56.68 F
Washington DC
April 21, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Uncategorized

ኦሮሙማ ሲገማና ሲገለማ (ወይራው እርገጤ) | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

ወያኔ በዘረፋ፡በዘረኝነት በጸረ ኢትዮጵና በጸረ አንድነት የተሳሳተ ቅኝቱ ከልክ አልፎ በእብሪት በመወጠሩ በህዝቡ ትግል ወድቆ ታሪካዊ ሞቱን ሊሞት ችሏል፡፡ በወያኔ አምሳያ ተፈጥሮና በዘረኝነት መርዝ ተኮትኩቶ ያደገው ኦሮሙማም በተራው የሞት ጽዋውን ሊጎነጭ አፋፍ ላይ ደርሷል፡፡ አገራችን በታሪኳ አይታው የማታውቃችው እጅግ አሳፋሪ የሆኑ ብሄራዊ ውርደቶችን፡ የህይወት ምስቅልቅሎችንና ሊታሰቡና ህሊና ሊሸከማቸው የማይችሉ እጅግ ሰቅጣጭ ዘር ተኮር ጭፍጨፋወችን አስተናግዳለች፡፡አሁንም እያስተናገደች ነው፡፡ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ ምንድን ነው ብለን ብንጠይቅ መልሱ አንድ ብቻ ነው፡፤ በገራሙና በየዋሁ የኦሮሞ ሰፊ ህዝብ ስም የሚምሉትና የተደራጁት ተረኛ የኦሮሙማ መንጋወች በራሳቸው ህልም የሳሏትን ኢትዮጵያን በሚያልሟት ታላቁዋ ኦሮሚያ ልክና መልክ ቀርጸው ለመተግበር በመነሳታቸው ነው፡፡መልሱም በአጭሩ አይቻልም ነው፡፡ ከብቶች ተሽጠውላቸው እንዲማሩ የተደረጉ ጥቂት የማይባሉ የኦርሙማው መንጋ አባላት አስተሳሰባቸው ከተሸጡት ከብቶች ያልተሻለ በመሆኑ አያሌ አሳፋሪና አሳዛኝ ስራወችን ሲሰሩ ይስተዋላሉ፡፡

የኦሮሙማ አላማ የታላቋን ኦሮሚያ የበላይነት በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ኪሳራና ውድቀት በተለይም የአማራውን ነገድ የበታች በማድረግ ኢትዮጵያን በኦሮሞ ልክና አምሳያ የመቅርጽ፡ የመፍጠርና የማስፋፋት ፕሮጀክት ነው፡፡ኦሮሙማን ከላይ አስኳል ሆኖ የሚመራው በኦሮሞ ብልጽግና ውስጥ ያሸመቀው ህቡእና ይፋዊ ቡድን ሲሆን በይፋ ከሚታወቁት የቡድኑ አባላት ውስጥ እነ አባዱላ ገመዳ፡ሌንጮ ለታና ሌንጮ ባቲ፣ድማ ነገዎ፡ ግርማ ብሩ፡..ወዘተ ይገኙበታል፡፡ ከላይ ቁንጮው አብይ አህመድ ቢሆንም በኦሮሙማ ፕሮጀክት ውስጥ ከውጭ ሲታዩ የማይስማሙ የሚመስሉ በውስጥ ሌሎች አንጃወችም አሉ፡፡ የመሪነት ወንበሩ ላይ ማን ይቀመጥ በሚለውና በአካሄድ ጥያቄ ይለያዩ እንጅ በፕሮጀክቱ ሁሉም አንጃወች አንድ ናቸው፡፡ኦነግ ፡ኦፌኮና ኦነግ ሸኔ ..ወዘተ ተብለው ከሚጠሩት ክፍልፋዮች ጋር በምስጢር የተገመደው የኦሮሙማ ገመድ እጅግ ውስብስብ ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት በአገራችን ኦሮሙማ በተረኝነት በመታበይ ከሁሉም የኦሮሞ ተጎራባች ክልሎች ጋር ግዛትን በማስፋፋት ከባድ ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡ ለዚሁ እውነታነት ይረዳን ዘንድ በየኦጎራባች ክልሎች ውስጥ በመካሄድ ላይ ያሉትን በሴራና በማንአለብኝነት የተሞሉ ወረራወችን በዝርዝር እንመልከታቸው፡፡ወያኔ በጉልበት አገር አፍርሶ መርዝ ነስንሶ ህዝቡን በዘር ከማናከሱ በፊት ጎንደር ከትግራይ ጋር ድንበሩ የተከዜ ወንዝ እንደሆነ ያውቅ እንደነበረ ሁሉ ወለጋም ከጎጃም ጋር ድንበሩ የአባይ ወንዝ መሆኑን ኦሮሙማ ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ አሁን ላይ ኦሮሙማ አሻድሌ ሀስን የተሰኘ የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንት ተብዬን በመሳሪያነት በመጠቀም በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር በቤንሻንጉል ውስጥ በመተከልና ዙሪያዋ የሚያደርገው ዘር ተኮር ጭፍጨፋን ያካተተ አማራን የማፈናቀል አደገኛ ዘመቻ የታላቁን ህዳሴ ግድብ ወደ ኦሮምያ ክልል የማካተት ዘመቻ ነው፡: በነገራችን ላይ ወያኔ ቤንሻንጉል ጉምዝ ብሎ የፈጠረው ክልል ውስጥ የክልሉ 67% መሬት የተውሰደው ከጎጃም መተከልን ሲሆን ቀሪወቹ ሁለቱ የካማሸና ጉሙዝ ዞኖች ከወለጋ የተወሰዱ ናቸው፡፡ እዚህ ላይ ማጤን ያለብን ጉዳይ ወያኔም ኦሮሙማም ዋና አላማቸው የተሀድሶ ግድቡ ያለበትን ቦታ መቆጣጠር ነበር፡፡ወያኔ እንደከሸፈበት ሁሉ ኦሮሙማም አይሳካለትም፡፤ ይህ ሴራ ግን ለአድሮ ቃሪያወቹ የአማራ ብልጽግናወች የውርደት ካባቸው ነው፡፡ወሎ ኦሮሞ ነው (እንዲያውም እስከ አሽንጌ ድረስ ተዘርግቶ ወልድያን መርሳንና ደሴን ያካተተ ካርታ በመስራት) ለሚለው ከንቱ ምኞታቸውም ክብር ለታላቁ የወሎ መሪ ለንጉስ ሚካኤል ይሁንና በወረኢሉ አውራጃ ድንበር አካባቢ ካሉት ከሸዋ ጋር ኩታ ገጠም ከሆኑ ወረዳወች በስተቀር ወሎ አማራ እንጅ ኦሮሞ አይደለም፡፡በምኞትና በጉልበት የሚቀየር እውነታ አይኖርም፡፡ በከሚሴ፡ በአጣዬና በካራቆሪ ኦሮሙማ የሚያደርርገው ተደጋጋሚ የወረራ ሙከራም የዚሁ ተስፋፊነት አካል ሲሆን ኦሮሙማ ወደፊት እንዲተነፍስ ሲደረግ በቀላሉ ይለይለታል፡፡ ኦሮሙማ ከሌሎች ተጎራባች ክልሎች ጋር ያለውንም የወረራ እቅድ ደግሞ በአጭሩ እንደሚከተለው እንመልከት፦ በሱማሌ በኩል እስከ ጅጅጋ ኦጋዴን ቆላማ ቦታወች ድረስ፡ በአፋራ በኩል አዋሽ ፡በሲዳማ በኩል ሻሼመኔንና ወንዶ ገነት፡ ከጌድዮና ጉጂ ጋር፡ ከጋሞ ጋር አርባ ምንጭን ጨምሮ በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ : በሰባት ቤት ጉራጌ ከ150 አመት በኋላ የአባገዳ ስርአት ምስረታን ያካተተ ትርክት፡ የአዲስ አበባና የዲሬዳዋ ከተሞች የስልቀጣ ስትራቴጅ፡ በጋምቤላም ብቸኛው ወደሱዳን መውጫችን ነው በማለት በቄለም ወለጋ በኩል የሚሰራው መስፋፋት … ወዘተ የሚታወቁና ግልጽ የሆኑ ኬኛወቹ ለታላቋ ኦሮምያ ምስረታ በየአቅጣጫው የሚያደርጓቸው ወረራወች ናቸው፡፡ እነዚህ ወረራወች በየአቅጣጫው በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ተጋድሎ በቶሎ ካልተገቱ አገሪቱን በዘመነ መሳፍንት ጊዜ ከነበረችበት በባሰ ደረጃ ሊከፋፍሏትና ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ሊከቷት እንደሚችሉ ግልጽ ነው፡፤

ኦሮሙማ በእንደዚህ አይነት ደረጃ ገምቶና ገልምቶ ባለበት በዚህ ወቅት የአገሪቱ መሪ ተብየው አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ የሚመጥን መሪ ባለመሆኑ ሁሉም አይነት የአገር ውርደቶችና ውድቀቶች ሲፈጸሙ ዝም ብሎ “አገር አትፈርስም” እያለ ከመደስኮር በስተቀር ያመጣው ተጨባጭ መፍትሄ የለም፡፡ ማንም እንደሚታዘበው ሰውየው አስተሳሰቡ ጨቅላና እንጭጭ ነው፡፡ እውቀትና ችሎታ የለሽ ብቻ ሳይሆን ፈሪም ነው፡፤ በተፈጥሮ ፈሪ ሰው ጨካኝ ሲሆን ጀግና ግን ሩህሩህ ነው፡፡ ስንኖር ኢትዮጵያዊያን ስንሞት ኢትዮጵያ ነን ብሎ እንዳልተናገረ ሁሉ ኦቦ ጃዋር ተከበብኩ ብሎ በኦሮሙማ መንጋ ያስጨፈጨፋቸውን ንጹሀን አብይ በዘር እየለየ ቆጠረልን፡፡ ሰውየው ችሎታ ቢስ ነው እንጅ ወያኔ የሰሜኑን ጦር እንዳይንቀሳቀስ መንገድ ዘግቶ ሲያግደው ያኔዉኑ በትኩሱ በወያኔ ላይ እርምጃ ወስዶ ቢሆን ኖሮ ጦሩ ለትናንትናው የወያኔ እርድ ባልተዳረገም ነበር፡፡ በትግራይ ጦርነቱም ባልተፈጠረ ነበር፡፤ ሌላም እናንሳ፦ ሱዳኖች ወረራውን ያካሄድነው አብይ ቦታውን ያዙት ብሎን ነው ብለው በይፋ ሲናገሩ እርሱ ስለዚህ ጉዳይ እስካሁን ምንም ያለው ነገር የለም፡፡እንደገና ሌላም እናንሳ፦ አብይ አገር በጠላት ስትወረር፡ በሾማቸው ኦሮሙማወች ህንጻወች ሲዘረፉ ፡21 ባንኮች በመንጋው ታፍነው የህዝብና የመንግስት ገንዘብ ሲመዘበር፡ ኣያሌ የህዝብ ንብረት ሲሰረቅ፡ ሙስና ሲንሰራፋ ወዘተ ምንም ሳይተነፍስ ቀርቶ ነገር ግን ቦሌ መንገድ ላይ ያስተከለው አበባ ጠፋ ብሎ አፉን ሞልቶ ለህዝብ የተናገረ ሰው ነው፡፡ ታዲያ ይህንን ዘረኛ የኦሮሙማ ቁንጮ ለታሪክና ለፍርድ ከማቅረብ ሌላ ለእምዬ ኢትዮጵያ ምን ፋይዳ ኖሮት እንደመሪ እንቆጥረዋለን? ይህንን አይነቱንስ የገማና የገለማ የኦሮሙማ አገዛዝ ምን ያህል እንታገሰዋለን? መጥኔ ለእኛ !!

 

Source link