56.68 F
Washington DC
April 21, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የማኀበረሰቡ የግንዛቤ እጥረትና የመሰረተ ልማት ችግሮች ነፍሰጡር እናቶች በቤታቸው ወልደው ለችግር እንዲጋለጡ ምክንያት መሆናቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡

የማኀበረሰቡ የግንዛቤ እጥረትና የመሰረተ ልማት ችግሮች ነፍሰጡር እናቶች በቤታቸው ወልደው ለችግር እንዲጋለጡ ምክንያት መሆናቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) ወይዘሮ አገሬ ወርቁ በባሶ ሊበን ወረዳ የአራቱ አምባ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ የወሊድ ጊዜአቸው በመቃረቡ የጁቤ ጤና ጣቢያ ላይ ክትትል እየተደረገላቸው ነው፡፡ እንደ ወይዘሮ አገሬ ገለጻ የሚኖሩበት አካባቢ ለትራንስፖርት ምቹ ባለመሆኑ ጤና ጣቢያው ላይ እንዲቆዩ መገደዳቸውን ነግረውናል፡፡ በጤና ጣቢያው የተሻለ አገልግሎት እያገኙ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በባሶ ሊበን ወረዳ የየጁቤ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ላቀ እንዳሉት በጤና ጣቢያው ስር ዘጠኝ ጤና ኬላዎች በክላስተር ተደራጅተዋል፡፡ እነዚህን ጤና ኬላዎች በማጠናከር እናቶች ጤና ጣቢያ መጥተው እንዲወልዱ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የእናቶችን የልማት ቡድን ተጠቅመው በየቀበሌው የሚገኙ ነፍሰ ጡር እናቶችን ስም በመመዝገብ ወደ ጤና ጣቢያ ቢያመጡም በየጁቤ ጤና ጣቢያ ላይ ተገኝተው የወለዱ እናቶች ቁጥር አናሳ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የየጁቤ ጤና ጣቢያ የአምቡላንስ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ በአካባቢው የሚገኙ ቀበሌዎች ለትራንስፖርት ምቹ አለመሆንና የአምቡላንሶች የሥራ መደራረብ ሁሉም እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ ለማድረግ እንቅፋት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ በእናቶች መቆያ ክፍል እንዲቆዩ የማድረጉ ተግባርም ተቀዛቅዟል ብለዋል፡፡ የእናቶችን ሞት ለማስቀረት “ሃያ ብር ለእናቶች” በሚል የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል፡፡

ለትራንስፖርት አመች ካልሆኑ ቀበሌዎች ለክትትል የሚመጡ እናቶች ወራቸው መግባቱ ከተረጋገጠ የኮረናቫይረስ ወረርሽኝን መከላከል በሚያስችል ሁኔታ በጤና ተቋም እንዲቆዩ እየተደረጉ መሆኑን ኀላፊው ነግረውናል፡፡ የትዳር አጋሮች፣ ማኅበረሰቡ፣ እንዲሁም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ነፍሰ ጡር እናቶች ምጥ ሲጀምራቸው በጤና ተቋም እንዲወልዱ የድርሻቸውን እንዲወጡም አስገንዝበዋል፡፡

የባሶ ሊበን ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አባይ ካሳው የእናቶች በጤና ተቋም መገላገል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም በሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመድረሱን ተናግረዋል፡፡ እንደ ባሶ ሊበን ወረዳ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በጤና ተቋም ይወልዳሉ ተብለው በእቅድ ከተያዙ 2 ሺህ 458 እናቶች ውስጥ 952 እናቶች ብቻ ናቸው በጤና ተቋም የተገላገሉ ብለዋል ኀላፊው፡፡ የማኀበረሰቡ የግንዛቤ እጥረትና የመሰረተ ልማት ችግር እናቶች በቤታቸው ወልደው ለችግር እንዲጋለጡ እንዳደረጋቸውም ተጠቁሟል፡፡

ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት እያደረጉ መሆናቸውን ነግረውናል፡፡ ማኅበረሰቡ ባህላዊ አምቡላንስ ተጠቅሞ ነፍሰ ጡር እናቶችን ወደ ጤና ተቋም በማምጣት ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡

በወረዳው ሥር የሚገኙ የጤና ጣቢያዎችን አፈጻጸም በመገምገምም የማሻሻያ ሀሳብ በመስጠት ያሉባቸውን ችግሮች እንዲያስተካክሉ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የማኀበረሰቡ የግንዛቤ እጥረትና የመሰረተ ልማት ችግሮች ነፍሰጡር እናቶች በቤታቸው ወልደው ለችግር እንዲጋለጡ ምክንያት መሆናቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡ የምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኀላፊና የጤና እክብካቤ የሥራ ሂደት አስተባባሪ ሲስተር ደሃብ አላምረው የእናቶችን ሞትና ስቃይ ለመቀነስ በርካታ ስልቶች ተነድፈው ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡

በዚህም የእናቶች የሞት መጠን ከ46 በመቶ ወደ 12 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ በጤና ተቋም የሚወልዱ እናቶች ቁጥር በተፈለገው መጠን አለመሆኑን ተናግረዋል ምክትል ኀላፊዋ፡፡

እንደ ምክትል ኀላፊዋ መረጃ ባለፉት ስድስት ወራትም በእቅድ ከተያዘው 56 በመቶ ብቻ ናቸው በጤና ተቋም የወለዱት፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት 3 በመቶ ቀንሷል፤ ችግሩን ለመቅረፍ እናቶች ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንዳይጋለጡ በማድረግ በጤና ተቋም የሚገላገሉበትን መንገድ ማመቻቸት፣ በጤና ኬላ ይካሄዱ የነበሩ የነፍሰ ጡር እናቶች ኮንፈረንስ እንዲቀጥልና የጤና ባለሙያዎች ቤት ለቤት የሚያደርጉትን የግንዛቤ ፈጠራ ማጠናከር ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

የእናቶች ማቆያ በተጠናከረ መንገድ ወደ ሥራ እንዲገባ ይደረጋልም ብለዋል፡፡ በተጨማሪ ለወረዳዎች ሳምንታዊ የአፈጻጻም ውጤት እየላኩ መሆናቸውን ምክትል ኀላፊዋ ገልጸዋል፡፡ የእናቶችን ጤና መጠበቅና ከሞት መታደግ ቤተሰብን፣ ማኅበረሰብንና ሀገርን መታደግ እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የፌቤላ ዘይት ፋብሪካ ምርት ወደ መዲናዋ መግባት ጀመረ

admin

በትግራይ ክልል እየተደረገ ከሚገኘው ድጋፍ 70 በመቶው በመንግስት የተሸፈነ መሆኑ ተገለጸ

admin

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተመለከተ የሚመጡ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን መቋቋም የሚያስችል የተደራጀ ሥልት መቀየስ እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ።

admin