91.11 F
Washington DC
June 21, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“ኤርትራዊ ነን” በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ የኖሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ

ጀርመን መረጃ መጠየቅ ጀምራለች

“የማንፈልገው ጉዳይ ውስጥ እየገባን ነው” ይላሉ ዜናውን ያረጋገጡት ዲፕሎማት። ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆነው የጎልጉል የዘወትር ተባባሪያችን እንዳሉት አንዳንድ አገራት የስደተኞች መረጃ ለመጠየቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ጀርመን ወደ ሥራ ገብታለች።

በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ድንበር አካባቢ ባሉ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ በተመዘገቡ ስደተኞች ስም በርካታ የትግራይ ተወላጆች “ስደተኛ ናቸው” በሚል ከአገር እንዲወጡ መደረጉን እንደ አንድ ምክንያት ጠቅሰው የዓለምአቀፉ የስደተኞች ተቋም ትግራይ ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ላይ ያሉት ካምፖች እንዲዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው ጥያቄው የተነሳው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ንግግራቸው የኤርትራን ወደ ትግራይ መግባት አስመልክቶ ሲናገሩ ይህንኑ ማለታቸውን ተከትሎ የጀርመን ኤምባሲ ጉዳዩን ለአገሩ ወዲያው ሪፖርት አድርጓል።

እንደ ዲፕሎማቱ ገለጻ ሌሎች የአውሮጳ አገራትም የማጣራት ሥራ የመሥራት ዕቅድ አስቀድሞ የነበራቸው ቢሆንም ሰሞኑንን በኦፊሻል ባይሆንም በግል ጥያቄ እንዳቀረቡላቸው አስታውቀዋል።

ጀርመን የትግርኛ ተናጋሪ ስደተኞችን አጠቃላይ መረጃና ግንኙነት በማጥናት እርምጃ እንደምትወስድ መስማታቸውን የጠቀሱት ዲፕሎማቱ “ወንጀለኞችን ለፍትሕ ማቅረብ አግባብ ቢሆንም እንዲህ ያለው ጉዳይ በአንድ የድሃ አገር ነዋሪዎች ላይ እንዲከሰት በግል አልመኝም” ብለዋል። ጀርመን ለዚህ ተግባር ይጠቅመኛል ያለችውን መረጃ መጠየቋን እንደሚያውቁ አመልክተዋል።

ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይህንን መተግበር ብዙም የሚከብድ አይደለም ይላሉ። አብዛኛዎቹ “ኤርትራዊ ነን” በማለት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙ የትህነግ ደጋፊች እነማን እንደሆኑ ይታወቃሉ፤ ሰልፍ ሲወጡ ፎቶዎቻቸው እና ቪዲዮ ተሰብስቧል፤ ከዚህ በላይ በየራሳቸው የማኅበራዊ ሚዲያ የሚለጥፉት በየጊዜው “ስክሪንሾት” እየተደረገ ተቀምጧል። እስከዛሬ “ኤርትራዊ ነን” ብለው ሌላ ነገር ሲያደርጉ ስላልታዩ ምንም ማለት አልተቻለም ነበር። አሁን ግን ትግሬ መሆናቸውን በግልጽ በመናገር ለትህነግ በአደባባይ በሚሰጡት ድጋፍ ነገሩን አቅልለውልናል፤ አሁን መንግሥታት ይህንን መጀመራቸው ከታወቀ መረጃ ለማቀበሉ ብዙም ችግር እንደማይኖር ሃሳባቸውን ለጎልጉል ተናግረዋል።

በዚህ የማጋለጥ ዘመቻ በተለይ ኤርትራዊያን እንዲተባበሩ ጥሪ የቀረበ ሲሆን በስማቸውና በማንነታቸው በትህነግ ሰዎች የደረሰባቸውን ግፍ እና ስም ማጥፋት በተገቢው የሕግ አግባብ ወደ መጨረሻ ማድረስ የሚችሉበት ጊዜ አሁን መሆኑ ተጠቁሟል።    

በትግራይ የሚገኘውን የስደተኛ ካምፕ አስመልክቶ የዛሬ ዓመት ጎልጉል ይህንን ጽፎ ነበር፤

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተለያዩ ወገኖች የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በዚህ “ኤርትራውያን” ይኖሩበታል በሚባለው የስደተኞች መጠለያ በአብዛኛው እየተጠቀሙ የነበሩት ከህወሓት ጋር የጥቅም ግንኙነት ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ነበሩ። ከኢትዮጵያ ውደ አውሮጳ የሚፈልሱ የትግራይ ተወላጆች በተለይም ከህወሓት ሹሞች ጋር ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸው አውሮጳ ከመሰደዳቸው በፊት ኤርትራውያን እንደሆኑና አውሮጳ ሲደርሱ በቀላሉ የመኖሪያ ፈቃድ ሊያስገኝላቸው የሚችል ሰነድ ይዘው የሚወጡት ከዚህ የስደተኞች ማዕከል ነው።

ከአገር አስቀድመው ሰነዶችን አዘጋጅተው ከወጡ በኋላ ከአውሮፓ አገራት በአንዱ የመኖሪያ ፈቃድ ጠይቀው በርካቶች ዓመታት የሚወስድባቸውን በጥቂት ወራት ለማግኘት ሲችሉ ቆይተዋል። ከዚህ ሌላ እነዚሁ የህወሃት ሰዎች ወረቀታቸውን ካገኙ በኋላ ቀጣዩ ሥራቸው ባሉበት የአውሮጳ ከተማ ወይም አገር ማን ምን እንደሚያደርግ፤ ማን ሰልፍ እንደሚወጣ፤ ስብሰባ እንደሚደራጅ፤ ወዘተ መረጃ እየሰበሰቡ ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ትልቅ የስለላ ሥራ ሲሠሩ ቆተዋል። የደብረጽዮን “ማንኛውም ኃይል” ሊዘጋው አይችልም ፍርሃት ከዚህ ጋር የተቆራኘ ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት ይሰጣል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & EmailSource link

Related posts

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አወቃቀር እንደ ሰው ልጅ አካል የበርካታ አካላት ድምር ውጤት ነው-ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

admin

ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ ስናይፐር፣ ብሬን፣ ሽጉጥና ከ5 ሺህ በላይ ልዩ ልዩ ጥይቶች ተያዙ

admin

የገንዘብ እጥረት የባሕር ዳርን ስታዲዬም ጣሪያ እንዳይለብስ አድርጎታል፡፡

admin