87.71 F
Washington DC
June 15, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም”

የቀድሞው ኢህአዴግ ካድሬዎች እና የህወሓት ጀነራሎች ሂሳብ አስተማሪው ኤርሚያስ ለገሰ ሆን ብሎ በቁጥር ሊጫወት ሞክሯል፡፡ አላማው ኢዜማ የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ሊያሸንፍ እንደማይችል አስመስሎ መሳል ነው፡፡ ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ሆኖበት ነው፡፡

ኤርምያስ ሹመት አስቦ የለውጡ ደጋፊ የነበረ ጊዜ የተናገረው

የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም፡፡ ምናልባት እንዲገባው ከዚህ በፊት ከነበረው የተቃዋሚዎች ዕጩዎች ቁጥር በ11% እድገት አሳይተናል እንበለው ይሆን?? ምንም እንኳን [ለእንደዚ አይነቱ አውቆ አበድ መፍትሄው] ንቆ መተው ቢሆንም ያቀረበውን የተንኮል መረጃ እንደ እውነት ሊወስዱ የሚችሉ ቅኖችን ከስህተት ለማዳን ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁ፡፡

ምርጫ የሚደረገው በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ፦

አዲስ_አበባ – ለክልልም ሆነ ለተወካዮች ምክር ቤት ሙሉ ዕጩዎችን ያስመዘገበው ብቸኛው ፓርቲ ኢዜማ ብቻ ነው፡፡ (ከአብን እና ከመኢአድ ጋር በጋር ዕጩዎችን አቅርቦ በስሙ የሚወዳደሩት ባልደራስም ሆነ ገዢው ፓርቲ ሙሉ ዕጩዎችን አላቀረቡም!)

ደቡብ ክልል – በፌደራልም ሆነ በክልል ምክር ቤት በሁሉም ወንበሮች እንወዳደራለን።

አማራ ክልል – በፌደራልም ሆነ በክልል ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ እንወዳደራለን።

ጋምቤላ – ያለው የክልል ም/ቤት ወንበር 155 ነው በ114 የክልል ም/ቤት ተወዳዳሪ አቅርበናል የተቀሩት 41 ላይ በምዝገባ ችግር ስለተፈጠረብን ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቅርበናል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ እንወዳደራለን።

ሀረሪ – 36 ወንበር ነው ያለው – በአንደኛው ምርጫ ክልል ሙሉ 18 ዕጩዎች ያቀረብን ሲሆን በሌላኛው ምርጫ ክልል ለአደሬ ብሄረሰብ ብቻ የተተወውን 9 ወንበር ጨምረን ዕጩ አቅርበናል የጎደለን 4 የክልል ምክር ቤት ዕጩ ብቻ ነው፡፡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ለአደሬ ብሔረሰብ የተተወውን ወንበር ጭምር ዕጩ አቅርበንበታል፡፡

ሲዳማ – ካሉት 19 ወረዳዎች በ16ቱ አብላጫውን ዕጩዎች አቅርበናል በተቀሩት በ3ቱም ዕጩ ብናዘጋጅም በምርጫ ቦርድ ምክኒያት አልተመዘገቡም ቅሬታ ለምርጫ ቦርድ አስገብተናል።

አፋር – በተቃዋሚዎች ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ ለክልል ምክር ቤት 50 ሲደመር 1 ወንበር ማሸነፍ የሚያስችል ዕጩዎች አቅርበናል በሕዝብ ተወካዮ ምክር ቤትም አባላ ከምትባል ወረዳ እና በትግራይ ድንበር አካባቢ ካለ አንድ ወረዳ ውጪ በሁሉም ዕጩ አቅርበናል።

ቤኒሻንጉል_ጉምዝ – በፀጥጻ ችግር ምክኒያት በ4 ወረዳዎች ዕጩ ማቅረብ አልቻልንም በ5 ወረዳዎች የተወካዮ ምክር ቤት እና ከፊል የክልል ምክር ቤት ዕጩ አቅርበናል።

ኦሮሚያ – በሕዝብ ተወካዮችም ሆነ በክልል ምክር ቤት ዕጩዎችን ለማስመዝገብ ከፍተኛ ተግዳሮት ገጥሞናል ለምርጫ ቦርድ በዝርዝር ቅሬታ ያቀረብን በመሆኑ መልስ ስናገኝ ዝርዝሩን እመለስበታለሁ።

ሱማሌ – ለክልል ምክር ቤት ያቀረብናቸው ዕጩዎ 50 ሲደመር አንድ አይሞሉም ለፓርላማም ያቀረብናቸው 11 ዕጩዎን ብቻ ነው። (13 ቦታ ላይ ዕጩ አላቀረብንም)

በክልል ምክርቤት ብቻችንን የክልል መንግስት የመመስረት ዕድል የሌለን በኦሮሚያ፤ በሶማሌ እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ብቻ ነው፡፡ እነሱንም የፀጥታው ችግር ሲስተካከል አሻሽለን በሚቀጥለው አናሻሽላለን፡፡

ሰውን ተስፋ አስቆርጦ በምርጫው ተስፋ እንዲቆርጥ ለማድረግ ያደረከው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡ ከቻልክ ከቻልክ የራስህን ፓርቲ ለማጠንከር ሞክር፤ የእኛን ለኛ ተውልን፡፡

ኢዜማ የተስፈኞች ቤት ነው፡፡ እንኳን ባንተ አይነቱ ከሩቅ ተኳሽ አጠገባችን ባሉት ገዳዮቻችን እንኳን ተስፋ አንቆርጥም፡፡

ኢዮብ መሳፍንት፤ የኢዜማ ዓለም አቀፍ አባላት ተጠሪና የሕግ ባለሙያ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & EmailSource link

Related posts

የእናቶችን ሞት 50 በመቶ ለመቀነስ እየተሰራ ነው – ጤና ሚኒስቴር

admin

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኖርዌይ አቻቸው ጋር ተወያዩ፡፡

admin

ኢትዮጵያን ለማዳከምና አንድነቷን ለማናጋት ከየትኛውም አካል የሚሰነዘር ትንኮሳ እና ጫና በአንድነት ልንመክት ይገባል -አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ

admin