69.73 F
Washington DC
June 15, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የብልጽግና ፓርቲ ድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ በደብረ ታቦር ከተማ ተካሄደ።

የብልጽግና ፓርቲ ድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ በደብረ ታቦር ከተማ ተካሄደ።

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች በደብረ ታቦር ከተማ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ አካሂደዋል። የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ወንዴ መሠረት ለታዳሚዎቹ እንዳሉት ብልጽግና ውልደቱና ሂደቱ ለፍትሕ እና ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የቆመ መሆኑ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው አድርጓል።

ፓርቲው በኢትዮጵያ ተዘርቶ የነበረውን የዘረኝነት እና የፅንፈኝነት አስተሳሰብ ለሀገር አይበጅም በማለት ወንድማማችነትን በማጎልበት ዘረኝነትን ነቅሎ ለመጣል እየሠራ ሆኑንም አስታውቀዋል። ብልጽግና ኢትዮጵያ አሁን ለገጠማት ችግር ፍቱን መድኃኒቱ ወንድማማችነት ነው ብሎ እንደሚያምንም ገልጸዋል።

ፓርቲው ከስኬት እና ከስህተት በመማር በእጅ የሚጨበጥ መፍትሔ የሚሰጥ እንጂ ርዕዮት ዓለም ናፋቂ እንዳልሆነም ነው አቶ ወንዴ የገለጹት። ብልጽግናን መምረጥ ሀገርን ማስቀጠልና ለውጡን ስር እንዲሰድ ማድረግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አሜሪካ የወሰደችው ርምጃ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚዳፈርና ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም ገልጸዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ በሰልፉ ላይ እንዳሉት ኢትዮጵያ በበርካታ ችግሮች ውስጥ ተከባ ትገኛለች፤ ወዳጆቿ ጭምር እየካዷት ይባስ ብለው ክንዳቸውን ሊያሳርፉባት ከዘመናት ባለጋራዎቿ ጋር እየተባበሩባት ይገኛሉ፤ ውስጣዊ ችግሮቿም ሕዝብን እያሳዘኑ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በነዚህ ችግሮች ውስጥ ሆና ለማካሄድ እየተንቀሳቀሰች መሆኗን ነው ዋና አስተዳዳሪው የገለጹት። ምርጫ ማድረግ የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት እንዲኖር ያደርጋል፤ ለውስጥ ችግሮች እና ለውጭ ጠላቶች መድኃኒት መሆኑንም ተናግረዋል።

ምርጫውን ማድረግ ኢትዮጵያ ካንዣበበባት ችግር ውስጥ የምትወጣበት መሆኑንም አስገንዝበዋል። የውጭ ኃይሎች መንግሥት ያካሄደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ከመደገፍ ይልቅ የጥፋት ቡድኑ እንደገና እንዲያንሰራራ ለማድረግ ጫና እያሳደሩ ነው ብለዋል።

የዘመናት ባላንጣዎችና የቅርብ ወዳጅ የሆኑ ሀገራት ሳይቀር አንድነት ፈጥረው ኢትዮጵያን ለመውጋት መድረሳቸውንም ገልጸዋል።

የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግንድብ ኹለተኛ ዙር ውኃ ሙሌት ለማሰናከል ያልተደገሰ የጥፋት ድግስና ያልተሞከረ ሴራ አለመኖሩንም ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል። አቶ ቀለመወርቅ ዲሞክራሲያዊ፣ በሕዝብ ዘንድ ታማኝነት ያለው ምርጫ ለማካሄድ ኢትዮጵያ ተግታ እየተንቀሳቀሰች መሆኗንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከፈተና ወጥታ ሰላም የሰፈነባት ሀገር እንድትሆን የብልጽግና ፓርቲ የለውጥ ኃይል እየሠራ መሆኑንም አቶ ቀለመወርቅ አብራርተዋል። ሕዝቡ ድምፅ ከሰጣቸው በውስጥ ያለውን ችግር በማረም የዜጎችን ሞትና መፈናቀል አስቁመው ሁሉን በእኩል የምታስተናግድ ፍትሐዊነት የሰፈነባት ጠንካራ ኢትዮጵያን እንደሚገነቡም ተናግረዋል።

በሰልፉ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ፈንታ ማንደፍሮ (ዶክተር)፣ የኢፌዴሪ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስተሩ መላኩ አለበል፣ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሂሩት ካሳው (ዶክተር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የአነጋጋሪዋ ቃለ መጠይቅ አድራጊ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

admin

“በሞታችን የሚያተርፉ እና በቁስላችን የሚነግዱ ሕሊና ቢሶች በዝተዋል፤ ሕዝቡ ነቅቶ ኢትዮጵያን ሊያድንና ወደ ቀደመዉ ክብሯ ሊመልስ ይገባል” የባሕር ዳር የሰላም ልዑክ

admin

የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እና የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ስለሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ መጠንቀቅ ያስፈልጋል- ኢንስቲትዩቱ

admin