናገሩት።
አቶ አብርሃም በመልዕክታቸው ከትንሳኤ በፊት ስቅለት እንዳለ አምነን ኅብረታችንን እናጠናክር፤ በሚደርስብን መከራ፣
በሚፈጸምብን ግፍ ምክንያት ቅስማችን ቢሰበር እንኳ በፍጹም ተስፋ መቁረጥ የለብንም፤ በማንኛውም ጊዜና በማንኛውም ሁኔታ
የምናሸንፍ ፣ ለማንኛውም ጠላት የማንበረከክ ሕዝብ ነን፤ ደጋግመን እንደምንለው በመጨረሻም የምናሸንፈው እኛ ነን ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleሰበር ዜና
Next article“ሕወሓት እና ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የውሳኔ ሐሳብ መቅረቡ በሀገር ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ ሚና ይኖረዋል” የሕግ ባለሙያ

Source link

Related posts

በኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ የተፈጠረውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እየተሰራ ነው

admin

የፖለቲካ ፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ከጥላቻ ንግግር በጸዳ መልኩ መሆን እንዳለበት የሕግ ምሁር ገለጹ፡፡

admin

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለአካባቢው ማኀበረሰብ የተለያዩ ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በመስጠት አለኝታነቱን እያሳየ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡

admin