51.91 F
Washington DC
May 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“ኢትዮጵያ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት በኩል እንዲካሄድ የያዘችው አቋም ለሕብረቱ ያላትን ክብርና እውቅና የሚያሳይና የሚደነቅ ነው” መሀመድ አል አሩሲ አክቲቪስትና የፖለቲካ ተንታኝ“ኢትዮጵያ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት በኩል እንዲካሄድ የያዘችው አቋም ለሕብረቱ ያላትን ክብርና እውቅና የሚያሳይና የሚደነቅ
ነው” መሀመድ አል አሩሲ አክቲቪስትና የፖለቲካ ተንታኝ
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን ወክሎ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ
በመከራከር የሚታወቀው መሀመድ አል አሩሲ እንዳለው ኢትዮጵያ የታላቁን ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሚነሱ ችግሮች
በአፍሪካውያን እንዲፈታ የምታደርገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለአፍሪካውያን አብሮነት መጠናከር እንዲሁም ችግራቸውን
በራሳቸው መፍታት እንደሚችሉ ጥልቅ መነቃቃት እንዳላት ማሳያ ነው።
የአፍሪካ ችግሮች መፈታት ያለባቸው በአፍሪካ ነው ያለው መሀመድ አል አሩሲ “ኢትዮጵያ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት በኩል
እንዲካሄድ የያዘችው አቋም ለሕብረቱ ያላትን ክብርና እውቅና የሚያሳይና የሚደነቅ ነው” ብሏል፡፡
‹‹ገመናችንን፤ ችግራችንን ውጭ ማውጣት ትልቅ ውርደት ነው። እንደእኔ እምነት አማራጭ ሲጠፋ ሌሎች ሀገራት በጉዳዩ
እንዲገቡ ማድረግ ይቻል ነበር ፤ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ሁሉንም አማራጭ መጠቀም ሳይቻል ወደ ሌላ ማቅናት አሳፋሪ ነው።
በዚህ ረገድ ግብጽና ሱዳን ጉዳዩን ወደ ውጭ አካላት ለመውሰድ የሚያደርጉት ጥረት ድርድሩን ለማበላሸት ካላቸው ፅኑ ፍላጎት
የተነሳ መሆኑን ገልጿል።
እንደ መሃመድ አል አሩሲ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በዲፕሎማሲ ረገድ እያደረገ ያለው ጥረት በጣም የሚደነቅና መላውን
ኢትዮጵያውያንን ያኮራ ነው። በተለይም የሀገሪቱን ጥቅም አለማስደፈሩ ትልቅ ከበሬታ ሊሰጠው ይገባል። ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን
ዓለምአቀፋዊ ተፅእኖ ለመፍጠር እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ በመመከት ረገድ ብዙ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ አመላክቷል፡፡
በዲፕሎማሲም ሆነ በሚዲያ ዘመቻ በኩል ትልቅ ሥራ ይጠበቅብናል፤ ይህንን ሥራ በተደራጀና በተጠና መንገድ ማከናወን
ይገባልም ነው ያለው።
‹‹አንዳንዱን ነገር በጣም በጥንቃቄ መመልከትን ፣ ማጥናት፣ አዳዲስ ነገሮች በደንብ መከታተልን የሚጠይቅ ነው ያለው
መሀመድ ውጤታማ ለመሆን ራስን በአግባቡ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግም አመልክቷል።
እንደ መሀመድ አል አሩሲ ማብራሪያ፤ ግብጽ ያላትን ክብር ኢትዮጵያም በዓለም ሆነ በአፍሪካ ላይ አላት። ሌላው ይቅርና ኢትዮጵያ
በአረብ ሀገራትም ጭምር ትልቅ ክብር፣ታሪክ እና ሕዝብ ያላት ሀገር ናት። በመልከዓ ምድራዊ አቀማመጧም በአረብ ሀገራቱ ዘንድ
ትልቅ ስፍራ ያላት ናት። በቀደሙት ዓመታት ከአረብ ሀገራት ጋር የነበራት ግንኙነት ትልቅ ክፍተት ነበረው። አብዛኞቹ የአረብ ሀገራት
ስለኢትዮጵያ በቂ እውቀት እንዲኖራቸው አልተደረገም።
በተቃራኒው ደግሞ ግብጽ በብቸኝነት የራስዋን አጀንዳ ታስተላልፋለች፤ በተለይም ባሏት በርካታ መገናኛ ብዙኃን ሁሉ በመጠቀም
የራሷን ችግር ብቻ መግለጿን ጠቁሟል፡፡”በአንፃሩ በኢትዮጵያ በኩል ዝምታ ነበር ፣ ያ ክፍተት አሁን ላለንበት ችግር መንስኤ
ሆኗል” ብሏል።
በሀገራቱ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት በመጠቀም ጉዳዩን በሁለቱም ወገን በኩል እንዲያዩት ማድረግ እንደሚገባ
ያመለከተው አቶ መሀመድ እውነቱን እንዲያዩ እና እንዲፈርዱ ማድረግ መቻል አለብን ነው ያለው፡፡ አሁን ላይ ኢትዮጵያ በዚህ
ረገድ ያለባትን ክፍተት እያሻሻለች መሆኗን ጠቅሶ፤ ራሷን እያስተዋወቀች ስለመብቷም ሆነ ግዴታዋ በደንብ መልእክት ማስተላልፍ
መጀመሯን አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በጉልበት የሚደረግባትን ጫና ፈፅሞ ትቀበላለች የሚል እምነት እንደሌለው የተናገረው መሀመድ አል አሩሲ “ከዚህ
ቀደምም ወራሪዎችን አዋርዳ እንዳባረረችው እና ራሷን እንዳስከበረችው ሁሉ አሁንም የሚደረግባትን ጫና ተቋቁማ
ወደምትፈልገው ልማት ትደርሳለች” የሚል እምነት እንዳለው አመልክቷል።
የግብጽ እና ሱዳን መንግሥታት የሚያደርጉት ጫና ቢኖርም በሦስቱ ሀገራት ሕዝቦች መካከል ያለው ግኑኝነት ጥሩ በመሆኑ
ይህንን በማጠናከር ወደ መግባባት መሄድ የሚቻልበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ መግለጹን ኢትዮ ፕረስ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleʺጎንደር ከግንቡ ላይ ያለው ነጭ አንበጣ ፣ ከምን ሊገባ ነው አሞራው ሲመጣ”

Source link

Related posts

ሱማሌ ክልልን ለሁሉም ተምሳሌት ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡

admin

በአሜሪካ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 ሚሊየንን አለፈ

admin

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ለማድረግ የተቀናጀ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።

admin