76.68 F
Washington DC
June 17, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“ኢትዮጵያ የራሷን ችግር የመፍታት አቅም አላት፣ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ላይ እጇን ታንሳ” የባዕከር ከተማ ነዋሪዎች

“ኢትዮጵያ የራሷን ችግር የመፍታት አቅም አላት፣ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ላይ እጇን ታንሳ” የባዕከር ከተማ ነዋሪዎች

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 03/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሑመራ ከተማ የተጀመረው የአሸባሪው ሕወሓት ግፍን የማውገዝና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬም በባዕከር ከተማ ቀጥሎ ውሏል። ነዋሪዎቹ አሸባሪው ሕወሓት የፈፀመባቸውን ግፍ በተደጋጋሚ ሲያወግዙ ኖረዋል። ከግፋቸው በላይ ሌላ ግፍ እንዲፈፀምባቸው የውስጥና የውጭ ጫናዎች በመበራከታቸው የተቃውሞ ሐሳባቸውን ዳግም ለማሰማት ወደ አደባባይ ወጥተዋል። ነዋሪዎቹ የተለያዩ መልእክቶችን ይዘው አሸባሪውን ሕወሓት አውግዘዋል፣ ጫና የሚያደርሱትን ተቃውመዋል፣ እውነታቸውን እውነት ለሚወድ ሁሉ አስተላልፈዋል።

የባዕከር ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ ማርዬ ጥሩዓለም አሸባሪው ሕወሓት ተጠራርጎ እስኪወጣ ድረስ ግፍና በደል ሲደርስብን ኖሯል ብለዋል። በማንነታቸው ብቻ ለዓመታት ግፍና በደል ሲደርስባቸው የጠየቃቸው እንዳልነበር ያስታወሱት ነዋሪዋ በግፍ ብንኖርም ዛሬ ላይ ማንነታችን ተመልሷል፣ ደስተኞችም ነን ነው ያሉት። የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻን ከልብ እናመስግናለን ብለዋል፡፡ የአሸባሪውን ሕወሓትን ግፍ እናወግዛለን፣ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት በፅኑ እንደሚቃወሙም ተናግረዋል። ለማንነት እና ለሉዓላዊነት በሚደረገው ትግል ወደ ኋላ እንደማይመለሱም ገልፀዋል።

አደም በርሄ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ ሲደርስ የነበረው ግፍና መከራ አሰቃቂ እንደነበር ነው ያስታወሱት፣ አማራ በመሆናቸው ብቻ ሀብት እንዳያፈሩ መሬታቸውን እየወረሱ፣ እያሳደዱ፣ እየገደሉ ግፍ ይፈፅሙባቸው እንደነበርም ተናግረዋል። የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በደል በዛብን ብሎ ሲነሳም ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሲጨቁኑን ኖረዋልም ብለዋል። ዛሬ ላይ እንደ አዲስ እንደተፈጠርኩ እቆጥረዋለሁ፣ አሸባሪው ሕወሓት በወልቃይት ጠገዴ ቦታ የለውም ነው ያሉት። ምዕራባዊያን አካሄዳቸውን ያስተካክሉ፣ ከዚህ በኋላ የአማራ ሕዝብ ለማንም ተገዥ አይሆንምም ነው ያሉት።

ወይዘሮ አልማዝ ነጋሽ በነፃነት ሰልፍ ወጥተን አናውቅም፣ በማንነታችን ምክንያት ተሸማቀን ነው የኖርነው፣ አሁን ግን በአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና የመከላከያ ሠራዊት ነፃ ወጥተናል ብለዋል። የእኛ ጠላታችን ሕወሓት እንጂ ሰላማዊ የትግራይ ሕዝብ አይደለምም ብለዋል። ኢትዮጵያ የራሷን ችግር የመፍታት አቅም አላት፣ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ላይ እጇን ታንሳ ነው ያሉት።

በሰላማዊ ሰልፉ መልዕክት ያስተላለፉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አማረ ጎሹ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ለዓመታት ግፍና በደል ሲደርስበት ግፉን በጸጋ ያልተቀበለ ለማንነቱ ሲታገል የኖረ ሕዝብ መሆኑን ገልጸዋል። ያለ ፈቃዱ ማንነት ተሰጥቶት ግፍ የተፈፀመበት የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ሲያነሳቸው በነበሩ ጥያቄዎች በአሸባሪዎች ግፍ ሲፈጸምበት ኖሯል ብለዋል። በማንነት ጥያቄ ምክንያት ብዙዎች መስዋዕት መሆናቸውንም አንስተዋል። የሕዝብ ትግል እያየለ ሲመጣ አሸባሪው ሕወሓት ከስልጣን መውረዱንም አስታውሰዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ያገኘው ድል ያልተመቻቸው ጠላቶች አሁንም አለማረፋቸውን ገልጸዋል። የውጭና የውስጥ ጠላቶችን ለመዋጋት አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል። ሕዝብን የከዱ አካላት ከስህተታቸው ሊታረሙ ይገባልም ብለዋል። በወልቃይት ጠገዴ የልማት ሥራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባም ኀላፊው ተናግረዋል፡፡ የአሸባሪውን ሕወሓት ቅሪት መታገል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ዘመናት የተሻገረ የሀገረ መንግሥትነት ታሪክ ያላት፣ ኢትዮጵያውያንም አንድ የሆነ ስነ ልቦና ያላቸው በመሆኑ ማንም ጠላት ቢመጣ ሳትንበረክክ ትሻግራለች ነው ያሉት። አሁንም የውጭም የውስጥም ጠላቶች ቢበዙም አንሸነፍም ብለዋል። የአሜሪካ መንግሥት የሚያደርገው ሙከራ የማይሳካ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ነው ያሉት። አሸባሪው ሕወሓትን መደገፍ ስለማንነታቸው ሲሉ በግፍ የተገደሉ የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎችን ድጋሜ መበደል፣ የሕዝብን ነፃነት መጋፋት መሆኑንም ተናግረዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች የድልና የእድል ዘመን ትውልዶች ናቸው ያሉት ኀላፊው ድሉን ዘላቂ ማድረግ፣ ሕዝብን ከጎን በማሰለፍ፣ መለያዬትን በማወገዝ፣ ከትግራይን ሕዝብ ጋር በጋራ መኖር ይገባል ብለዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሕዝብ አማራ ነው፤ ኩሩ፣ እንግዳ ተቀባይ ነውና ዛሬም ይህን ማስቀጠል አለበት ነው ያሉት። መንግሥታት የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ ሐሳብ ተረድተው አብረው እንዲቆሙም ጠይቀዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Source link

Related posts

6ኛው ሀገር አቀፍ የፓራ ኦሎምፒክ ቅርጫት ኳስ ውድድር በባሕር ዳር ተጀምሯል፡፡

admin

በዓለም ላይ የትምህርት፣ ባህልና ቱሪዝም ዘርፎችን ታሳቢ ያደረገ የኮቪድ19 ክትባት አቅርቦት ሊኖር ይገባል-የትምህርት ሚኒስትሩ

admin

የአፋር ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

admin