56.68 F
Washington DC
April 21, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ዝክረ ዓድዋ ዝግጅት የሁሉም አፍሪካውያን መሆን እንዳለበት በዩጋንዳ ማኬሬሬ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር አስገነዘቡ፡፡

ዝክረ ዓድዋ ዝግጅት የሁሉም አፍሪካውያን መሆን እንዳለበት በዩጋንዳ ማኬሬሬ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር አስገነዘቡ፡፡

ባሕር ዳር ፡ የካቲት 19/2013 ዓ.ም (አብመድ)በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና ማኬሬሬ ዩኒቨርስቲ በትብብር ያዘጋጁት 125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዩጋንዳ ካምፓላ ሸራትን ሆቴል በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡ በዓሉ ‹‹የዓድዋ ድል እና ፓን አፍሪካኒዝም›› በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተከበረው፡፡ የዓድዋ ድል አፍሪካውያን ብሎም መላው ጥቁር ሕዝብ የተጋረጠበትን ወቅታዊ የሉዓላዊነት እና የልማት ተግዳሮቶች ለመዋጋት የነፃነት ኃይል የሚያሰባስብበት እና ወኔ የሚሰንቁበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የዓድዋ ድል የጣሊያን የቅኝ ግዛት ምኞት በአጭሩ የቀጩበት መሆኑ ተወስቷል፡፡ የዓድዋ ድል በዓል ጣልያን ኢትዮጵያን የማዳከም ሴራ እና በ1889(እ.ኤ.አ.) በተፈረመው የውጫሌ ስምምነት ቅጥፈት የተጋለጠበት መሆኑ ተነስቷል፡፡

በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለምፀሐይ መሠረት በውይይቱ መክፈቻ ንግግራቸው ዓድዋ ጥቁር ሕዝቦች በነጮች ላይ የተጎናጸፉት ድል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

እንደ አምባሳደሯ ገለጻ ዓድዋ ለአዲሱ አፍሪካዊ ትውልድ የህይወት ፈተናዎችን የማሸነፍ እና በራስ የመተማመን ስነልቦና የሚጎናጸፍበት ነው፤ ዓድዋ የሕዝቦች አንድነት፣ በአግባቡ የተጠና እና ግዙፍ የሰው ሀይል፣ ስንቅ እና ትጥቅን በሚገባ የመምራት ጥበብ እና የላቀ ዲፕሎማሲ ብቃት ውጤት ነው፤ ይህን መላው አፍሪካውያን ልንማረው የሚገባው ነው፡፡

በዓድዋ ድል ዙሪያ ተጨማሪ ጥናት እና ምርምሮችን በማድረግ ለአፍሪካውያን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋቶቹን ማጉላት እንደሚጠበቅም አስረድተዋል፡፡ በክብር እንግድነት በበይነመረብ የተሳተፉት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ‹‹የዓድዋ ድል የመላው የጥቁር ሕዝቦች ድል ነው›› ሲሉ ገልጸውታል፡፡

125ኛው መታሰቢያ በዓል በፓን አፍሪካኒስቷ ሀገር ዩጋንዳ መከበሩ ለአህጉሪቱ ትልቅ ትርጉም እንዳለውም አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹ከአድዋ የምንማረው አንዱ መቋቋም የማንችለው የሚመስለንን ችግር በተገቢ ዝግጅት እና አንድነት መፍታት ወደሚያስችል ደረጃ ማምጣትን ነው›› ሲሉም ተናግረዋል።

ዓድዋ አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግሮች በራሳቸው ተነሳሽነት መፍታት እንደሚችሉና የየትኛውም የውጭ ኃይል ሞግዚትነት እንደማያስፈልጋቸው ያስገነዘበ መሆኑን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

የዓድዋ ተዋጊዎች የማይቻል እና የማይሸነፍ የሚመስለውን በጋራ ችለው እንዳሸነፉት ሁሉ በአሁኑ ወቅት በአህጉሪቱ ያሉ ተግዳሮቶችን ለማሸነፍ አፍሪካውያን በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በማኬሬሬ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ከፍተኛ መምህር ምዋምቡጻያ ንደቤሳ እንዳሉት ዓድዋ በአፍሪካ ውስጥ የነፃነት እንቅስቃሴዎችን በማወጅ፣ ተጽዕኖ በማሳደር እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም በቅኝ ገዢዎች ላይ ድል የተቀዳጀ ተምሳሌታዊ ክስተት ነው፡፡

የአፍሪካውያን የጋራ ታሪክ የሆነው ዓድዋ የፓን አፍሪካኒዝም እና አህጉራዊ ውህደት ጥረቶችን ለማስፋፋት እንደ መሳሪያ ሊያገለግል እንደሚችልም ጠቅሰዋል፡፡

ምሁሩ ዓድዋ ለአፍሪካውያን የጋራ የኩራት ስሜት የሚፈጥር እና የውጭ ኀይሎች የበላይነትን ለመቃወም እንደ ማነሳሻ ስለሚሆን ዝክረ አድዋ ዝግጅት የሁሉንም አፍሪካውያን መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ፡-ኔክስት ሚዲያ ዩጋንዳ

በየማነብርሃን ጌታቸው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

በፌደራል ተቋማት ውስጥ በብልሽት ተጠራቅመው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶች ከነገ ጀምሮ ይመዘገባሉ ተብሏል

admin

የፖለቲካ ሽግግሩ በታሰበው ልክ ለውጥ እያመጣ አለመሆኑን የፖለቲካ ምሁራን ተናገሩ።

admin

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ ጀምረዋል።

admin