76.87 F
Washington DC
June 20, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“የትናንት ጠላቶች፣ ከውጭ ኀይሎች ጋር በመተባበር አማራን አንገት ለማስደፋት እየሠሩ ነው” የርእሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ደሳለኝ አስራደ

“የትናንት ጠላቶች፣ ከውጭ ኀይሎች ጋር በመተባበር አማራን አንገት ለማስደፋት እየሠሩ ነው” የርእሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ደሳለኝ አስራደ

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ የምስጋና እና የእውቅና ዝግጅት እየተደረገ ነው። የእውቅና ዝግጅቱ እየተደረገ የሚገኘው በወፍ አርግፍ ከተማ ነው። በምስጋና እና እውቅና ዝግጅት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርእስ መስተዳድር ልዩ አማካሪ ደሳለኝ አስራደ “ያ ክፉ ቀን አልፏል፣ ዛሬ ሌላ ቀን ነው” ብለዋል።

በሕወሃት ዘመን ግፍን መቀበል እንጂ መናገር አይቻልም ነበር ያሉት ልዩ አማካሪው ያ ዘመን አልፎ ለመነጋገር መገናኘት ቀላል ክብር የሚሰጠው አይደለም ነው ያሉት። መላው የአማራ ሕዝብ በወልቃይት ጠገዴ ሕመም ሲታመም ኖሯል፣ ታግሏልም ብለዋል። ለወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ድምፅ የሆኑ ሁሉ ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተንገላተዋልም ነው ያሉት፡፡

ዛሬ ለተገኘው ድል ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የተደረገው ተጋድሎ ምክንያት መሆኑን አንስተዋል። የሀገሬው ሕዝብ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና መከላከያ ለተገኘው ድል ዋጋ እንደከፈለ ገልጸዋል። ፈተናዎችን ለማለፍ ቃል ኪዳን ማሰር፣ ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከርና ዝግጁ መ‘ን እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በርካታ ፈተናዎች እየገጠሟት ነው ያሉት አቶ ደሳለኝ በተለይም የትናንት ጠላቶች፣ ከውጭ ኀይሎች ጋር በመተባበር የአማራን ሕዝብ ክብር ለመቀነስና የአማራን አንገት ለማስደፋት የተለያዩ ሥራዎችን እየጸሠሩ ነው ብለዋል። የዘወትር ጥላቶች ከወትሮው በተለዬ በመደራጄት ነገር እየጎነጎኑ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

በማንነት ላይ የተመሠረተ ግድያና መፈናቀል አሁንም አልቆመም፣ ሕወሃት ተወገደ እንጂ የዘራው ክፉ ዘር ገና አልተነቀለም። የጥላቻ ክፉ ዘር አለ፣ በቀልተኝነት አለ፣ አሸባሪው ቡድን መጠራጠርን አለመተማመንን ሰርቷል ነው ያሉት። ሕወሃት በሠራው ሥራ የአማራ ሕዝብ አሁን ድረስ ዋጋ እየከፈለ ነውም ብለዋል።

የውጭ ኀይሎች ሳይቀሩ ኢትዮጵያ የምትዳከምበትን አጀንዳ ይዘው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸዋል። ከአሜሪካ መንግሥት የተሠማው መግለጫ የሕወሃት ተባባሪ መሆናቸውን ያሳየ ሲሆን ይህም እጅግ ጠንካራ ሀገር እንዲፈጠር የሚደርግ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ጠላቶች ከሚያመጡት ክፋት ለመዳን ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር አስፈላጊ ነውም ብለዋል። አንድነትን የሚሸረሽር ማናቸውንም አሉባልታና ወሬ መቀበል እንደማይገባም አስገንዝበዋል። በመከራው ዘመን ያልተሸነፍነው በነፃነት ጊዜ በወሬ አንበረከክም ብለዋል። ትልቁን ነገር እስክናሳካ ድረስ አንድነትን ማጠናከርና ዘመኑን የዋጄ የትግል ሥልት መከተል እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

በወልቃይት ጠገዴ በጠቅላላው በአማራ ሕዝብ ላይ የደረሰውን በደል መናገርና መግለጽ ይገባልም ነው ያሉት። “በደላችን በግልፅ ስላልተናገርን ነው ተበዳይ ሆነን ሳለ በዳይ የተባልነው፣ ተወረን ሳለ ወራሪ የተባል ነው” ነው ያሉት። የደረሰብንን በደል ለዓለም ከማሳወቅ ባለፈ ሕዝቡ ፊቱን ወደ ልማት ማዞር እንደሚገባውም አሳስበዋል።

የወልቃይት ሕዝብ የተነፈገውን የልማት እጦት መመለስ እንዳለበትም ጠቁመዋል። ነፃነት እንዲመጣ መስዋእትነት ለከፈሉ ሁሉ ምስጋና እንደሚገባቸውም በአጽኖት ገልጸዋል። በመጨረሻም ጠላቶቻችን አይተኙም እኛም ድል ማድረጋችን አይቀርም ነው ያሉት።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

በትግራይ ክልል ‘ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም’ የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት አስበው ነው – ዶክተር ሙሉ ነጋ

admin

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ

admin

በጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት እያደረገ ይገኛል

admin