73.18 F
Washington DC
June 17, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ከነበረው የኢንተርኔት አቅርቦት በ14 እጥፍ የሚልቅ የኢንተርኔት አገልግሎት ይፋ ሆነ።

ከነበረው የኢንተርኔት አቅርቦት በ14 እጥፍ የሚልቅ የኢንተርኔት አገልግሎት ይፋ ሆነ።

ባሕር ዳር: መጋቢት 23/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምዕራብ ሪጅን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ የኢንተርኔት አገልግሎት አስጀምሯል። አገልግሎት የጀመረባቸው ከተሞች ባሕር ዳርን ጨምሮ ፍኖተሰላም፣ ዳንግላ፣ እንጅባራ፣ ቡሬ፣ ደብረማርቆስ እና ቻግኒ ናቸው።

የጀመረው የ4 ጂ የኢንተርኔት አገልግሎት በቀጣናው የነበረውን የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት በ14 እጥፍ ያሻሽለዋል ነው የተባለው።

በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ከሥፍራው በቀላሉ ለማስተዋወቅ፣ የንግድ ሥርዓቱን ለማሳለጥ፣ ለኢንቨስትመንት፣ የትምህርት ተቋማትን አሠራር ቀላል ለማድረግና ለሌሎች አገልግሎቶች መልካም አጋጣሚ ነውም ተብሏል።

በመርኃግብሩ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወርቀሰሙ ማሞ ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝን ጨምሮ የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ ሠራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንዳሉት ኢትዮ ቴሌኮም በአፍሪካም ግዙፍ ከሚባሉ ተቋማት አንዱ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮ ቴሌኮም ተመራጭ ብቻ ሳይሆን አንደኛ እንዲሆን እየሠራ መሆንም ተናግረዋል።

127 ዓመታት ያስቆጠረው ኢትዮ ቴሌኮም በበርካታ ለውጦች ውስጥ አልፏል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ለዜጎቿ የቴሌኮም አገልግሎት የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር መሆኗንም አንስተዋል።

በሦስት ዓመት የዕቅድ ትግበራ ውስጥ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የ4ጂ አገልግሎት መስጠት አንደኛው መሆኑንም ተናግረዋል።

በ2020 የተጀመረውን የ5ጂ የኢንተርኔት አገልግሎት በኢትዮጵያ በ2022 ለማስጀምር እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት የሚኖሩ ሀገራት ዜጎች 47 በመቶ ብቻ የሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው።

የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 26 በመቶ ሲሆኑ በ4ጂ አገልግሎት ደግሞ 9 በመቶ ብቻ ተጠቃሚዎች ናቸው። ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ 52 ነጥብ 7 ሚሊዮን ደንበኛ አለው።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ምክር ቤት ተመሰረተ

admin

“በኢትዮጵያ ደካማና ተላላኪ መንግሥት ለመፍጠር የሚሹ ሀገራት አይሳካላቸውም” የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች

admin

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መገናኛ ብዙኀን ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው የሰላም ሚኒስቴር አሳሰበ።

admin