71.89 F
Washington DC
June 22, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ኢትዮጵያ “failed state” አይደለችም – የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት

የም/ቤቱ አባላት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነፃነት እና የግዛት አንድነት ያላቸውን ጠንካራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በክልሉ ላለው ቀውስ እልባት ለመስጠት የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወነ ያለውን ተግባር አድንቋል፡፡

መግለጫው እንደሚለው፣ የፀጥታው ም/ቤት አባላት የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብዓዊ ዕርዳታን ለማቅረብ እና ሰብዓዊ ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ እያደረገ ላለው ጥረት እውቅና ሰጥተዋል፡፡ ይሁንና የም/ቤቱ አባላት የሰብዓዊ ችግሮች አሁንም መኖራቸውን እንደሚገነዘቡ እና በክልሉ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸውም ነው መግለጫው ያመለከተው፡፡

ከምግብ ዋስትና ጋር በተያያዘም የሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ መጨመር እንዳለበት እና ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ለሁሉም የተቸገሩ ወገኖች ተደራሽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

ከተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ አስቸኳይ እርዳታ መርሆዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ሰብዓዊነትን፣ ገለልተኛነትን እና ነፃነትን መሰረት በማድረግ የሚከናወኑ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶች እንዲቀጥሉ የፀጥታው ም/ቤት አባላት ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

በትግራይ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለቀጣይ የሰብአዊ አገልግሎቶች እንቅፋት መሆኑን በመግለጽ መደበኛ ሁኔታው እንዲመለስም አባላቱ መጠየቃቸው በመግለጫው ተካቷል ፡፡

በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የፆታ ጥቃት እንደሚፈጸም የሚያመለክቱ ሪፖርቶችን ጨምሮ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች ላይ የተሰማቸውን ጥልቅ ስጋት በመግለፅ፣ ምርመራ ተደርጎ ጥፋተኞች ለህግ እንዲቀርቡም ነው የፀጥታው ም/ቤት አባላት የጠየቁት፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች ላይ የሚያካሂዱትን የጋራ ምርመራ በአድናቆት ተቀብለዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተሳትፎም የፀጥታው ም/ቤት አባላት በአድናቆት መቀበላቸው ተገልጿል፡፡

ዓለም አቀፍ ህግን ሙሉ በሙሉ ማክበር አስፈላጊ መሆኑንም አባላቱ አሳስበዋል ፡፡

የም/ቤቱ አባላት ለአህጉራዊ እና ለክፍለ-አህጉራዊ ጥረቶች እና ድርጅቶች ማለትም ለአፍሪካ ህብረት እና ለኢጋድ ያላቸውን ጠንካራ ድጋፍ የገለጹ ሲሆን የድርጅቶቹ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስምረውበታል፡፡

የፀጥታው ም/ቤት አባላት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነፃነት፣ የግዛት እና ሀገራዊ አንድነት ያላቸውን ጠንካራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡ (አል-ዐይን)

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ጎልጉል ያነጋገራቸውና ለጉዳዩ ቅርብት ያላቸው የዲፕሎማሲ ኤክስፐርት እንዳሉት ይህ የጸጥታው ምክር ቤት ወሳኔ በዲፕሎማሲ አነጋገር ኢትዮጵያ “failed state” አይደለችም፤ መንግሥት ያለባት አገር ነች፤ የግዛቷ ልዕልና እናከብራልን፤ የድንበሯን ወሰን እናከብራልን፤ ሰላም አስከባሪ ኃይል አንልክም፤ የራሷን ችግር መወጣት የሚችል ብቃት ያለው መንግሥት ያለባት አገር መሆኑን አረጋግጠናል የሚል መግለጫ ነው ብለዋል።

ይህ የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ያነሳሳውና በቴድሮስ አድሃኖም፣ በብርሃነ ገብረክርስቶስ እንዲሁም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከእነርሱ ጋር በማበር ኢትዮጵያ መንግሥት የሌለባት አገር (failed state) ነች ሲሉ ለነበሩ ሚዲያ ላይ ሲደሰኩሩ እና ጋዜጣዊ መግለጫና ሲሰጡ ለነበሩ ቅስም ሰባሪ፣ አንገት አስደፊ ውሳኔ ሆኖ መገኘቱ በሥፋት እየተወራበት ያለ ዜና ሆኗል። (ፎቶ፤ ከቀድሞ የUNSMIL ክምችት)

UN Security Council reaffirms commitment to Ethiopia’s sovereignty, political independence and unity

The UN Security Council member countries reaffirms commitment to Ethiopia’s sovereignty, political independence and unity. And acknowledged the efforts by the Government of Ethiopia to provide humanitarian assistance and to provide increased humanitarian access.

Security Council Press Statement on Ethiopia

The following Security Council press statement was issued today by Council President Dinh Quy Dang (Viet Nam):

The members of the Security Council noted with concern the humanitarian situation in the Tigray region, Ethiopia.

The members of the Security Council acknowledged the efforts by the Government of Ethiopia to provide humanitarian assistance and to provide increased humanitarian access.  The members of the Security Council recognized, nevertheless, that humanitarian challenges remain.  They called for a scaled-up humanitarian response and unfettered humanitarian access to all people in need, including in the context of the food security situation.

The members of the Security Council called for a continuation of international relief efforts in a manner consistent with the United Nations guiding principles of humanitarian emergency assistance, including humanity, neutrality, impartiality and independence.  The members of the Security Council noted that insecurity in Tigray constitutes an impediment to the ongoing humanitarian operations and called for a restoration of normalcy.

The members of the Security Council expressed their deep concern about allegations of human rights violations and abuses, including reports of sexual violence against women and girls in the Tigray region and called for investigations to find those responsible and bring them to justice. They welcomed the joint investigation by the Office of the United Nations High Commissioner for Human Rights (OHCHR) and the Ethiopian Human Rights Commission into alleged human rights violations and abuses.  The members of the Security Council also welcomed the engagement on this issue of the African Commission on Human and People’s Rights.

The members of the Security Council stressed the need for full compliance with international law.

The members of the Security Council reiterated their strong support to regional and subregional efforts and organizations, namely the African Union and the Intergovernmental Authority on Development (IGAD), and underscored the importance of their continued engagement.

The members of the Security Council reaffirmed their strong commitment to the sovereignty, political independence, territorial integrity and unity of Ethiopia.

Read the original press release here

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & EmailSource link

Related posts

መሬት አስረክቦ ትዕግስት – እግር እያስበሉ ዝምታ …!!! (አባይነህ ካሴ)

admin

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች  216 ሺህ ብር አበረከቱ

admin

የጥፋት ሀይሎችን ህግ ፊት ለማቅረብ መንግስት እየሰራ ይገኛል- የሰላም ሚኒስቴር

admin