31.01 F
Washington DC
March 2, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የምርት ብክነትንና የጥራት መጓደልን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡

የምርት ብክነትንና የጥራት መጓደልን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የምርት ብክነትን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑን የሳሳካዋ አፍሪካ አሶሴሽን የኢትዮጵያ ፕሮግራም አስታውቋል።

ግበረ ሰናይ ድርጅቱ ከግብርና ሚኒስቴርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ላለፉት 28 ዓመታት የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጅዎችን በማቅረብ ለምርትና ምርታማነት መጨመር አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

የቴክኖሎጂው ተጠቃሚና አስተያየታቸውን ከሰጡን አርሶ አደሮች መካከል ወይዘሮ እድሜዓለም ዋነኛው እና አቶ አልማው ደሥታ እንዳሉት ቀደም ሲል እህሉ የሚወቃው በባሕላዊ መንገድ ስለሆነ ከድካም ባለፈ የሚወቃው አፈር ላይ በመሆኑ የምርት ብክነት እና ጥራት መጓደል ይከሰት ነበር፡፡ በተጨማሪም ሥራው ጊዜ ቆጣቢ ባለመሆኑ እህሉ ሳይወቃ ወቅቱን ላልጠበቀ ዝናብ እና በክምችት ወቅትም ለብክነት ይጋለጥ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ችግሩን መፍታት እንደቻሉም ተናግረዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኤክስቴንሽ ዳይሬክተር ወይዘሮ የኔነሽ ኤጉ ሳሳካዋ በኢትዮጵያ የግብርና ምርት እድገት ላይ አሻራ የጣለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው ብለዋል።

ድርጅቱ እቅዱን ከማስተዋወቅ ባሻገር ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ድረስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። ከፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር ጋር የተናበበ እቅድ አውጥቶ እየሠራ መሆኑንና እቅዱን እየገመገመ ማስተካከያ እያደረገ ነው ተብሏል።

የሳሳካዋ አፍሪካ አሶሴሽን የኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ፈንታሁን መንግሥቱ (ዶክተር) እንደተናገሩት እ.ኤ.አ በ1986 ጀምሮ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ አዳዲስ አሠራሮችን በሰርቶ ማሳያዎች በመስራትና በማስተዋወቅ ለአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እየሠሩ ነው፡፡ ፕሮግራሙ የምርት ብክነትን የሚቀንሱ አሠራሮችን በመዘርጋት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሆነም ነግረውናል።

ወጣቶችን በማደራጀት የአርሶ አደሩን የምርት ብክነት ሊቀንሱ የሚችሉ የተሻሻሉ አነስተኛና መለስተኛ እህል መውቂያ መሳሪያዎችን እና የምርት ማጠራቀሚያ ጎተራና የእህል ማዳበሪያ (ፒካስ) እያቀረቡ ነው ብለዋል። ድርጀቱ በቀጣይ ሁለት ዓመታት ዘላቂና አዳሽ የግብርና ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ አርሶ አደሮች ገበያ መር ምርት በማምረት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ይሠራል፤ በሀገራችን ለሚገነቡ የተቀናጁ አግሮ ኢንዱስትሪዎች በቂ ምርት የሚያመርቱበት ሂደትም እያመቻቸ እንደሆነ ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

“ግብርናን ግብርና ብቻ ሳይሆን ንግድ በማድረግ የሁሉንም ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይጠበቃል” ነው ያሉት ዳይሬክተሩ። አርሶ አደሮች ገበያ መር ምርት ማምረት ብቻ ሳይሆን ምርቱን የሚያመርቱበትን አካባቢ በስነ አካላዊና በስነ ሕይወታዊ ዘዴ የሚሸፍኑበት መንገድ እንደሚሠራም አስታውቀዋል። ዶክተር ፈንታሁን እንዳሉት ግብርና ትርፍ ማምረት ብቻ ሳይሆን ያመረቱትን ምርት ሳይባክን ለተገቢው ዓላማ ማዋል፣ የሚመረትበትን አካባቢ በመንከባከብ ብዝሀ ሕይወትን ማስቀጠልና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆን አለበት።

ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ከግብርና ሚንስቴርና ከባለድርሻ አካላት ጋር በ2013 ዓ.ም እና በ2014 ዓ.ም እቅድ ላይ በባሕር ዳር ከተማ እየመከረ ነው።

ዘጋቢ:- ትርንጎ ይፍሩ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ለመተከል ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ።

admin

ባለሃብቶች ለተፈናቀሉ እና ዕርዳታ ለሚሹ ወገኖች የጀመሩትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ተጠየቀ

admin

“የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር ለሀገር ብልጽግና ቁልፍ ሚና አለው” የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል

admin