63.7 F
Washington DC
June 17, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“የሞጣ ከተማ ሕዝብ አረፋ እና ልደትን፣ ኢድ እና ትንሣኤን በጋራ የሚያከብር ሕዝብ ነው” ርዕሰ ደብር አፈወርቅ መኮንን

“የሞጣ ከተማ ሕዝብ አረፋ እና ልደትን፣ ኢድ እና ትንሣኤን በጋራ የሚያከብር ሕዝብ ነው” ርዕሰ ደብር አፈወርቅ መኮንን

“ኢትዮጵያ እንደዛሬ ሳይሆን እስልምና በተገፋበት ወቅት በዚያ ክፉ ዘመን እንኳ ሃይማኖቱን በክብር ተቀብላ የራሷ ያደረገች ሀገር ናት” ሼህ አደም ኢብራሂም

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ለዘመናት በአብሮነት ለዘለቁት የሞጣ ከተማ ነዋሪዎች ታኅሣሥ 10/2012 ዓ.ም በጎ የምትባል ቀን አልነበረችም። ግጭትና ጥላቻ ጠማቂዎች፤ ልዩነት አቀንቃኞች በማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ተለያይቶ የማያውቀውን የሞጣ ከተማ ነዋሪ ስንጥቅ ሊፈጥሩለት ሞከሩ።

እኩይ ኃይሎቹ ያጠፉት ቢበዛም፣ የሄዱበት ርቀት ተገማች ባይሆንም በፈለጉት ልክ ግን የፈለጉት አልሆነም። የእምነት ተቋማት ቢጎዱም፣ የንግድ ማዕከላት ቢነዱም የከተማዋ ነዋሪዎች በተፈጠረው ሁኔታ ቢከፉም ነገሮችን ወደነበሩበት ለመመለስ ጊዜ አልፈጀባቸውም።

የከተማዋ ነዋሪዎች ዛሬ በከተማቸው “ሕብር እና ፍቅር በሰባቱ ዋርካ ስር” በሚል መሪ መልእክት ሕዝባዊ ውይይት አካሂደዋል።

በሞጣ ከተማ የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ለዘመናት አብረው የኖሩ መሆናቸውን ያወሱት ርዕሰ ደብር አፈወርቅ መኮንን በኹለቱም ሃይማኖቶች ሞጣን አንቱ ያስባሉ አባቶች እንደነበሩ ገልጸዋል።

የሞጣ ከተማ ሕዝብ አረፋ እና ልደትን፣ ኢድ እና ትንሣኤን በጋራ የሚያከብር ሕዝብ ነው ያሉት ርዕሰ ደብር አፈወርቅ መከፋፈል ለመፍጠር ዓልመው የተነሱ ኃይሎች ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ እንደዛሬ ሳይሆን እስልምና በተገፋበት ወቅት በዚያ ክፉ ዘመን እንኳ ሃይማኖቱን በክብር ተቀብላ የራሷ ያደረገች ሀገር እንደሆነች ሼህ አደም ኢብራሂም አንስተዋል።

ኢትዮጵያውያንን ከሚያለያዩ ጥቃቅን ነገሮች ይልቅ በጋራ እንዲቆሙ የሚያስገድዱ በርካታ ፈተናዎች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ ሼህ አደም “21ኛው ክፍለ ዘመን በዘር እና በሃይማኖት መከፋፈል ኢትዮጵያን አያሻግርም” ነው ያሉት።

የሃይማኖት አባቶቹ በሰጡት አስተያየት ሞጣን አሁን ካለችበት ሁኔታ በማሻሻል ወደ ሚገባት ከፍታ ለማውጣት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ እንዲሟላላቸው ጠይቀዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው – ከሞጣ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተደራሽነቱን ከማስፋት ባለፈ የዜናና ፕሮግራም አቀራረብ ማሻሻያዎችን እያከናወነ ነው።

admin

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የተሻለ የአመራር ስልጠና እንዲሰጥ የሚያደርጉ የሪፎርም ስራዎችን እያካሔደ መሆኑ ገለጸ

admin

የብሔራዊ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን የአሰራር ለውጥ ሊያደርግ ነው

admin