51.91 F
Washington DC
May 11, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ከመተከል ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ ራንች ጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ተፈናቃዮች የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላክል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ እንዲቀርብላቸው ጠየቁ፡፡

ከመተከል ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ ራንች ጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ተፈናቃዮች የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላክል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ እንዲቀርብላቸው ጠየቁ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 05/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ሥር ከ60ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በአንድ አካባቢ ተሰባስበው እንደሚኖሩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ያሉበት ሁኔታም የወቅቱን የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል የማያስችል በመሆኑ ሥጋት እንደገባቸው ነው አሚኮ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች የገለጹት፡፡

እንደ ተፈናቃዮቹ ገለጻ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መግዛት አልቻሉም፤ ረጂ ድርጅቶችና መንግሥትም ወርሃዊ ስንዴ ከማቅረብ ውጭ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላክል የንጽህና መጠበቂያን ጨምሮ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ እንዳላቀረቡላቸው ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የሚገኙበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የኮሮና ወረርሽኝን መከላከል የሚያስችል ቁሳቁስ እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል፡፡

የቻግኒ ከተማ አሥተዳደር ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደሳለኝ ብዙ እንዳሉት ጽሕፈት ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ባለሙያ መድቦ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየሠራ ነው፤ ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ዜጎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ ጤና ጣቢያና በቻግኒ ሆስፒታል ክትባቱን እንዲወስዱ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ለማቅረብ ግን ከወረዳው ጤና ጥብቃ ጽሕፈት ቤት አቅም በላይ እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡

በአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኀብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከል፣ መቆጣጠር፣ ምላሽ መስጠት እና መልሶ ማቋቋም ባለሙያ ተመስገን አንተዬ እንዳሉት ደግሞ ተፈናቃዮች ብዙ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ለማቅረብ አስቸጋሪ ቢሆንም ረጂ ድርጅቶች የሚያቀርቡትን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ቅድሚያ ለተፈናቃዮች በመስጠት ተደራሽ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል፡፡

በጊዜያዊነትም ቢሆን ተፈናቃዮች ወደ ሌላ ቦታ ሳይወጡ ከሚኖሩበት አካባቢ በመሆን ወረርሽኙን መከላከል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ከውጭ ወደ ተፈናቃዮቹ መኖሪያ የሚገቡ ባለሙያዎችም ወረርሽኙ ወደ ተፈናቃዮች እንዳይተላለፍ በጥንቃቄ ሥራዎችን እንዲሠሩ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ እስከ አሁንም የከፋ ችግር እንዳልተከሰተ ተናገረዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

በመዲናዋ ከ314 የግል አሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲዎች ባስመዘገቡት አድራሻ የተገኙት 150 ኤጀንሲዎች ብቻ መሆናቸው ተገለጸ

admin

ኢዜማ ከባሕር ዳር ከተማ እና አካባቢው ከሚገኙ የሲቪል ማኅበራት ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡

admin

ባለቤቱን ካልናቁ ፤አጥሩን አይነቀንቁም !! – ማላጂ  

admin