70.74 F
Washington DC
May 14, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“የመተከል ዞን ግብረኀይል እስካሁን ውጤታማ ተግባራትን ቢያከናውንም አሁንም ቀሪ ሥራዎች ይጠበቁበታ” የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኀንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው“የመተከል ዞን ግብረኀይል እስካሁን ውጤታማ ተግባራትን ቢያከናውንም አሁንም ቀሪ ሥራዎች ይጠበቁበታ” የጠቅላይ ሚኒስትሩ
የደኀንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በመተከል ዞን የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረሃይል እስካሁን ውጤታማ ተግባራትን
ቢያከናውንም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ቀሪ ስራዎች እንደሚጠበቁበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኀንነት አማካሪ ገዱ
አንዳርጋቸው ተናገሩ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኀንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ
ጉባኤዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል የመንግሥት የሥራ ኀለፊዎችን ያካተተ ልኡክ በመተከል ዞን የኮማንድ ፖስቱን ክንውን
ገምግሟል።
በቆይታቸው የኮማንድ ፖስቱን ሥራዎች ከመገምገም በተጨማሪ ከተለያዩ አመራሮች፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና የዞኑ ነዋሪዎች ጋር
ጠቃሚ ውይይቶች ማካሄዳቸውን አቶ ገዱ ገልጸዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመው ግብረ ኀይል የዜጎችን ሞት፣ መፈናቀልና ንብረት ውድመት በማስቆም ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ
ማስፈን ቀዳሚ ተልዕኮው መሆኑንም አንስተዋል።
ለዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና ንብረት ውድመት ምክንያት የሆነው የታጠቀ ሽፍታ ላይ ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ ረገድ ግብረኀይሉ
ጥሩ ሥራ ማከናወኑንም አቶ ገዱ ገልጸዋል።
ከታቀደው ግብ አኳያ ግብረ ኀይሉ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን የገለጹት አቶ ገዱ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ቀሪ
ሥራዎች ይጠበቁበታል ብለዋል።
በሌላ በኩል በሰላማዊ አማራጭ ችግሩን ለመፍታት በሀገር ሽማግሌዎች ጥረት ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ የተሠራው
ሥራም ትልቅ ግምት የሚሰጠው መሆኑን አንስተዋል።
የታጠቀውን ኀይል በድርድር ወደ ሰላም እንዲገባ በማግባባት ከ3 ሺህ 400 በላይ ታጣቂዎች እንደተመለሱም አስታውሰዋል።
ከዞን እስከ ቀበሌ ፈርሶ የነበረውን የመንግስት መዋቅር አዲስ አደረጃጅት መፈጠርና ኀብረተሰቡ ራሱን በራሱ እንዲጠብቅ
ሚሊሻ በማሰልጠን ጭምር የተከናወነው ሥራም የኮማንድ ፖስቱ የጥረት ውጤት መሆኑን አቶ ገዱ ገልጸዋል።
ያም ሆኖ ታጣቂውን ኀይል ትጥቅ በማስፈታትና መልሶ በማቋቋም እንዲሁም የሰለጠነውን ሚሊሻ መዋቅሩን በማጠናከርና ትጥቅ
በማሟላት ውስንነቶች አሉ ብለዋል።
በመተከል ንጹሃን ዜጎች በከፍተኛ ደረጃ የጉዳትና የመፈናቀል አደጋ ደርሶባቸዋል ያሉት አቶ ገዱ፣ የተመሰቃቀለውን አካባቢ ወደ
ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ማምጣት የግብረሃይሉ ያደሩ ቀሪ ስራዎች ናቸው ብለዋል።
እንደ አጠቃላይ የመተከል ዞንን መከላከያ ሠራዊት ከኀብረተሰቡ ጋር በመተባበር ወደ ቀደመ ሰላምና መረጋጋት እንዲመለስ
ያደረገው ጥረት ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው መሆኑንም አቶ ገዱ ተናግረዋል።
በዞኑ ወደ ሰላም የተመለሰውን ኀይል አሰልጥኖ በፍጥነት ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲገባ የማቋቋም እንዲሁም ትጥቅ ባለመፍታት
የሸፈተውን ኀይል የማደን ስራው በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የመተከል ሰላምና መረጋጋት በመከላከያ ሠራዊት ጥረት ብቻ እውን ስለማይሆን ኀብረተሰቡ፣ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላት
ቅንጅታዊ ስራ ያስፈልጋልም ነው ያሉት።
በዚህ ዙሪያ በተለይ የአማራ ክልል ከቤኑሻንጉል ጉሙዝ ክልልና ከኮማንድ ፖስቱ ጋር አብሮ መሥራት ይገባዋልም ብለዋል።
የጉሙዝም ሆነ የሌላው ማኀበረሰብ የጋራ ጠላት የሆነው የታጠቀ ሽፍታ እንጂ የሕዝቡ አብሮነትና የጋራ እሴት እንዳለ መሆኑን
መገንዘብም ይገባል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m ።
Previous articleለቴክኖሎጂ ቅጂና ፈጠራ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ የአማራ ክልል ቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
Next articleለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በቦንድ ሽያጭና በስጦታ ከ136 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ።

Source link

Related posts

ቦርዱ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ( ኦነግ) የተከናወነው ጠቅላላ ጉባኤ ተቀባይነት እንደሌለው አስታወቀ

admin

ፊቤላ ኢንዱስትሪ ከ12 ሚሊየን ሊትር በላይ ዘይት ለገበያ ማቅረቡን አስታወቀ

admin

እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ-ኢትዮጵያ | የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት

admin