49.28 F
Washington DC
February 26, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የሱዳን ጦር የሦስተኛ ወገን ፍላጎት ለማሳካት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

የሱዳን ጦር የሦስተኛ ወገን ፍላጎት ለማሳካት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

ባሕር ዳር: የካቲት 12/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብን በተመለከተ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል፡፡

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን የድንበር ጉዳይ አስመልክቶ የሱዳን መንግሥት ጠብአጫሪነት እንቅስቃሴውን በጥብቅ ኮንኗል፡፡

ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚነሳ ማንኛውም ግጭት ከፍተኛ የሆነ ቀጣናዊ ጉዳትን የሚያስከትል እና የሁለቱን ሕዝቦች ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብላ ታምናለች ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡

በሱዳን መንግሥት ወታደራዊ ክንፍ እየተደረገ ግጭት የመቀስቀስ ፍላጎት የሱዳንን ሕዝብ ዋጋ የሚያስከፍል እና የሦስተኛ ወገንን ፍላጎት ብቻ ለማሳካት እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት በፅኑ ያምናል ብሏል፡፡

መግለጫው ሁለቱ መንግሥታት ማናቸውንም የድንበር ይገባኛል እና የማካለል ጥያቄዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል በቂ ስልቶች እንዳሏቸውም ገልጿል፡፡ ሆኖም የሱዳን ጦር (እ.ኤ.አ.) በኅዳር 2020 ኢትዮጵያን በመውረር ዓለም አቀፍ የሕግ መሰረታዊ መርሆችን መጣሱን ጠቅሷል፡፡

የጠብ አጫሪነት ድርጊቱ በሁለቱ መንግሥታት በድንበር አካባቢ ያሉ ዜጎች እንዳይፈናቀሉ እና ጉዳዩ ባለበት ሁኔታ እንዲቆይ የሚደነግግውን የሀገራቱን የድንበር ስምምነት የጣሰ እንደሆነም ገልጿል፡፡ የጋራ ድንበሩን እንደገና የማካለል ሥራን ለማጠናቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሲሠሩ የነበሩትን የጋራ የድንበር ኮሚቴዎች ጥረት በሱዳን በኩል እንዲስተጓጎል እና ዋጋ እንዲያጣ እየተደረገ ነው ብሏል መግለጫው፡፡

በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ካለው የወዳጅነት እና የትብብር መንፈስ በተቃራኒ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት ንብረቶችን ዘርፏል፣ ካምፖችን አቃጠሏል፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በማጥቃት ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል፣ የተለቀቁ ወታደራዊ ካምፖችን ይዟል ብሏል፡፡

እንደ ሚኒስቴሩ መግለጫ ሱዳን በመሬት ላይ ያሉ እውነታዎችን በተሳሳተ መንገድ በማቅረብ ኢትዮጵያን እየወነጀለች ነው፤ ራሷ ወርራ እንደተወረረች በማስመሰል ከተጠያቂነት ለመሸሽ እና በወረራው ለመቀጠል በኢትዮጵያ ላይ የተሳሳተ መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ እያካሄደች ነው፡፡

ለሱዳን ተስፋፊ እና ጠብአጫሪ እንቅስቃሴዎች ኢትዮጵያ የበዛ ትዕግስትን አሳይታለች ብሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በመግለጫው፡፡

ራስን የመከላከል ሕጋዊ መብቷን ከመጠቀም ተቆጥባ የነበረች ከመሆኗም በላይ አሁን ባለው ነባር ወሰን ዙሪያ ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት መወሰኗን በተደጋጋሚ እየገለጸች ነው ብሏል፡፡

ጉዳዩን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት የፖለቲካ ፍቃደኝነት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች የቆየ የወንድማማችነት ግንኙነት ላይ ጥብቅ እምነት እንዳላት አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያና የሱዳን ሕዝቦችን ወደ አላስፈላጊ ጦርነት ለማስገባት በሱዳን ጦር እየተደረገ ያለው ጠብአጫሪነት የዜጎችን ብሎም የቀጣናውን ሠላም፣ መረጋጋትና ልማት የሚያደፈርስ ከባድ ስህተት ነው ብሏል፡፡

የሱዳን ጦር የሦስተኛ ወገን ፍላጎት ለማሳካት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንዲያስቆም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሱዳን ሕዝብ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የሱዳን መንግሥት ከጠብ አጫሪነት ድርጊቱ ታቅቦ የድንበር ጉዳዮችን በሠላማዊ መንገድ ብቻ ለመፍታት እንዲንቀሳቀስ እንዲመክሩ ለአፍሪካ ሀገራትም ጥሪ ቀርቧል፡፡ ሁኔታውን በሚገባ በመረዳት ከፍተኛ ትዕግስት እያሳየ ላለው የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥት ምስጋና አቅርቧል፡፡

ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በየማነብርሃን ጌታቸው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Amhara Mass Media Agency ®

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት

Source link

Related posts

የሃይማኖት ተቋማት ስለሰላም ፣አንድነት እና መቻቻል ከማስተማር ባለፈ በማህበረሰባዊ ልማት ላይ እያደረጉ ያለውን ተሳትፎ በይበልጥ ተቀራርበው ሊሰሩ ይገባል- ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

admin

የኢትዮጵያና ሱዳንን የድንበር ጉዳይ መፍታት የሚቻለው አገራቱ ባቋቋሟቸው መዋቅሮች ብቻ መሆኑ ተገለጸ

admin

በአማራ ክልል ውስብስብ መሬት ነክ ችግሮችን በቀላሉ ለመምራት፣ ሕገወጥነትን ለመከላከልና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሠራ መሆኑን ኤጄንሲው አስታወቀ፡፡

admin