68.25 F
Washington DC
May 13, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“የትንሣኤን ለሰው ልጆች ከመከራ የመነሳት የተስፋ ምልክት መነሻ በማድረግ ያጋጠሙ የውስጥና የውጭ ችግሮችን በአሸናፊነትና በጽናት ለመሻገር መነሳት ይኖርብናል” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር

“የትንሣኤን ለሰው ልጆች ከመከራ የመነሳት የተስፋ ምልክት መነሻ በማድረግ ያጋጠሙ የውስጥና የውጭ ችግሮችን በአሸናፊነትና በጽናት ለመሻገር መነሳት ይኖርብናል” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈዋል፡፡

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዩች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ!

የትንሣኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዩች ዘንድ በልዩ ድምቀት የሚከበር በዓል ሲሆን እየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ሃጢአት ማስተሰርያ ሲል፣ ክቡር ደሙን አፍሦ፣ የስቃይን ሞት ሞቶልን፣ ተቀብሮ፣ በሦስተኛው ቀን ደግሞ፣ ሞትን ድል በመንሳት፣ ከሙታን ሁሉ በኩር ሆኖ፣ የተነሳበትን ቀን በማሰብ የሚከበር ልዩ ቀን ነው።

ትንሣኤ ለሰው ልጆች ሁሉ ከመከራ የመነሳት የተስፋ ምልክት ተደርጎ የሚወሰድ በመሆኑ እኛም አሁን የገጠሙንን የውስጥና የውጭ ችግሮች ተቋቁመን ፈተናወቹን ሁሉ በአሸናፊነት ተሻግረን ወደ ከፍታው የምንነሳ ህዝቦች መሆናችንን አምነን ፈተናወችን በፅናት ለመሻገር መነሳት ይኖርብናል።

የምንገኝበት ወቅት እንደ ሀገርም ይሁን እንደ ክልላችን ተስፋም ስጋትም መሳ ለመሳ ሁነው የሚታይበት ወቅት በመሆኑ የስጋት ድባቡን እየታገልን የተስፋ ብርሃኑን አለምልመን በአሸናፊነት የመውጣታችን ጉዳይ የፍላጎት ብቻ ሳይሆን የህልውናችንም ጉዳይ ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው ነው።

በክልላችን የተረጋገጠዉ አስተማማኝ ሰላም በአሁኑ ሰዓት የስጋት ድባብ እንዲያንዣብብበት ፅንፈኛ ቡድኖች ፣ የውስጥና የውጭ ኀይሎች ተቀናጅተው የሰላሙን አየር ሊበክሉት ሙከራ እያደረጉበት ይገኛል። በተለይም ወቅቱ የምርጫ ወቅት እንደመሆኑ መጠን ይህንን አጋጣሚ እንደመልካም እድል ሊጠቀሙበት ያሰፈሰፉ ኀይሎች በየአቅጣጫው እየሠሩ ይገኛሉ። በመሆኑም ከውስጥ የሚመነጨውን ተጋላጭነታችን በማክሰም እና አንድነታችንን ከመቸዉም ጊዜ በላይ በማጠናከር ልክ እንደትናንቱ ሁሉ ጠላቶቻችንን በአንድነት ቁመን ልንታገላቸውና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ልንረባረብ ይገባል።

የአማራን ህዝብ በጠላትነት የፈረጁ ኀይሎች በሕዝባችን ላይ የከፈቱትን መጠነ ሰፊ ጥቃት ልንላከል ከሆነ ጠላቶቻችን በቀደዱልን ቦይ ልንፈስላቸውና ክልላችንን እየበጠበጥን የነሱን አላማ በማሳካት ሳይሆን የጥፋት ኀይሎችን ሴራ ለማፈራረስ ጠንካራ እና ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ ሊሆን ይገባል እላለሁ። የክልላችን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል መስተዳደሮችና የጸጥታ ኀይሎች ጋር በትብብር እየሰራን እንገኛለን።

በመሆኑም የዘንድሮውን የትንሣኤ በዓል ስናከብር አንድም በጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሰማእታት ቤተሰቦች እንዲሁም በየአካባቢው በተከሰቱ ማንነት ተኮር ጥቃቶች የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ከጎናቸው መሆናችንን በማሳየትና በመደገፍ በተጨማሪም ለሕግ የበላይነትና የክልላችን ሰላም እንዲረጋገጥ የበኩላችን ድርሻ በመወጣት ሊሆን ይገባል።

የገጠሙንን ፈተናዎች ሁሉ በፅናት እንሻገራቸዋለን!!!

ፈጣሪ ኢትዩጵያንና ልጆቿን ይባርክ!!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ለዓመታት የጨለመች በወራት አበራች። | የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት

admin

ምርጫ ቦርድ እውቅና ሰጠ፡፡ | የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት

admin

የኢትዮጵያ ሳምንት ሊከበር ነው፡፡ | አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

admin