55.85 F
Washington DC
March 3, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰሞኑን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠ ቅመው አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን በተመለከተ  ሃሰተኛ  መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው  በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ  አሳስቧል፡፡

ከዚህ በኋላ የሀሰት መረጃዎችንና አሉባልታዎችን  በማህበራዊ ትስስር ገጾች በማሰራጨት  የሀገርን ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና ለመጉዳት እንዲሁም የህዝብን ሰላምና  ደህንነት ስጋት  ላይ ለመጣል  የሚንቀሳቀሱ  አካላት ላይ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ማስረጃዎችን በማጠናቀር በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ከወዲሁ ያሳውቃል። 

ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት  በሀገር ላይ የሚቃጡ  የፀጥታና የደህንነት  ስጋቶችን በማስቀረት  ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን  ከማንኛውም ጊዜ በላይ ከሁሉም  የጸጥታና የደህንነት  ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ እንደሚገኝ መግለጫው  አመልክቷል።

በተያያዘ  ዜና የብሔራዊ መረጃ  ዩኒቨርስቲ ኮሌጅን  በኢንተለጀንስና በደህንነት መስኮች የልህቀት ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው የለውጥ ትግበራ ተጠናክሮ  እንደሚቀጥል  የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ። 

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን በተመለከተ  ሃሰተኛ  መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው  በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በአገልገሎት መሥሪያ ቤቱ ሥር  የሚገኘውን የብሄራዊ መረጃ ዩኒቨርሲቲ  ኮሌጅ የሥራ እንቅስቃሴን  በዛሬው  ዕለት ጎብኝተዋል።     

አገልገሎት መሥሪያ ቤቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የብሔራዊ  መረጃና ደህንነት አገልግሎት  ዳይሬክተር  ጀነራል  አቶ  ተመሰገን ጥሩነህ  በጉብኝታቸው ወቅት በሥልጠና ማዕከል ደረጃ የነበረው  ተቋም  ወደ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ደረጃ ማደጉ አስደሳች መሆኑን ገልፀው  ዩኒቨርስቲ  ኮሌጁ  ከዚህ በላይ  የመሥራት  እምቅ አቅም  እንዳለው ተናግረዋል።

ዩኒቨርስቲ ኮሌጁን በአፍሪካ በኢንተለጀንስና በደህንነት መስኮች የልህቀት ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው የለውጥ ትግበራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተቋሙ አመራሮች ድጋፍ እንደማይለየውም አመልክተዋል፡፡

አዲስ  አበባ  የአፍሪካና የዓለም አቀፍ ተቋማት የዲፕሎማሲ  መቀመጫ መሆኗን የጠቆሙት ዳይሬክተር ጀነራሉ፤ የብሔራዊ መረጃ ዩኒቨርሲቲ ኮሎጁ በዘርፉ የማሰልጠን አቅሙን ከፍ ወዳለ ደረጃ ካደረሰ አፍሪካውያንን  በማስልጠን በአፍሪካ የልህቅት  ማዕከል  መሆን እንደሚችልም  ጠቁመዋል።

የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁን አቅም ይበልጥ ለማሳደግ፣ ለ ማዘመንና በቴክኖሎጂ  ታግዞ  ዓለም አቀፍ ደረጃውን  ጠብቆ  ተልዕኮውን  እንዲወጣ  ለማስቻል  አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ  አስፈላጊውን  የፋይናንስና የሎጀስቲክስ ድጋፍ እያደረገ  መሆኑንና ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል  አስረድተዋል።

የብሄራዊ መረጃ ዩኒቨርሲቲ  ኮሌጅ  ባለፈው ዓመት ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በደህንነት ፣ በኢንተለጀንስ፣ በስትራቴጂክ ጥናትና በቋንቋ የትምህርት መስኮች በዲግሪና በዲፕሎማ ስልጠና ለመስጠት እውቅና ማግኘቱ ይታወሳል፡፡ (ኢ.ፕ.ድ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & EmailSource link

Related posts

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

admin

ሲዋጉና ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ዋሉ

admin

አቶ ስዩም መስፍን ፣አቶ አስመላሽ ወልደስላሴና አቶ አባይ ፀሃዬ ተደመሰሱ

admin