70.74 F
Washington DC
May 14, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 10ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል” የአማራ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት“የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 10ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል” የአማራ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ
ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 12/2013 ዓ.ም (አብመድ) “ዓለም አቀፋዊ ዲፕሎማሲውን በሚያጎላ እና ሀገራዊ ትኩረቱን በሚያጠናክር
መልኩ” የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 10ኛ ዓመት ግንባታን ለማክበር መዘጋጀቱን የአማራ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ
ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ መነሻውን ከምሥራቅ አፍሪካዊቱ ቀደምት ሀገር ኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል
ያደረገው የዓለማችን ረጂሙ የዓባይ ወንዝ 6 ሺህ 671 ኪሎ ሜትር በመጓዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚው ነው፡፡ በወቅቱ
የዓለማችን የውኃ ጂኦ ፖለቲካል ሰጣ ገባ ግንባር ቀደም አጀንዳ የሆነው የዓባይ ወንዝ 86 በመቶ የሚሆነው የውኃ ድርሻም
የሚገኘው ምንጩ ከሆነችው ኢትዮጵያ ሰሜናዊ ከፍተኛ ቦታዎች ነው፡፡
ዓባይ 76 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ዓመታዊ ውኃ ለምትለግሰው ኢትዮጵያ ወንዝ ብቻ ሳይሆን የማንነቷም መገለጫ ነው፡፡ ከተከዜ
እስከ ዲንደር፣ ከባሮ እስከ ጣና፣ ከዴዴሳ እስከ ዳቦስ፣ ከበለስ እስከ በሽሎ፣ ከጃማ እስከ ሙገር እና ከዲንደር እስከ ጉደር ያሉ
ተፋሰሶች ዓባይ የቀጣናውን ምድር ያረሰርሳል፡፡ ለዘመናት የባዕዳንን ምድረ በዳ ገነት ሲያደርግ ለአብራኩ ክፋይ ኢትዮጵያ ግን
ከእንጉርጉሮ የዘለለ ሲሳይ አልነበረውም፡፡ የቀኝ ገዥ ምዕራባዊያንን ሸውራራ ሰንኮፍ ነቅለው እና የአልጠግብ ባዮቹን የታችኞቹን
የተፋሰሱን ሀገራት ሴራ ተቋቁመው ኢትዮጵያዊያን ዓባይን በራሳቸው ሃብት እና እውቀት ለሀገራቸው ልማት፤ ለጎረቤቶቻቸው
ትሩፋት ለማድረግ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የጀመሩት መጋቢት 24/2013 ዓ.ም ነበር፡፡
ኢትዮጵያዊያን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ሲጀምሩ ዓላማቸው “ፍትሐዊ የውኃ ተጠቃሚነት መርህን” መሰረት
አድርገው ነው፡፡ ምንም እንኳን እንዳለመታደል ሆኖ “ብቻችንን በልተን ብቻችሁን ሙቱ” ባዮች ቢበዙም፡፡ ዓለም አቀፋዊ ጫናን
በመርህ ተቋቁማ፣ ውጫዊ ተፅዕኖን በብስለት እያለፈች እና ውስጣዊ ችግሮቿን በትዕግስት እየተሻገረች ያለችው ኢትዮጵያ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ከተጀመረች 10ኛ ዓመት ዋዜማው ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ በ10ኛ ዓመት የግንባታው ዋዜማም
ላይ ለሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ተቃርባ፣ ለሁለት ተርባይኖች የሙከራ ጅማሮ ተዘጋጅታ እና 79 በመቶ አጠቃላይ የግንባታውን
ሂደት አጠናቃ ነው የምትገኘው፡፡
የአብመድ 10ኛውን ዓመት የግንባታ በዓል እንዴት ለማክበር ተዘጋጅታችኋል ሲል የአማራ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ
ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤትን አነጋግሯል፡፡ “ዓለም አቀፋዊ ዲፕሎማሲውን በሚያጎላ እና ሀገራዊ ትኩረቱን በሚያጠናክር መልኩ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 10ኛ ዓመት ግንባታን ለማክበር ተዘጋጅተናል” ያሉት የጽሕፈት ቤት ኀላፊው አቶ ላቀ ጥላዬ
ናቸው፡፡ በዓሉን በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር እንደተዘጋጁም ነግረውናል፡፡ እንደ ኀላፊው ገለፃ ኢትዮጵያ
በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ያላት የማይናወጥ አቋም ከመቼውም ጊዜ በላይ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግልፅ
መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ሲባል በክልሉ ባለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም አማካኝነት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በዓሉን
በተለየ ሁኔታ እንዲያከብሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡
በ10ኛ ዓመት የግንባታው ክብረ በዓል ላይ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጥናታዊ እና የምርምር ጽሑፎችን አቅርበው ይወያያሉ፤ ይህም
በየአካባቢያቸው ላለው ማኅበረሰብ የጋራ ግንዛቤ መፍጠሪያ እና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግልፀኝነት መፍጠሪያ አውድ ይሆናል
ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከክልል ተቋማት ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ባሉ የመንግሥት ተቋማት እና የግል ድርጅቶች በዓሉ
በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ የግድቡን አጠቃላይ ሂደት በትኩረት
እየተከታተሉ እንደሆነ ጽሕፈት ቤት ኀላፊው ጠቅሰዋል፡፡
አጋጣሚውን ወደ ዕድል በመቀየር የገንዘብ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ከመጋቢት 15/2013 ዓ.ም እስከ
መጋቢት 30/2013 ዓ.ም የሚዘልቅ “የቦንድ ንቅናቄ ሳምንት” ይካሄዳል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት
ባንክ እና የአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ለንቅናቄ ሳምንቱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቻቸውን አጠናቀዋል ተብሏል፡፡ የገንዘብ
ተቋማቱ ለዚሁ የንቅናቄ ዝግጅት ቅርንጫፎቻቸውን ከማዘጋጀት አልፈው በየሁነቶቹ ላይ ቦንድ ይዘው በመገኘት ሽያጭ ይፈፅማሉ፡፡
“10ኛ ዓመት የግድቡን የግንባታ ጅማሮ ስናከብር ለሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ተዘጋጅተን፣ ለሁለቱ ተርባይኖች ሙከራ ተቃርበን
እና 79 በመቶ በላይ አጠቃላይ የግንባታውን ሂደት አጠናቀን ነው” ብለዋል አቶ ላቀ፡፡ የግብጽንና ሱዳንን ተንኮል እና የዓለም
አቀፉን ማኅበረሰብ ጫና በመቋቋም ግድቡን ለማጠናቀቅ ሀገራዊ አንድነት ማጠናከር ለነገ የማይባል ተልዕኮ እንደሆነ ነው አቶ
ላቀ ያስታወቁት፡፡
የአማራ ክልል ሕዝብ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ወቅት አንስቶ 27 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የገንዘብ እና የጉልበት
ድጋፍ አድርጓል፡፡ ከዚህ ውስጥም 1 ቢሊዮን 198 ሚሊዮን 802 ሺህ ብር በላይ በቀጥታ ቦንድ እና ልገሳ ተሰብስቧል፡፡ የግድቡን
ግንባታ ዘላቂነት ለመጠበቅ የሚያስችል 26 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚገመት የተፈጥሮ ሃብት እና የተፋሰስ ልማት ሥራዎች
በሕዝቡ ጉልበት መሠራቱን ከጽሕፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleበስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ በአካባቢው ኅብረተሰብ ተሳትፎ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን የፓርኩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

Source link

Related posts

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኮሮናን በመከላከል ምርት እንዳይስተጓጎል ያደረገው ጥረት ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው – የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

admin

“ኢትዮጵያዊነት የማይደበዝዝ ይልቁንም በይበልጥ የሚደምቅና የሚፈካ የጋራ ማንነታችን ሊሆን ይገባል” ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር

admin

የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓትን ለማሻሻል የገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ ይፋ አደረገ

admin