71.98 F
Washington DC
May 17, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የሰላም ጥሪ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች – ሽማግሌው ከሁስተን ቴክሳስ | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

 

peace
peace

እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ሁሉ የፈጠረው ከአንድ አባት ከአዳም ነበር።ሔዋን እንኳን የተሠራችው ከአዳም በተወሰደ አንዲት አጥንት ነበር።ስለሆነም  በተፈጥሮ ሰው ሁሉ እኩል ነው።  አንዱ ከሌላው አይበልጥም አያንስም።እግዚአብሔር አምላክ ሰማይና ምድርን የፈጠርው ከሁሉም በፊት በመሆኑ፣ ሰው እንኳን የተሠራው ከመሬት በተገኘ አፈር ነው።ቋንቋ መግባቢያ ሲሆን፣ የኖህ ልጆች ይግባቡ የነበረው በአንድ ቋንቋ ነበር። ቋንቋቸው የተደበላለቀው፣በጥበባቸው ወደ ከእግዚአብሔር መንግሥት ለመድረስ  ፈልገው የባቢሎንን ግንብ በሠሩ ጊዜ ነበር።ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ነው።በአዲስ ኪዳንም መንፈስ ቅዱስ በጌታ ደቀመዛሙርት ላይ በወረደ ጊዜ ትንቢት የተናገሩት በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ነበር።

ስለዚህም ቋንቋና ብሔር  ከእኛ ዕውቂያና ፈቃድ ወጭ፣ በተፈጥሮ ሂደት ውስጥ የተከሰቱ በመሆናቸው እንዳሉ እንቀበላለን እንጂ፣መርጠን ጠፍጥፈን የምንሠራቸው አይደሉም። ሆኖም ሰይጣን ክፉ ነውና የሰው ልጆችን ፈቃድ በማጣመም ከፈጣሪ አምላኩ ፈቃድ ለመለየት ሌት ተቀን ይጥራል።ለዚህም ነው ቃየንን በቅናት አስቶ ወንድሙን አቤልን እንዲገድልና እንዲረገም ያደረገው።በመሆኑም ሰይጣን የሰው  ልጆች ሁሉ የዘር ጠላት በመሆኑ፣ እነሆ  እኛንም በትዕቢት፣ በቅናትና በምቀኝነት ሞልቶ ከእግዚአብሔር ፈቃድ በመውጣት እርስ በርስ እያፋጀን ይገኛል።

አምላካችን እግዚአብሔር  ፈቃዱን ለኖኅና ለልጆቹ ሲገልጥ “ሰውን የገደለ ሁሉ ስለሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፣የሟቹን ሰው ደም ከገዳዩ፣ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ” ብሏል።ስለዚህም ነው አንበጣና በሽታ ሰዶ፣ተቃዋሚ እያበዛ ተመለሱ በማለት እየገሰጸን ያለው።ይህን ግሣጼውን ሰምተን በንስሓ ካልተመላስን ደግሞ ምሳር በዛፎቹ ሥር ተቀምጧል ዛፎቹም ተቆርጠው ለእሳት ይጣላሉ።

የነነዌ ሰዎች የነቢዩ ዮናስን ማስጠንቀቂያ ስምተው ንስሓ በመግባት ከፈጣሪ ቁጣ እንደ ተመለሱ ሁሉ፣እኛም የፈጣሪ አምላካችንን ፈቃድ መተላለፋችን ገብቶን የንጹሓንን ደም በከንቱ ከማፍሰስ መታቀብ ይኖርብናል። የወሎ ሕዝብ በረሃብ ሲረግፍ፣ በአዲስ አበባ ከተማ መኳንንቱና ካህናቱ፤ የንጉሡን ሰማንኛ የልደት በአል በማክበር፣እንጸባራቂው ኮከብ፣ ጸሐዩ ንጉሣችን እያሉ ያዋድሱ፣ ጮማ ይቆርጡ፣ውስኪ ይራጩ ነበር። ይህ ግን ለአማትም አልዘለቀም፣ወታደራዊ ምንግሥት ሥልጣን ጨበጠና መቃብራቸው እንኳን አልተገኘም።

የደርግም ዕጣ ፈንታ ከእነሩስ አልተሻለም በእሥራት፣ በረሃብና በስደት  ማቀቁ እንጂ፣  ኢሕአዴግ  እንዲሁ በሕዝባችን ላይ ብዙ ተቀማጥሏል፣ ዛሬ ደግሞ ያንኑ የዘራውን በማጨድ ላይ ይገኛል።እግዚአብሔ ጻድቅ ፈርዱም ትክክል ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ሁሉ አንዱ ከሌላው ሳይበልጥና ሳያንስ ተስማምተው ፈጣሪ በሰጣቸው ጸጋ በሰላም ሊጥቀሙ ይገባል።መሬት እንደ ሆን እኛን ትበላለች እንጂ፣ እኛ በልተን እንጨርሳትም።ሕዝባችን ዛሬ አንድ መቶ ሚሊየን የሆነው ይህ ትውልድ ሳያልፍ ሁለት መቶ ሚሊየን ይሆናል።በዚያም ሂደት የብሔርም ሆነ የቋንቋ ጥያቄዎች ሁሉ ተገቢውን መፍትሔ ያገኛሉ።እስከዚያ ድረስ ግን ሁላችንም መታገስ ይገባላል።

ስለዚህም ሁሉም ራሱን ይመርምር፣  በእግዚአብሔር ፊት ራሱን ዝቅ አድርጎ ለፈጸመው ጥፋት ንስሓ ይገባ፣ማንም በእግዚአብሔር ፊት ጻዲቅ የለም፣ጽድቃችን እንደ መርገም ጨርቅ የረከሰ ነው።ከፈጣሪ አምላካችን ምሕረትን ለማግኘት ሕዝባችን ሁሉ ባለባት አካባቢ እርስ በርሱ ይታረቅ። የታሠሩ ይፈቱ፣ከምርጫው የወጡ ይመለሱ። የምርጫ ቅስቀሳ ይብቃ።መከላከያ ወደ ካምቡ ይመለስ፣ሕዝቡ የፈቀደውን እጩ ራሱ ይምረጥ፣በትግራይ ቀደም ሲል የተካሔደ የሕዝቡ ምርጫ ይከበር።በተከታዩ ምርጫ የተመረጡ የህዝብ ተወካዮች፣ከሁሉ በፊት ሕገ መንግሥቱንም ሆነ ሥርዓቱን እንደገና ገምግመው ለውሳኔ ሕዝብ ያቅርቡ።የሕዝቡም ውሳኔ ይከበር።እስከዚያው ድረስ ያለው መንግሥት ቀድሞ በነበረው መልኩ በሥልጣን ላይ ይቆይ።በትግራይ ከሥልጣን  ለተባረሩት ምሕረት ተደርጎ ቀድሞ ያገኙት የነበረው ደመወዝ ይከፈል።

ይህ ከሆነ እግዚአብሔር ይታረቀናል፣ሰላም ወዳድ ሕዝቦች ሁሉ ከጎናችን ይሰለፋሉ። ራሃብ ይወገዳል።ሰላም ሰፍኖ አገራችን በልጆቿ ሕብረት አብባና ደምቃ ለዘላልም ትኖራለች፡፡

ሽማግሌው ነኝ ከሁስተን ቴክሳስ።

 

Source link

Related posts

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል ስራ የተመደበ ገንዘብ ያለአግባብ ጥቅም ላይ ያዋሉ ሀላፊዎች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

admin

በምን እንግባባ .??? – መሰረት ተስፉ | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

admin

ቦርዱ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ( ኦነግ) የተከናወነው ጠቅላላ ጉባኤ ተቀባይነት እንደሌለው አስታወቀ

admin