70.61 F
Washington DC
June 22, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ከሞት የበለጠ አስፈሪ ነገር ምን አለ?ከሞት የበለጠ አስፈሪ ነገር ምን አለ?
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 05/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከጅማሮው የከፋ ፍፃሜ እያስተዋልን ነው፡፡ ነገር ግን በኮሮናቫይረስ የመጀመሪያ
ክስተት ወቅት የነበረ ትኩረት ዛሬ አይስተዋልም፡፡ ከንድፈ ሃሳብ የተሻገረው የወረርሽኙ አስከፊነት ዛሬ የእያንዳንዱን ማኅበረሰብ
በር እያንኳኳ ነው፡፡ ውለታቸውን በምስጋና ያልከፈልናቸው እናቶቻችንን ሳናስብ ተነጥቀናል፡፡ ብዙ ስላልተጮኽለት ብቻ እየሞትን
አልመሰለንም እንጅ ሲለዩ የሚያጎድሉ ሰዎችን አጥተናል፡፡
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሉታዊ ተፅዕኖ ከሚነገረው በላይ የሚታይ ቢሆንም አሁን ትልቁ ስጋት በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ሞት
ነው፡፡
መጋቢት 4/2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ አንድ ያለው የኮሮናቫይረስ ክስተት አሁን የስርጭት አድማሱ ሰፍቶ እና የጉዳት መጠኑ ገዝፎ
ተጋላጭ ያልሆነ የማኅበረሰብ ክፍል የማይኖርበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እየጎዳው ያለው በእድሜ የገፋውን የሕብረተሰብ ክፍል ብቻ አድርጎ መመልከቱ ደግሞ ከቦታ ቦታ አብዝቶ
የሚንቀሳቀሰውን ወጣት የሕብረተሰብ ክፍል ለተሳሳተ እይታ ዳርጎታል፡፡
ወረርሽኙ የበለጠ የሚያጠቃው በእድሜ የገፉትን ብቻ ቢሆን እንኳን እሱ ወይም እሷ ባመጡት ጦስ አባቱን ወይም እናቱን ማጣት
የሚፈልግ ማን ነው? የቤተሰቡ የጤና ሁኔታ የማያስጨንቀው፣ ቤተሰቡን አደጋ ላይ ለመጣል የሚመኝ እና ኅላፊነት የማይሰማው
ሊኖር ይችላልን? ችግሮቻችን የኅብረት ማጣት እና ከልማድ ያለመውጣት ማነቆ ካልሆኑ በቀር፡፡
የኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋት ከሆነበት ጊዜ አንስቶ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ለመከላከል ያግዛሉ የሚሏቸውን
የአሠራር መመሪያ እና ደንቦች ሲያዘጋጁ ቢስተዋልም ተፈፃሚነቱ ግን ያን ያክል ጎልቶ የወጣ አይደለም፡፡
አልፎ አልፎም መመሪያ አውጭው አካል ያወጣውን መመሪያ መልሶ ሲጥስ ማየትም የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡
ከሰሞኑ ወደ ፈለገ ሕይዎት ሪፈራል ሆስፒታል ለግል ጉዳይ በተደጋጋሚ ሄጀ ነበር፡፡ በሆስፒታሉ በር አካባቢ ያለው ቁጥጥር
አበረታች ነው፡፡ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭብል ሳያደርጉ ወደ ውስጥ ዘልቆ መግባት ፈፅሞ አይቻልም በተደጋጋሚ ጊዜ
ያስተዋልኳቸው ጥበቃዎች በዚህ ዙሪያ እጅጉን ንቁ ናቸው፡፡
ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ግን ማስካቸውን አውልቀው ወደ ኪሳቸው የሚያስገቡት ደግሞ ብዙዎች ናቸው፡፡ ነገሩ “ሌባ እና ፖሊስ”
የሚሉት የልጆች ጨዋታን ይመስላል፡፡ እንድትለብስ ስትጠየቅ ትለብሳለህ ካልተጠየክ ደግሞ አውልቆ ወደ ኪስ ማስገባት
ሆኗል፡፡ ማስክ የምንለብሰው ስለምንጠየቅ እንጂ ወረርሽኙን ፈርተን እና ራሳችንን እና ቤተሰቦቻችንን ከቫይረሱ ለመታደግ
አይመስልም፡፡
በእርግጥ ቀርቤ ያነጋገርኳቸው አንዳንድ አስታማሚዎች እንደሚሉት ሆስፒታሉ ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ
ነው ባይ ናቸው፡፡ በሆስፒታሉ ውስጥ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ህሙማን አልጋ ከያዙ ህሙማን ጋር በጋራ ይስተናገዳሉ፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ ከሰሞኑ በሆስፒታሉ ውስጥ በዘመቻ የሚሰጠው የዐይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ከኮሮናቫይረስ መከላከያ ፕሮቶኮል
ጋር የሚቃረን ነው፡፡
የአስታማሚዎቹ አስተያየት ትክክል ነው ያሉት የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ዐቢይ ፍስሃ የኮሮናቫይረስ መከላከል ሥራው መፋዘዝ
ገጥሞታል ይላሉ፡፡ ችግሮቹ ደግሞ ወጥ የሆነ የአሠራር ሂደት አለመኖር እና የመከላከያ መሳሪያዎች እጥረት የፈጠሩት ነው
ብለውናል፡፡
ከ560 የማይበልጡ አልጋዎች ያሉት ሆስፒታሉ በሪፈር ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ህሙማንን ተቀብሎ ያስተናግዳል፡፡
በየጊዜው ወደ ሆስፒታሉ የሚገቡ ህሙማን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤታቸው እስኪታወቅ ድረስ ከሌሎች
ህሙማን ጋር በአንድ ክፍል የሚያሳልፉበት ሁኔታ አለ ነው ያሉን፡፡
በዘመቻ እየተሰጠ ያለው የዐይን ሞራ ግርዶሽ አሁን የወጣውን የኮሮናቫይረስ ፕሮቶኮል የሚጥስ ቢሆንም ህክምናው በዘመቻ
የሚሰጥ በመሆኑ እና አስፈላጊነቱ ትልቅ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ እንደነገሩን እንደ ሀገርም እንደ ሆስፒታልም የኦክስጅን እጥረት ገጥሟል፡፡ ፈለገ ሕይዎት በቀን 200
ሲሊንደር ኦክስጅን ቢያስፈልገውም በቀን ከ80 በላይ ሲሊንደር እያገኘ አይደለም፡፡ በየቀኑ ከተለያዩ አካባቢዎች በሪፈር የሚመጡ
የኮሮናቫይረስ ሕሙማን በሽታን የመቋቋም አቅማቸው ተዳክሞ ስለሚደርሱ ሕይዎታቸውን መታደግ አልተቻለም፤ በኮሮናቫይረስ
ሕይዎታቸውን የሚያጡት በእድሜ የገፉ ብቻ አይደሉም ይህ በየቀኑ የምናየው ሀቅ ነው፤ ሐኪሞች በቂ የመከላከያ ቁሳቁስ
በሌለበት ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው እየሠሩ መሆኑን ሥራአስኪያጁ ገልጸዋል።
“ልትረዱን ይገባል፤ ታማችሁ ስትመጡ እህት እና ወንድሞቻችን ናችሁና መስተንግዶ ልንከለክላችሁ ሙያችንም ሆነ
ኢትዮጵያዊነታችን አይፈቅድም፤ ነገር ግን የኛ ሐኪሞችም የእኔ የሚሉት የራሳቸው ቤተሰብ እና ሕይዎት አላቸውና ልንደጋገፍ
ይገባል፡፡ ሌላ ነገር አናስቸግራችሁም ቢያንስ ከብዙ ሰዎች ጋር ስትገናኙ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ተጠቀሙ፤
እጆቻችሁን በአልኮል እና ሳኒታይዘር አፅዱ፤ ራሳችሁን ከኮሮና ቫይረስ ተከላከሉ፡፡ ከዚህ አልፎ የሚከሰትን ችግር ሐኪሞቻችን
ለመቆጣጠር ይሞክራሉ” ብለዋል የፈለገ ሕይዎት ሪፈራል ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ፡፡
በታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleበኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥናት ሊካሄድ ነው።

Source link

Related posts

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ760 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት በመስኖ ለምቶ ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ፡፡

admin

ጠ/ሚ ዐቢይ ከክልል አመራሮች ጋር ለሃገራዊው ምርጫ ያለውን አጠቃላይ ዝግጅት ገመገሙ

admin

የጥፋት ሀይሎችን ህግ ፊት ለማቅረብ መንግስት እየሰራ ይገኛል- የሰላም ሚኒስቴር

admin