67.32 F
Washington DC
June 14, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ከማሪታይም ዘርፉ ኢትዮጵያ  ማግኘት የሚገባትን  ያህል እየተጠቀመች አለመሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ከ90 በመቶ በላይ የሆነውን የወጪና ገቢ ንግድ በማሪታይም  የምታሳልጠው  ኢትዮጵያ ከዘርፉ የሚገባትን ያህል እየተጠቀመች አለመሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በመተባበር  ብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ  ላይ ያተኮረ የውይይት  መድረክ አዘጋጅቷል።

መድረኩ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን ለማሳደግ እና  ለማሪታይም ዘርፍ የላቀ አፈፃፀም እንዲያመጣ ታስቦ

የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።

በተጨማሪም  የብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ ፣በስትራቴጂው ትግበራ ላይ የባለድርሻ አካላትን ኃላፊነትና ሚና በማስገንዘብ ለተግባራዊነቱ ለማዘጋጀት ታሳቢ ተደርጎ   መዘጋጀቱ ተገልጿል ።

በመድረኩም የብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ዝርዝር ዓላማ አስፈላጊነት እና ዝርዝር አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል ።

በውይይቱም የማሪታይም ዘርፉ ብዙ ጠቀሜታ ያለዉ ቢሆንም ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ያህል እየተጠቀመች አለመሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን  የዘርፉን ከፍተኛ ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ በመገንዘብ የብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ቀርፆና ከእስትራቴጂው  የተቀዳ የ10ዓመት መሪ የልማት እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጿል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያብባል አዲስ÷  ዘርፉ የሚጠበቅበትን ድርሻ ማበርከት እንዲችል ደግሞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸው የዘርፉ ተዋናዮች የብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን ተገንዝበው በጋራ መስራት መቻል እንዳለባቸው አንስተዋል።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በማሪታይም ዘርፉ የተለያዩ የግል እና የመንግስት ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 Source link

Related posts

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አሁን ካለው ቴሌቪዥን ስርጭት በተጨማሪ “አማራ ሕብር” ኹለተኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ በቅርቡ የሙከራ ሥርጭት እንደሚጀምር የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥየ አስታወቁ፡፡

admin

“የሴቶች ተሣትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ የሴቶች የምክክር መድረክ ተካሄደ

admin

ከተማ አስተዳደሩ በመሬት ወረራ፣በባለቤት አልባ ህንጻዎች፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዙሪያ ያካሄደውን ጥናት ይፋ አደረገ

admin