59.29 F
Washington DC
April 21, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ መግባቱ የሱዳን ሕዝብ ፍላጎት ሳይሆን የሌላ አካል አጀንዳ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።

የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ መግባቱ የሱዳን ሕዝብ ፍላጎት ሳይሆን የሌላ አካል አጀንዳ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።

ባሕር ዳር፡ የካቲት 30/2013 ዓ.ም (አብመድ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እንደገለጹት፤ ሱዳንና ኢትዮጵያ በወዳጅነታቸው የሚታወቁ ሀገራት ናቸው። አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ እና የሱዳን ሕዝቦች ወዳጅ መሆናቸው ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም ብለዋል።

የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ መግባቱ ፣ ከሱዳናውያን ፍላጎት የመነጨ ሳይሆን የሌላ አካል አጀንዳ ይዞ ከመንቀሳቀስ የመነጨ ስህተት እንደሆነ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የሕግ ማስከበር እርምጃ ላይ በነበረችበት ወቅት የሱዳን መንግሥት ድንበር ጥሶ መግባቱ በእርግጠኛነት ትክክል እንዳልሆነ መናገር ይቻላል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በሰከነ መንገድ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ፍላጎት እንዳላት ያመለከቱት አፈ ጉባኤው ፣ ሱዳናውያን ይህን እድል ሊጠቀሙበት እንደሚገባ መክረዋል። ሱዳናውያን በጥሞና ረጋ ብለው የተፈጠረውን ችግር ማጤን አለባቸው። አላግባብ የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው መግባታቸው ጥፋት ቢሆንም ቀድሞ ወደነበሩበት ቦታ ተመልሰው ወደ ድርድር መግባት እንደሚችሉ አመልክተዋል።

አሁንም ችግሩን በውይይት መፍታት የሚቻልበት እድል መኖሩን ያስታወቁት አቶ ታገሰ ፣ ከዚህ ቀደም ቢሆን በኢትዮጵያ ከወዳጅ እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር በመመካከር ለችግሮች መፍትሄ የማምጣት ልምድ አላት። ይህን የኢትዮጵያ አቋም ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ለማሳወቅ ጥረት መደረጉንም አመልክተዋል።

ከሱዳን ጋር ያለውን ጉዳይ በሚመለከት እንደ ፓርላማ በተገኙት አጋጣሚዎች ሁሉ ለማሳወቅ ጥረት እያደረግን ነው ያሉት አቶ ታገሰ ፣ ‹‹ከተለያዩ ሚሲዮኖች እና አምባሳደሮች ጋር ስንነጋገርም ሆነ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ስንወያይ የምናነሳው ሱዳን ቀደም ብሎ ችግር ውስጥ በገባችባቸው ጊዜያት የኢትዮጵያ መንግሥት በብዙ መንገድ ሀገሪቷ እንድትረጋጋ እና የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ከፍተኛ ጥረት መደረጉ ነው ብለዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አንስቶ በርካታ ዲፕሎማቶች ባደረጉት ጥረት በሱዳን የሽግግር መንግሥት ተቋቁሞ ወደመረጋጋት እንድትሸጋገር ተደርጓል። ይህን ያላገናዘበ ጥፋት የሱዳን መንግሥት መፈጸሙን አመልክተዋል። የሱዳን መንግሥት የሌላ አካል አጀንዳ ከማስፈፀም እንዲቆጠብ መልዕክቶችን እንደፓርላማ መተላለፋቸውን መግለጻቸውን ኢትዮ ፕረስ ዘግቧል።

በፓርላማ ዲፕሎማሲ ጉዳዩን ለዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ለማሳወቅ ተሞክሯል፤ አሁንም ለማሳወቅ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች ጋር ጥሩ ግንኙነት በመፈጠሩ የመረጃ ልውውጥ በመደረግ ላይ ነው።

ከሱዳን ጋር በተያያዘ ግን ሀገሪቷ በአሁኑ ወቅት የሽግግር መንግሥት ላይ በመሆኗ እና ፓርላማዋ ስለተበተነ ከሱዳን ፓርላማ አባላት ጋር ግንኙነት ለማድረግ እና ችግሮች ወደሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥረት ማድረግ አልተቻለም ብለዋል።

እንደ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ከሆነ፤ የህዳሴ ግድብ በተመለከተ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር በተያያዘ ያለውን ጉዳይ በተመለከተ የፓርላማ ዲፕሎማሲ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም ቦታው ላይ ጭምር በመሄድ ክትትል ያደርጋሉ። የሚገኘውን መረጃም ለፓርላማ ዲፕሎማሲ ሥራ ጥቅም ላይ ይውላል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

እንንቃ!!! – በህይወት አበበ መኳንንት | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

admin

በትግራይ ክልል ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ተሰዎች እርዳታ ለማቅረብ በቂ ዝግጅት ተደርጓል – የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን 

admin

አገር አቀፍ የማኅበረሰብ ተኮር የምክክር መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

admin