51.91 F
Washington DC
May 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዕውን እንዳይሆን የሚሹ ኀይሎች አካባቢውን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ እየሠሩ ነው፡፡

የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዕውን እንዳይሆን የሚሹ ኀይሎች አካባቢውን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ እየሠሩ ነው፡፡

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዕውን እንዳይሆን የሚሹ የውጭ ኀይሎች አካባቢውን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ እየሠሩ እንደሆነ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አፈ ጉባዔዎች ገለጹ። የግድቡ መገኛ የሆነው የመተከል ዞን ግጭት የውጭ ኀይሎች እጅ እንዳለበት በመግለጽ ድርጊቱን ኮንነዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ “በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ በግንባታ ላይ የሚገኘው የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓይን፣ ልብና መንፈስ ነው” ብለዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አደም ፋራህ በበኩላቸው “የሕዳሴውን ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን አሻራ ያረፈበት የባንዲራ ፕሮጀክት” ብለውታል።

“የግድቡን ግንባታ ለማስተጓጎል የውጭ ኀይሎች ግንባታው የሚገኝበትን የመተከል ዞን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ እየሠሩ ነው” በማለትም ኮንነዋል። በዚህም ከሶስት ዓመት በፊት ከግለሰብ ወደ ብሔር የዞረው የመተከል ግጭት የውጭ ኀይሎች እጅ እንዳለበት ገልጸዋል። የመተከል ግጭት በዋናነት ከሕዳሴ ግድብ ጋር የተያያዘ መሆኑን ተረድቶ ትንኮሳዎችን ተቋቁሞ ፕሮጀክቱን ዳር ማድረስ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

እነዚህ ኀይሎች ፕሮጀክቱ እንዳይጠናቀቅ ለማድረግ ሙሉ አቅማቸውን በመጠቀም እርስ በርስ ለማጋጨት እየሠሩ መሆኑን በመገንዘብ ኢትዮጵያዊያን በጋራ መቆም እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። “በሀገር ሉዓላዊነት፣ በዜጎችና በሀገር ክብር አንደራደርም፤ ታሪክ ምስክር ነው” የሚሉት አፈ ጉባዔዎቹ፤ አሁንም በውኃ ድርድሩ በሉዓላዊነት ‘እንደማንደራደር አሳይተናል’ ብለዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣናው ሀገራት ሠላም እንደምትሻ፣ ሌሎችን መጉዳት እንደማትፈልግ፣ ሌሎችን ሳትጎዳ በድንበር ተሻጋሪ የውኃ ሀብቷ በመጠቀም ተፈጥራዊ መብቷ እንደማትደራደር ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስከብራ የቆየች ባለታሪክ ታላቅ አገር መሆኗን ገልጸው፤ ኢትዮጵያዊያን የውጭ ኀይሎች በሚፈጥሩት አጀንዳ መጠለፍ እንደሌለባቸውም አስገንዝበዋል።

አንቂዎችና ማኅበራዊ ሚዲያዎች የእርስ በርስ ግጭት የሚያባብሱና ለጠላት ምቹ ዕድል የሚፈጥሩ መረጃዎችን ከማቅረብ እንዲታቀቡ መጠየቃቸውንም የዘገበው ኢዜአ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

በመዲናዋ ከ314 የግል አሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲዎች ባስመዘገቡት አድራሻ የተገኙት 150 ኤጀንሲዎች ብቻ መሆናቸው ተገለጸ

admin

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

admin

በርግጥ ኢትዮጵያ ዝናብ አዝንባለች?

admin