56.68 F
Washington DC
April 21, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“ዛሬ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የጥምቀት በዓል በአለም ቅርስነት በተመዘገበበት ወቅት ነው” ዶክተር ሂሩት ካሳው

“ዛሬ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የጥምቀት በዓል በአለም ቅርስነት በተመዘገበበት ወቅት ነው” ዶክተር ሂሩት ካሳው

ባሕር ዳር፡ ጥር 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) “ዛሬ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ በዓለም በማይዳሰስ ወካይ ቅርስነት በተመዘገበበት ወቅት ነው” ሲሉ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ገለጹ።

ዶክተር ሂሩት ዛሬ በአዲስ አባበ ጃን ሜዳ እየተከበረ በሚገኘው የጥምቀት በዓል ላይ ተገኝተው ለኢትይጵያውያን የእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጥምቀት በዓል በሀገራችን የሚወደድ እና የሚናፈቅ ዓመታዊ በዓል ነው ብለዋል።

በዚሁ ወቅት የጥምቀት በዓል ዩኔስኮ በዓለም በማይዳሰስ ወካይ ቅርስነት ከተመዘገበ አንድ ዓመት አልፎታል ነው ያሉት።

“በዚች ውብ ሀገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን የቀደምት እናት እና አቦቶቻችንን ቱፊት ተረክበን፤ተንከባክበን እና ጠብቀን ለተከታይ ትውልድ ማሻገር አለብን” በማለት ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ ለዚህ ደግሞ ሃይማኖታዊ አስተምህሮዎችን በሚገባ ማወቅ እንደሚገባና በተግባር መኖር አስፈላኒጊ ነው ያሉት።

ዶክተር ሂሩት ጥምቀትን ጨምሮ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የሚከበሩ ባህላዊም ሆነ ሃይማኖታዊ በዓላት በሚከበሩበት ወቅት በጋራ እና በመደጋገፍ የማክበር ባህላዊ እሴቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

“ፈጣሪ ያለ ፍቅር አይገኝምና ፍቅርን አስቀድመን፤አንዳችን ለሌላችን ዘብ በመቆም፤ እየተደጋገፍን የፍቅራችንን መልካም መዓዛ ለተከታይ ትውልድ ማስረከብ ይጠበቅብናል” ብለዋል።

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ በተለይም የሃይማኖት አባቶችን እና የስጋ እናትና አባቶችን ምክር በመስማት በሚገባ መተግበር ይገባል በማለት ተናግረዋል።

“ሀገር ክፉም ሆነ በጎ የሚባለው በውስጡ በሚኖሩ ሰዎች ተግባር በመሆኑ መልካም ስራ የሚሰሩ ወጣቶች፤ በመልካም ሥነ ምግባር የታነጻችሁ እና በስራም ትጉዎች በመሆን ሀገራችሁን ለመጥቀም አልማችሁ ተንቀሳቀሱ” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዶክተር ሂሩት ካሳው በዚሁ ወቅት ሁሉም ለሰላም እና ለፍቅር ጠበቃ እንዲሆን ጥሪ ማቅረባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

አቶ ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከተመራው የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

admin

የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ በሴቶች እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አመርቂ መሆናቸውን ገለጹ

admin

ከ8 ሺህ በላይ እጩዎችን መመዝገቡንና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች 49 የምርጫ መወዳደርያ ምልክቶችን መውሰዳቸውን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።

admin